Get Mystery Box with random crypto!

ኢስላማዊ እውነታ

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamictrueth — ኢስላማዊ እውነታ
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamictrueth — ኢስላማዊ እውነታ
የሰርጥ አድራሻ: @islamictrueth
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.31K
የሰርጥ መግለጫ

ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-20 13:33:52
ኢዲን የተመለከቱ ሀዲሶች!
1.5K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 06:15:21
1.5K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 04:42:16 ዘካቱል ፊጥር / የፍስግ ምጽዋት/


ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ተከትሎ በወቅቱ ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ/ አይነት ነው ፡፡ ለግንዛቤ ያህል ዘካተል ፊጥር ከዘካተል ማል ይለያል ።

እያንዳንዱ አባወራ ወይም እማወራ ወይም አስተዳዳሪ የራሱን ጨምሮ በእርሱ ስር እየቀለባቸው ላሉ ቤተሰቦቹ ሁሉ መስጠት ይኖርበታል ፡፡

ማስረጃ

አብዱላህ ኢብን አባስ አላህ ይውደዳቸውና እንዲህ ይላሉ፤
‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም
በ እርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር ለፆመኛ በጾሙ ወቅት ከፈፀማቸው ጥቅም አልባ ውድቅ ንግግሮችና ተግባሮች ጥፋት እንዲሁም የተቃራኒ ፆታ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮቹ ጥፋት ማፅጃ ይሆንለታል ። ለሚስኪኖች (ድሆች) መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውላታል ። ስለዚህም ከኢድ ሰላት በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከ ኢድ ሶላት ቦሃላ ዘካውን የሰጠ እንደማንኛውም ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል ።))
(አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)።

ኢብኑ ሙንዚር አል ኢጅማዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው ‹‹ዒልምን የተማርንባቸው
ዑለሞች ሁሉ ዘካተል ፊጥር ግዴታ መሆኑን
ተስማምተውበታል›› በማለት የ ኡለሞችን አጠቃላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዎል ።

የተደነገገበት ጥበብ

ከላይ ግዴታነቱን ለማመላከት በተጠቀሰው ሀዲስ እንደተጠቀሰው ፣ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው ።

መጠኑ

* የዘካተል ፊጥር መጠን ኢብኑ ኡመር ረዲየላሁ አንሁ ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይዘው ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል: – ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ቁና መስጠት በ እያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያም ሆነ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም )

1 ሷዕ / ቁና/ በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኞች ነው ። ወደ ኪሎ ግራም ሲቀየር እንደየ እህሉ ክብደትና ቅለት ይለያያል ። ለምሳሌ ፣
— አንድ ቁና (ሳእ) ፉርኖ ዱቄት 2.5 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ጤፍ 2·85 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ሩዝ 2·75 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ስንዴ 2·5 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ገብስ 2 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ማሽላ 2·63ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) በቆሎ 2·5 ኪሎ

ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው

— ሙስሊም በሆነ
— ረመዷን ወር ሲጠናቀቅ በህይወት የነበረ
— በእለቱ ለ24 ሰዓት ለራሱና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች ወጪ የሚያደርገው ሀብት ኑሮት ከዚያ የተረፈ ባለው ሰው ።

— * ዘካተል ፊጥር በነፍስ ወከፍ የሚደረግ ኢባዳ ስለሆነ በቤተሰብ ስር የሚኖር ሰው ለራሱ ሚያወጣበት ነገር ካለው ቤተሰቦቹን ከመጠበቅ ራሱ ማውጣት ይኖርበታል ።

ግዜው

* ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻው እለት
ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ የኢድ ሷላት ተሰግዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች (ረዲየላሁ አንሁም) ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት እንደሚቻል ይገልጻሉ ሲተገብሩትም ነበር ።

* ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ነው ። ድንገት አንድ ሰው ረስቶ ወይም ሳይመቸው ቀርቶ በወቅቱ ሳያወጣ ቢቀር ባስታወሰና በተመቸው ወቅት ማውጣት አለበት ።

የሚሰጠው ነገር
* ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶችን በተመለከተ አውጪዎቹ በሀገራቸው ከሚመገቡዋቸው እህሎች ውስጥ ይሆናል ለምሳሌ እንደ ተምር ፣ ዱቄት ፣ እሩዝ ፣ በቆሎ፤ ጤፍ …. ወዘተ ባሉ የምግብ እህል አይነቶች
ነው ። ይህን አስመልክተው የአላህ መልእተኛው ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በሀዲሳቸው የጠቀሷቸው የምግብ እህሎች ( ገብስ፤ ተምር፤ ዘቢብ) ፣ የመሳሰሉት ሲሆኑ፣ ነገር ግን የምግብ አይነቶቹ በነዚህ ላይ ብቻ እንደማይገደቡ የኢስላም ሊቃውንቶች ያስረዳሉ ። በዚህም መሰረት በማንኛውም አካባቢ የሚኖር ሙስሊም ማህበረሰቡ አዘውትሮ ከሚመገባቸው የምግብ እህሎች ዘካተል ፊጥሩን ማውጣት ይችላል፡፡

ለማን ይሰጥ

* ዘካተል ፊጥር ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ነው ሚሰጠው አብደላህ ብኑ አባስ ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለት ስለገለፁ ።

በዘካተል ፊጥር ስለመወከል

* ዘካተል ፊጥር የሚሰጥበት ወቅት የተገደበና ግዜውም አጭር ከመሆኑ አንፃር አውጪዎች ባሉበት ሀገር ወይም ሁኔታ ምክንያት በተወሰነለት ግዜ ማውጣት ካልቻሉ ወቅቱ ሳያልቅ ዘካውን ሚያወጣላቸው ሰው መወከል ይችላሉ ። በተመሳሳይ ዘካተል ፊጥርን የሚቀበሉ ምስኪኖችም ራሳቸው መቀበል ካልቻሉ ሚቀበልላቸውን ሰው መወከል ይችላሉ ።

* ተወካዪች ከሁለቱም ከሰጪና ከተቀባይ ወገን ከተወከሉ ወቅቱ ካለፈም በኋለ ለምስኪኖች ቢሰጡ ችግር የለውም ነገር ግን የተወከሉ በሰጪዎች ብቻ ከሆነ የግድ ወቅት ሳያልፍ ለሚገባቸው ሰዎች ማድረስ ይኖርባቸዋል ።

ለሌላ አካባቢ ስለመስጠት

* አግባቡ ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ ከመላክ
እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ማውጣቱ ቢሆንም የሚቀበል ሚስኪን ከሌለ ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይቻላል ።
1.4K views01:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:01:56 ዛሬ ለይሉ ነው


ለይለተል ቀድር ይበልጥ የሚገመተው ጊዜ 27ተኛዋ ለሊት ላይ ነው። 27ተኛዋ ለሊት ለይለተል ቀድር የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው ለዚህም የሀዲስ ማስረጃዎች አሉ። (ፈታዋ አል-ላጅናህ አል-ዳኢማህ ሊኢል-ቡሑት አል-ኢልሚያህ ወአል-ኢፍታ፣ 10/413)

ይህ ማለት ግን ከነጭራሹ በሌሎች ለሊቶች አትሆንም ማለት አይደለም።


ዛሬ ለሊቱን በዚክር፣ በዱዓእ፣ በኢስቲግፋር፣ በቁርኣን፣ በለይል ሶላት፣ በነቢያችን ላይ ሶላዋት በማውረድ… እንበራታ፡፡ አላህ ለይለቱል ቀድርን ይወፍቀን


ለይለተል ቀድር በኢባዳ ፈልገው እንጂ በረንዳ ላይ በመሆን ሰማይ ላይ የሚንቀሳቀስና የሚበር ነገር በመፈለግ አታባክነው። ትልቅ ሞኝነት ነው

አንዳንዶች ኮከብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲወረወር ሲያዩ ለይለተል ቀድር አየነው በማለት ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ቤታቸው የሚገቡም አሉ


ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ

ቴሌግራም t.me/khalidzemen


1.2K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 22:39:56
ቅጥ ያጣዉ የወንጌላዉያን ሰበካ!
781 views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:27:01
956 views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:35:17
ዝንብ ለማንሳት ዱላ ማንሳት እቃ ያሰብራል!

«ዳእዋ ላይ መረጋጋት በጣም ያስፈልጋል። አንድን መጥፎ ተግባር ያየ ሰዉ፤ ያንን ስህተት ለማስወገድ የሚያደርገዉ የሚወራጨዉና አደብ ማጣቱ የበለጠ ሌላ መጥፎ ነገር ያመጣል። ዝንብ ለማንሳት እሽሽ ብትላት ትሄዳለች። ነገር ግን ዱላ ካነሳህ ዝንቧም ታመልጥሀለች እቃም ታሰብርህና ትፀፀታለህ። ስለዚህ ከመቸኮል የምናገኘዉ ጥቅም የለም። ከመረጋጋት ግን ብዙ ጥቅም እናገኛለን።»

ሼይኽ መሀመድ ሀሚዲን
1.2K views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 10:06:03
1.1K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 12:47:32
645 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 17:18:18
362 views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ