Get Mystery Box with random crypto!

ቴሌቪዥን ላይ #ጥቁር_ጥላ ለምን ይፈጠራል? LCD ቴሌቪዥኖች በተለያየ ምክንያት ጥቁር ጥላ/dar | Jan Tech - ጃን ቴክ 📱

ቴሌቪዥን ላይ #ጥቁር_ጥላ ለምን ይፈጠራል?

LCD ቴሌቪዥኖች በተለያየ ምክንያት ጥቁር ጥላ/dark shadow ሊፈጥሩ ይችላሉ። ከነዚህም ምክንያቶች መካከል ስክሪን ውስጥ የሚገቡ ቆሻሻዎች፣ ከላይ ስክሪኑ ሲቆሽሽ፣ የሞቱ ፒክስሎች (dead pixels) አሊያም የማይንቀሳቀሱ ፒክስሎች (stuck pixels) የተወሰኑት ናቸው። ከነዚህ መካከል የቀደሙት ሁለቱን በቀላሉ መፍታት ሲቻል በሞቱ እና በማይንቀሳቀሱ ፒክስሎች አማካኝነት የሚፈጠሩ ጥቁር ጥላዎችን ማጥፋት ግን ቀላል የሚባል አይደለም።

ምክንያቶቹ ምንድናቸው?

የማይንቀሳቀሱ እና የሞቱ ፒክስሎች በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ከነዚህም መካከል
“burn in” አንዱ ነው። ይህም ቴሌቪዥኖች ላይ የማይንቀሳቀሱ ምስሎች ለረዥም ሰዓት ሲቆዩ የሚፈጠር ነው። የማይንቀሳቀሱ ምስሎች (still image) ቴሌቪዥን ስክሪን ላይ ለረዥም ጊዜ በሚቆዩ ጊዜ የቴሌቪዥኑ ስክሪን የምስሎቹን ቀለም የመያዝ እና የማስቀረት እድል ይኖረዋል። ይህም በረዥም ጊዜ የቴሌቪዥናችን ስክሪን ጥቁር ጥላ(black shadow) እና ጥቁር ነጥብ(black spot) እንዲያመጣ ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ ቴሌቪዥናችንን ማንም በማይጠቀምበት ጊዜ መዝጋት ይመከራል።

በተጨማሪም የማይንቀሳቀሱ ምስሎች (ለምሳሌ ያቆመነው ቪዲዮ) ከግማሽ ሰዓት በላይ ቴሌቪዥኖች ስክሪን ላይ መቆየት የለበትም።

                  
#Share
Via
Ethio tech

@jantech24