Get Mystery Box with random crypto!

#China vs #America የቲክቶክ እናት ኩባንያ ባይትዳንስ በአሜሪካ ኢንስታግራምን የሚፎካከ | Jan Tech - ጃን ቴክ 📱

#China vs #America

የቲክቶክ እናት ኩባንያ ባይትዳንስ በአሜሪካ ኢንስታግራምን የሚፎካከር “ሌመን 8” የተሰኘ መተግበሪያውን ይፋ አድርጓል

አሜሪካ በቻይና የቴክኖሎጂ ወረራ እየተፈጸመባት መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች፤ ይህንኑ "ወረራ" ይቀለብሳሉ ያለቻቸውን እርምጃዎችንም ስትወስድ ቆይታለች።

በቲክቶክ የተጀመረው “ወረራ” አሁን ደግሞ ወደ “ሎሚ አቢዮት” ተሸጋግሯል እያለች ነው።

የሜታ ንብረት የሆነውና ጎግል ፕሌይ ላይ ከ5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ያወረዱት ኢንስታግራም፥ በ”ሌመን 8” ከባድ ፉክክር ገጥሞት ከገበያ ይወጣል ወይ የሚለውን ጊዜ የሚፈታው ቢሆንም የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ግን ትልቅ ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡት ነው።

የቻይናው ባይትዳንስ አዲሱን መተግበሪያውን ለሚያስተዋውቁ በርካታ ተከታይ ላላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሜዎችም ከፍተኛ በጀት መድቦ እየሰራ መሆኑን ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል።

በአሜሪካ ከ150 ሚሊየን በላይ የቲክቶክ ተጠቃሚ ያለው ባይትዳንስ፥ አዲሱ የፎቶግራፍ እና አጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ መተግበሪያው ከኢንስታግራም ጋር በብዙ መልኩ እንደሚመሳሰል ተገልጿል።

እንደ ቲክቶክም “Follow” እና “For You” የሚሉ አማራጮችና እንደየፍላጎታችን የመዝናኛ፣ ፋሽን፣ ዜና፣ ስፖርት የመሳሰሉ ፎቶ እና ቪዲዮዎችን ለማቅረብ አስቀድሞ ያስመርጠናል።

ከጉዞ እና ከውበት ጋር የተያያዙ ምክሮችን የሚሰጡ ባለሙያዎችም በ“ሌመን 8” የራሳቸው ገጽ ይኖራቸዋል ተብሏል።

Via ሳይንስኛ

@jantech24