Get Mystery Box with random crypto!

ዲፕ ፌክ (#deep_fake) እና ሊፕ ሲንክ (#lip_synch) ምንድን ናቸው? አሁን አሁን | Jan Tech - ጃን ቴክ 📱

ዲፕ ፌክ (#deep_fake) እና ሊፕ ሲንክ (#lip_synch) ምንድን ናቸው?

አሁን አሁን እጅግ በረቀቀ መልኩ የሚሠሩ የምስል፣ የቪድዮ እና የድምፅ ቅንብሮች መታየት እየጀመሩ ነው። አንዳንዶቹ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (#AI) ጭምር በመታገዝ የሚሠሩ ሲሆን እውነት ይሁኑ ሐሰት መሆናቸውን ለመለየት አዳጋቾች ናቸው።

ፊት መቀያየር (face swap)፣ ፊት ቆርጦ ቀጥል (#re-face) እና ምስሎችን ማናገር (#talking faces) የተወሰኑት የዲፕ ፌክ አይነቶች ሲሆኑ የአይነታቸው ስፋት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፣ ይህም ከሶፍትዌሮች መዘመን እና ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መዘመን ጋር እንደሚገናኝ የዘርፉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።

ይህ ምስልን እና ድምፅን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት በማቀናበር የሚሠራ ቴክኖሎጂ ያልተባለን እንደተባለ፣ ያልተደረገን እንደተደረገ አርጎ ለማቅረብ ያስችላል።

ይህ ማለት የመሪዎችን፣ የሚድያ ሰዎችን፣ የታዋቂ ግለሰቦችን ወዘተ ምስል በመውሰድ እና የድምዕ ቅጣዮችን (#sound bites) በሊፕ ሲንክ በመጨመር ለማቀናበር ያስችላል። ሊፈጥር የሚችለውን ችግር ማሰብ ቀላል ነው፣ ለምሳሌ የሀገሪቱ መሪ መግለጫ ሳይሰጡ ነገር ግን እንደሰጡ ተደርጎ ለመለየት በሚያስቸግር የምስል እና ድምፅ ቅንብር ሊቀርብ ይችላል።

በተለይ አሁን ላይ #Generative Adversarial Networks (#GANs) የተባለውን እና ሁለት የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ስልተ-ቀመሮችን (#algorithms) በአንድ ላይ በማጣመር የሚሠራውን የቅንብር ሥራ ከእውነተኛው ለመለየት ለዘርፉ ባለሙያዎች ጭምር እጅግ ፈታኝ ሆኗል።

ይህን ችግር በመረዳት የቻይና እና የአሜሪካ መንግስታት ዲፕ ፌክን እንደ ትልቅ የስጋት ምንጭ በደህንነት ፕሮግራሞቻቸው ላይ ቀርፀው አስቀምጠዋል። በተለይ #ቻይና በጃንዋሪ 2019 ዲፕ ፌክን ሰርቶ ማሰራጨትን በግልፅ ከልክላለች።

አሁን ላይ #ዲፕ ፌክ በራችን ላይ ነው፣ ግን አሁንም ቀላል የፎቶ ቅንብሮችን የሚለየው እና በመተግበርያዎች አማካኝነት የሚያጣራው ሰው በጣም ጥቂቱ ነው። #ፌስቡክ ላይ የተፃፈ እና #ዩትዩብ ላይ የተወራ ሁሉ እውነት የሚመስለውን ማንቃት የሚገባቸው ሚድያዎች በዚህ ዙርያ ሲሠሩ አይታይም፣ እንደውም ራሳቸው ሐሰተኛ ምስሎችን እና መረጃዎችን አንዳንዴ እያጋሩ እንደሆነ እናያለን።

በዚህ ዙርያ ለመስራት የሚሞክሩት የመረጃ አጣሪ ተቋማት እና ግለሰቦች ደግሞ በመረጃ እጦት፣ ባልተገባ ፍረጃ እና ውንጀላ፣ በድጋፍ ማጣት እንዲሁም በእውቀት ማነስ ሲቸገሩ ይታያል።

ይህን ችግር በተወሰነ መልኩ ለመከላከል መፍትሄው መረጃዎች ሲሰራጩ ከትክክለኛ አካል የወጡ እንደሆነ ማረጋገጥ ዋነኛው ነው። ለዚህ ደግሞ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆችን፣ ድረ-ገፆችን እና የመልቲሚድያ ቻናሎችን አውቆ መከተል አስፈላጊ ነው።

Via ሳይንስኛ

@jantech24