2023-03-16 15:42:45
ከ ድግምት፣ ከክፉ ዐይን(ምቀኝነት) ለመጠበቅ የሚወሰዱ ቅድመ ጥንቃቄዎች!
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው!
1) ሙአዊዛትን(ሱረቱል ኢኽላስ፣ ፈለቅ፣ እና ናስ ምእራፎችን) ደጋግሞ ማንበብ!
ሰኢድ አል ኸድሪያ(ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከጅንና ከአይነ-ናስ መጠበቂያን ይጠቀሙ ነበር። እነኚህ ምዕራፎች በወረዱላቸው ጊዜ ግን የተቀሩትን(መጠቀምን) ትተዋል። ሲሉ አስተላልፈዋል። [ኢብኑ ማጃህ ዘግበውት አልባኒ ሰሂህ ብለውታል]
2) በረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተነገሩን የዘውትር ዱአዎችን መጠቀም።
ማለትም የጠዋት፣ የማታ፣ የመኝታ፣ ከሰላት ቡኃላ እንዲሁም ሌሎችን ዱአዎች የሚባሉትን ያለማቋረጥ ማድረግ!
3) ለማድረግ ያሰብነው ነገር በይፋ ሳንገልፅ በፊት ጉዳያችንን መፈፀም!
ምክንያቱም አይነ-ናስና ምቀኝነት መነሻው አድናቆት ነውና። ለዚህም ነው ለሙአዝ ኢቢኑ ጀበል(ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸውን አውስተዋል፦
"ማድረግ የምትሹትን እስክታከናውኑ ድረስ፤ ባለመናገር በዝምታ ታገዙ! ለባለፀጋ ሁሉ ተቀናቃኝ(ምቀኛ) አለበትና።" [በይሀቂ ዘግበውታል]
4) የሚያምር ነገር ስናይ ተበሩክ(መባረክን መፀለይ) ማድረግ!
አንድ አማኝ በወንድሙ(በእህቷ) ላይ የሚያስደምም ነገር ሲመለከት "ማሻአላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ፣ ማሻአላህ"(አላህ ያሻው ተፈፀመ። በአላህ እንጂ ሀይል የለም! እና መሰል ዱአዎችን ልንል ይገባል።
መልካም ነገር አይቶ ይህንን ዱአ ያለ ጉዳት አይደርስበትም!
አነስ(ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸውን አውስተዋል፦ "አንዳች የሚያስደምመውን(የማረከውን) ነገር ባየ ጊዜ እንዲህ ያለ አንዳችም አይጎዳውም። *ማሻ አላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ ለም የዲሩ*(አላህ የሻው ተፈፃሚ ሆነ፣ በአላህ እንጂ ሃይል የለም።) [ኢብኑ ስሪን ዘግበውታል]
5) ተውሂዳችን ማጥራትና ማስተካከል!
አላህን የሚፈራ ሰው አላህ መመኪያ መጠበቂያ መሸሻ ይሆነዋል። አላህን የሚፈራ፤ ለእርሱ መውጫ ያበጅለታል።
ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ፡- “አንድ ወቅት ከነቢዩ ጋር ነበርኩኝ እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ:- ልጄ ሆይ! ጥቂት ቃላትን አስተምርሀለሁ! አላህን አስታውስ እርሱ ይጠብቅሀል፤ አላህን አስታውስ ቅርብህ ሆኖ ታገኘዋለህ፤ መጠየቅህ የፈለግክ ጊዜ አላህን ብቻ ጠይቅ፤ እርዳታን ስትሻ ከአላህ ብቻ እርዳታን ፈልግ፤ ጠንቅቀህ እመን፣ አላህ ይጠቅምህ ዘንድ የወሰነው እንጂ ፍጥረታት ሁሉ ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አይጠቅሙህ፤ እንዲሁም ፍጥረታት ሁሉ ሊጎዱህ ቢሰባሰቡ በአንዳች አይጎዱህም በእርግጥ አላህ ሊጎዱህ ቢወስነው እንጂ።” (አል-ቲርሚዚ ሀዲስ ቁጥር 2442)
6) ተውበት(ንሰሀ) በማድረግ ወደ አላህ መመለስ!
ከጥፋት ታቅበን ንሰሀ(ተውበት) ማድረግ፤ ከብዙ አስከፊ ነገሮች እንደሚያስጥለን እሙን ነው። እንዲሁም ከእንደዚህ ያለ በሽታ ይገላግለናል።
وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ [ሱረቱል ሹራ 30]
የአላህ ፍቃድ ከሆነ በሚቀጥለው ክፍል በሰው አይን የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው አንዳንድ ምልክቶችን እናያለን!
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋና ጠቃሚ መረጃ በዚህ ይከታተሉን!
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
https://t.me/islamictrueth
በፌስቡክ ለመከታተል
Www.fb.com/islamictrueth
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
625 views12:42