2023-03-08 17:49:38
ዛሬ March የሴቶች ቀን ነው አሉ የሴቶች ነፃነት በሚል ሰበብ፣ ግርማ ሞገስ ያለውን አለባበሷን ማስጣል እና በቤት እመቤትነቷና በባሏ ላይ እንድትሸፍት ማድረግ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡
ብቻ አላማቸው የሴቶችን መብት ማክበር እንዳልሆነ ከሙስሊም ሴቶች አንፃር ያላቸው ፖሊሲ በተጨባጭ አይን ላለው ሁሉ እያሳየ ነው፡፡
እርቃንነትን እስከ ጥግ እየፈቀዱ ሙስሊሟን ግን አለባበሷን ምክኒያት በማድረግ፣ ከትምህርት ገበታ፣ ከስራ ቦታ ማፈናቀሉን ተያይዘውታል፡፡
እነዚህ ናቸው እንግዲህ ስለ ሴቶች መብት የሚያቀነቅኑት፡፡ ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ አለባበሶች ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ለሙስሊሟ ሲሆን ግን በየመንገዱ ይጎነትላሉ፡፡
አልፈውም ህገ-ደንብ ያወጣሉ፡፡ ፖሊሲ ያረቃሉ፡፡ ከዚያም አያፍሩም ስለ ሴቶች መብት ይደሰኩራሉ፡፡ “የምትለብሺውን እኔ ካልመረጥኩልሽ” ከማለት በላይ ምን አፈና አለ?!!
እህቴ ሆይ! ተጠንቀቂ!! ብዙዎቹ የሴቶች “ነፃ አውጪዎች” የሰይጣን ተልእኮ አራማጅ የሆኑ የሀሰት ጥሩ ንባዎች ናቸው፡፡ እውነት ተቆርቁሮልሽ እንዳይመስልሽ፡፡
ቢሆንማ ለእርቃን እሩብ ጉዳይ መሆንን ፈቅዶ መልበስሽን ለምን ይቃወምሻል እውነት ለመብትሽ ተሟጋች ከሆነ ስትራቆቺ ገልፍጦ ስትለብሺ ለምን ደሙ ይፈላል
ለምንስ በየመንገዱ ይጎነትላል ለምንስ ከየተቋሙ ያባርራል እመኚኝ “ነፃ ውጪ” የሚለው በየጎዳናው በነፃነት በነፃ ወይም በርካሽ እንዲያገኚሽ ነው፡፡
ለሰው ልጆች አጥፊና አውዳሚ ከሚባሉት ሁለት ፈተናዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የስሜትን ፈተናን በሂጃብ ልጎም እንዳታስሪው እስልምና ያስተምርሽል፣ ከዚህ ፈተና መጠበቁ ዋነኛ ተጠቃሚውም ተጎጂዋም አንቺ ነሽ
አስተውይ! ልብስሽን ስለጣልሽ ነፃ አትወጭም፡፡ ነፃ መሆን ልብስ በመጣል ከሆነ ነፃ ሰዎች ማለት እብ - ዶች ናቸው፡፡ የሚጮኸው ስለ ክቡር ማንነትሽ ሳይሆን ስለ እርቃን ገላሽ ነው፡፡
ሸሪዐውን የተከተለ ኢስላማዊ አለባበስ የአማኝ ሴት መገለጫ የንጽህናሽ ማስታወቂያ ነው። እንዳትደፈሪና ክብርሽ እንዳይነካ መከላከያሽ ነው።
ሂጃብ በመልበስሽ ወንዶች እንቺን አይተው ከመፈተን ይጠበቃሉ፡፡ ኧረ እንዲያውም አይናቸውን ሰበር ለሚያደርጉ ብርቅዮዎች ብቻ ሳይሆን ላይ ታቹን ለሚያማትሩትም አደብ ታስገጂበታለሽ
በተቃራኒው የምትገላለጪ ከሆነ የፈተና የጥፋት በር በማይዘጋ መልኩ ይበረገዳል፡፡ በዘመናችን ያለውን ሁኔታ ያስተዋለ አላህ ያዘነላት ካልሆነች በስተቀር ሴት ልጅ በገዛ እራሷ ክብሯን አሽቀንጥራ ወርውራዋለች፡፡
አይንሽ፣ ከንፈርሽ፣ ዳሌሽ ብለው በማማለል የማይረግብ ስሜታቸው ማርኪያ ሎሌ ያደርጉሻል፡፡ አንቺም ፊቴ አምሮ ቅርፄ ተስተካክሎ ይሆን እያልሽ የነሱ የወሲብ ማርኪያ ትሆያለሽ
መገላለጥ አንዱ የቂያማ መድረስ ምልክት ነው፣ ሰዉነታቸዉን አግባብ ባለዉ ልብስ ያልሸፈኑ ሴቶች በስፋት መታየት። ከፊል ገላቸውን ይሸፍናሉ። የሰውነታቸው ቅርፅ ለይቶ የሚያሳይ ጥብቅብቅ አልባሳትን ይለብሳሉ።
የነቁበት ነቅተውበት እየተመለሱ ነው፡፡ ይሄውና በምዕራቡ አለም ከሚሰልሙት ውስጥ 80% ሴቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች የምዕራቡን “ነፃነት” ሸሽተው ወደ ኢስላም “ጭቆና” ይጎርፉ ይዘዋል፡፡
በጊዜ ንቂ፡፡ ብልጥ ማለት በሌሎች ላይ ከደረሰው ቀድሞ የሚማር ነው፡፡ ምሳሌሽን በትክክል ምረጪ፡፡ በአኢሻ ስብእና እያፈርሽ አሊሻን መሆን ካማረሽ
ንቂ! ሙስሊም ወንድምሽ ስለበደለሽ በኢስላም ላይ ብታምጪ ኢስላምን ቅንጣት ታክል አትጎጂውም፡፡ ብቻ በዱንያም ላታተርፊ ሁለቱንም አገር የከሰርሽ ከሁለት ያጣሽ ትሆኛለሽ፡፡
እራስሽን ሁኚ፡፡ የገደል ማሚቶ አትሁኚ፡፡ ሌሎች ስለሳሉ አትሳይ ስላነጠሱም አታነጥሺ፡፡ የተፈጠርሺው ለክቡር አላማ ነው፡፡
ተጠንቀቂ!! ከሸሪዐው አጥር ውጭ ያለ የመብት ጥያቄ አትጠይቂ፡፡ የፈጠረሽ ጌታ አንቺ እራስሽን ከምታውቂው በላይ ያውቅሻል፡፡ ላንቺም ከተኩላው “እንባ ጠባቂ” ቀርቶ ከራስሽም በላይ ያዝንልሻል፡፡
ደግሞም አትዘንጊ፡፡ ህይወት ማለት የአኺራ ህይወት ነው፡፡ አላህ አድሎሽ ሰማንያ ዘጠና አመት ብትኖሪ እንኳ በጊዜ ከኢስላም ባቡር ውስጥ ካልተሳፈርሽ ሲመሽ ይቆጭሻል፡፡
ምን ብትኖሪ ህይወትሽ መጨረሻ አለው፣ ሞት፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ዘላለማዊ ህይወት፡፡ የዛሬው ተቆርቋሪ ለዚያ ቀርቶ ለዱንያ እንኳ ጤነኛ ህልም የለውም፡፡
ለአኺራማ እንኳን ላንቺ ለራሱም አይሆንም፡፡ ጆሮሽን ሰጥተሽ?! ቦታ ከሰጠሽውማ የአለም እዝነት የሆኑትን ነብይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጠላትሽ እንደሆኑ ቀስ እያለ እያዋዛ ያሰርፅብሻል፡፡
በጊዜ ካልነቃሽ መውጣት ከማትችይበት ውስጥ ይነክርሻል፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ስለቀረበ እንዳያታልልሽ፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡
ግን እስቲ እኔ ልጠይቅሽ እውነት ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላንቺ ስለማይቆረቆሩ ነው ከ1400 አመት በፊት ሶሐቦቻቸው በተሰበሰቡበት ታላቅ ቀንና ታላቅ ቦታ ላይ “የሴቶችን ነገር አደራ” እያሉ አዋጅ ያሰሙት
እርግጥ ነው ብዙ በደል አለብሽ/አለብን፡፡ ግን አስተውይ ከበደሎቹ ሁሉ የከፋው ዘላለማዊ ክብር የሚያጎናፅፍሽን ኢስላምሽን እንዳታውቂ መደረግሽ ነው፡፡
እናም እልሻለሁ በMarch 8 ሳይሆን ከኢስላም መብትሽን ፈልጊ፡፡ ለወዳኛው ህይወትሽም ትጊ፡፡
የአላህ ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡
ሼር በማድረግ ለእህቶች እንዲደርሳቸው ያድርጉ አላህ ሆይ፣ ቅኖችና ለሌሎችም መቀናት ምክንያት የሚሆኑ ሰዎች አድርገን
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:- “ወደ ቅን መንገድ የተጣራ ሰው፣ የተከተሉት ሰዎች ሁሉ የሚያገኙት አጅር ምንም ሳይጎድልባቸው ለሱም ይኖረዋል…" (ቡኻሪና ሙስሊም)
ቴሌግራም t.me/khalidzemen
463 views14:49