Get Mystery Box with random crypto!

⛤Islamic Direction⛤

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_direction — ⛤Islamic Direction⛤ I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_direction — ⛤Islamic Direction⛤
የሰርጥ አድራሻ: @islamic_direction
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.14K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ አላህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ ;"እኔ ከሙስሊም ነኝ" ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
(ቁ_41:33)
☑ ኢንሻ አላህ ይሄ ቻናል
#ሀዲሶች
#ቂሳዎች
#ቁርአናዊ ምክሮች
#ግጥሞች
የምናካፍልበት ይሆናል
➡ አላህ ያወቅነውን የምናሳውቅ ባወቅነውም ሰርተን የምንጠቀም ያድርገን አሚን!!

"For any Comment
@nepiikaa

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-08 18:01:02 ጀነትና ፀጋዋ
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

ውድ ወንድሜ…

  የጀነት ፀጋዎች በቃላት የማይገለፁና በሀሳብ የማይደረሱ ናቸው። የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች ነብዩን ሰለጀነት ሁኔታ እንዲነግሯቸው ጠየቋቸው።  ነብዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም) እንዲህ አሉ፦ ጠጠሮቹ ሉልና ያቁት ናቸው። አፈሩም ዛእፈራን ነው። የገቧት ይጠቃቀማሉ ፀጋ አይከዳቸውም፣ ልብሶቻቸው አያልቁም፣ ወጣትነታቸው አይከዳቸውም፣ በርሷም ዘውታሪ የማይሞቱ ሲሆኑ ሞት በነርሱ ላይ እርም ነች።

ህንፃዎቿና መኖሪያዎቿ ፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

ለአማኞች ምቹ የሆኑ ውብ መኖሪያዎች አሏት። አላህ እንዲህ ብሏል፦
لَـٰكِنِ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ لَهُمْ غُرَفٌ مِّن فَوْقِهَا غُرَفٌ مَّبْنِيَّةٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۖ وَعْدَ اللَّهِ ۖ لَا يُخْلِفُ اللَّهُ الْمِيعَادَ

( አል-ዙመር - 20)

ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለእነርሱ ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የኾኑ አልሏቸው፡፡ (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፡፡ አላህ ቃሉን አያፈርስም፡፡

ኢብኑ ከሲር (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ብሏል፦
【ልዕልናው የላቀውና ክብሩ የገነነው አላህ ደሰታን የተጎናፀፉት ሰዎች ጀነት ውስጥ ሰገነቶች እንዳላቸው ነግሮናል። እነዚህ ሰገነቶች እነርሱም አንዱ ከአንዱ የተነባበሩ ሲሆኑ በክእለትና በጥበብ የተገነቡ ህንፃዎች ናቸው።】

ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ግንባታውን ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል፦
لبنة من ذهب ولبنة من فضة ملاطها المسك الأذفر
《ግንባታቸው ከብርና ከወርቅ ሲሆን ቅባቸው ደግሞ ሚሰከል ኢዝፈር ነው።》

የጀነት ድንኳኖች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

አላህ ጀነት ውስጥ ድንኳኖች መኖራቸውን ተናግሯል።
حُورٌ مَّقْصُورَاتٌ فِي الْخِيَامِ
( ሱረቱ አል ረሕማን - 72)

በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡
ነብዩ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት
في الجنة خيمة من لؤلؤة مجوفة عرضها ستةن ميلا في كل زاوية منها إهل ما يرون الآ خرين يطوف عليهم المؤمن
«ጀነት ውስጥ ከሉል የተሰሩ ድንኳኖች አሉ የእያንዳንዱ ሰፋት 60 ማይል ሲሆን ከሰፋቱ የተነሳ በየማእዘኑ አማኞች የሚዘዋወሩባቸው የማይተያዩ ቤተሰቦች አሉ። »

የጀነት ዛፎች ፍራፍሬዎች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

አላህ ጀነት ውስጥ ብዙ ዓይነት ዛፎች እንዳሉ ነግሮናል ከነርሱ  የወይንና የሩማን ዛፍ እንዲሁም ዘንባባዎች ሲጠቀሱ ሌሎችም ቁርቁራ እና ሙዝ ዛፎች አሉ።

《ለጥንቁቆች መዳኛ ሰፍራ አላቸው አትክልቶችና ወይኖችም》

《የቀኝ ጓዶችም (ምንኛ የከበሩ) የቀኝ ጓዶች። በተቀፈቀፈ እሾህ በሌለው ቁርቁራ ውሰጥ ናቸው (ፍሬው) በተነባበረ ሙዝ ዛፍም።》

የጀነት እንሳትና አእዋፎቿ፦
•••✿❒ ❒✿•••

ጀነት ውስጥ አላህ ቢሆን እንጂ የማያውቃቸው እንሰሶችና አእዋፎች አሉ የጀነት ሰዎች ሰለሚያገኙት ፀጋ ሲገልፅ

አላህ እንዲህ ብሏል፦
《ከሚሹት በኾነ የበራሪ ሥጋ(ይዞሩባቸዋል)።》

ኢማም ሙስሊም ከኢብን መስኡድ ኢብን አንሳሪ እንደዘገቡት አንድ ሰው ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም) ዘንድ ልጓም ያላትን ግመል ይዞ መጣና ይህችን በአላህ መንገድ ላይ ትውል ዘንድ ጀብቻለሁ አለ። ነብዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም)
  «ሰባት መቶ የተለጎሙ ግመሎችን ተመነዳበታለህ» አሉት።

የጀነት ወንዞችና ጀረቶች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

ጀነት በሥሮቿ ወንዞች እንደሚፈሱ አላህ እንዲህ ሲል ነግሮናል፦

وَبَشِّرِ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ٌۖ
( አል-በቀራህ - 25)
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡

إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ
(ሱረቱ አል-ሒጅር - 45)
«እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡

የጀነት ነዋሪዎች አልባሳት፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••
የጀነት ነዋሪዎች እጅግ ማራኪና ውብ የሆኑ ልብሶችን ይለብሳሉ። በወርቅ፣ ብርና ሉል ይጋጌጣሉ። ልብሳቸውም ከሐር ነው።

يُحَلَّوْنَ فِيهَا مِنْ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٍ وَلُؤْلُؤًا ۖ وَلِبَاسُهُمْ فِيهَا حَرِيرٌ
( ሱረቱ አል-ሐጅ - 23)
በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ልብሶቻቸውም ሐር ናቸው፡፡

ምንጣፎቻቸውና አልጋዎቻቸው፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

የጀነት ሰገነቶች ፣በመናፈሻዎቿ ውስጥ ያሉ መቀመጫዎችና የአትክልት ሰፍራዎቿ ውብ በሆኑ ቀለሞች ባሸበረቁ ምንጣፎች የተነጠፉ ናቸው።

《በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አሉ። በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም። የተደረደሩ መከዳዎችም። የተነጠፉ ሰጋጃዎችም አሉ።》
( ሱረቱ ጋሺያ 13_16)

የጀነት ነዋሪዎች አገልጋዮች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••
የጀነት ነዋሪዎችን ያገለግሉ ዘንድ አላህ እጅግ መልከ መልካም የሆኑ ወጣቶች ልጆችን ፈጥሯል። በቁርአኑ ውስጥ አላህ እንዲህ ይላል።

《በነሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ። ከጠጂ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩሰኩሰቶ በፁዋም በነሱ ላይ ይዞራሉ።》

ይሁንና አላህ ሰለጀነት ፀጋዎች ያልገለፀልን እጅግ በጣም ብዙና አእምሮአችን ሊረዳው የማችልም፣ ጀሮዎች ያልሰሟቸውና በማንም አዕምሮ ውል ያላሉ ናቸው። ቡኻሪና ሙሰሊም እንደዘገቡት ነብዩ (ሰላለሁ ዐለይሂ ወስለም) አላህ እንዲህ ማለቱን ነግረውናል፦

《ለደጋጎች ባሮቼ ዓይባቸው ያላዩት፣ ጀሮዎች ያልሰሙትና በማንም ሰው አዕምሮ ውል ያላሉ ፀጋዎችን አዘጋጅቻለሁ》

فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
( ሱረቱ አል-ሰጅዳህ፣ - 17)
ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡

ሰለዚህ መንገደኛው ወንድሜ ወደዚህች ጀነት ለመግባት የሚያሰችልህን ካርድ ለማገኘት ወደ ቀጣዩ ፌርማታ አብረህን ግባ።

┄┄┉┉✽‌»‌ »‌✽‌┉┉┄┄
#ከምድራዊው_ዓለም_ወደ_መጨረሻው_ዓለም
አላህ ቀጥ ባለው በነብያት ጥሪ በተውሂድ ፀንተው ጀነትን ግቧት ከሚባሉት ያድርገን ያረብ

husnel_khuluk
420 viewsابن جمال, 15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:56:37 *በቀደር የማመን መሰረቶች*
*4ናቸው እነሱም:-*

1/ሁሉንም ነገር ከመሆኑ /ከመከሰቱ በፊት አላህ ያውቀዋል ብሎ ማመን፣

2/ማንኛውንም የሚሆን ነገር በሙሉ አላህ ፅፎታል ብሎ ማመን፣

3/ማንኛውም ነገር የሚከሰተው በሰማይም ይሁን በምድር ላይ አላህ ፈቅዶት እንጂ አይሆንም ብሎ ማመንና

4/የሆኑና የሚሆኑ/የሚከሰቱ ነገሮችን በሙሉ አላህ ነው ያደረገውና የሚያደርገው ብሎ ማመን ናቸው።

ማንኛውም ሰው ይህን
የማወቅና የመቀበል ግዴታ አለበት።

ከዛዱል መዓድ የትምህርት መድረክ
ከዐቂደቱል ዋሲጢያህ ማብራሪያ የተወሰደ




@Islamic_direction
695 viewsNizal Ümu ªň€s, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:22:54
470 viewsNizal Ümu ªň€s, 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 07:32:58 ።።።የጧት ስንቅ ......


በሕይወትህ  ለሚሆነው  ነገር  አትዘን።

የተፈጠርነውም  ለመሞከር  ነው።
አላህ የምንታገስና የማንታገስ መሆናችንን ለመለየት በዚህ ላይ እንድናልፍ አድርጎናል።

ነገሮችን አታካብድ።   የደስታ  ደመና  ቅርብ  በመሆኑ  እንደሚዘንብ    እርግጠኛ ሁን
#ዶ/ኢብራሒም_አልፈቂ



➵ ሰዎች በጩኽት ያልሰሙህን
☞ አላህ በዝምታህ ይሰማሀል ይረዳሀል
ምክንያቱም ልብህ ካንተ ይልቅ
ለሱ ቅርብ ናትና።
➵ ከሰዎች ዘንድ ፈልገህ ያጣኸውን
☞ ከአላህ ዘንድ ሳትፈልግ ታገኘዋለህ
ምክንያቱም አላህ ከምትፈልገው
ይልቅ የሚያስፈልግህን ያውቃልና።

"ደካማ ሰው ማለት ለስሜታዊ ዝንባሌ ተገዢ የሆነ (አንዳች የማይፈይድ ነገር ሳይሰራ) መልካምን ነገር የሚመኝና ከአላህ የሚጠብቅ ነው"
[Tirmizy]

:በጥረት  መልካም  ነገር  ሲሳካልህ  በአንተ  ጥረት  ሳይሆን  በአላህ እርዳታ  መሆኑን  አውቀህ   አመስግን።
ማንም ሰው በራሱ  አቅም ጭንቅላቱን ተሸክሞ  የሚሄድ የለም

   መልካም ውሎ


  husnul_khuluk
575 viewsابن جمال, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 23:21:25 አንቺ የምትሸጪ በግ አይደለሽም ፎቶሽን እዛም እዚህም አትለጥፊ
#ገዢ_እንዳጣ_በግ!! አዎ አንቺን ነዉ የተከበረዉ ጌታሽ በቁጥብነት በሀያዕ  አዞሻል እንደታዘዝሽዉ ቀጥ በይ።
#አንተንም_ይመለከታል_አኺ።

@Ethio_Suna_Media
@Ethio_Suna_Media
516 viewsAbu Umar Ibnu Sadik, 20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 23:21:13

ትወደኝ የለ...?
እያረገፈኝ
የዱንያ ማ'ቱ፣
እየቀጠፈኝ
ያለስስቱ፣
እየመነመንኩ
አቅም ሲርቀኝ፣
ግራውን ፍቀህ
ቅረበኝ በቀኝ።

ያረብ...!


@Islamic_direction
554 viewsNizal Ümu ªň€s, 20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 23:20:43
የተመኘሽው ባይሳካ ጭንቅ ጥብብ ካለሽ
የልብሽን ጭንቀት ሰብስቢና ወደ አላህ ውሰጂው
ወደሱ ብቻ ሂጂ ነጃን ታገኛለሽ
አትዘኚ አትፍሪም
የከበደሽ ነገር አላህ ጋር ቀላል ነው
ገዝፎ የታየሽ አላህ ጋር ትንሽ ነው
የማይቻል የመሰለሽ አላህ ጋር ገር ነው
ብቺ አንቺ በሩ ጋር ጠጋ በይ
በልብሽ ወደ ጌታሽ ተጓዢ
አንተ ለኔ የፈቀድከውም ያለፈቀድከውም ኸይር ነው ሁሌም አንተ ከራሴ በላይ መልካምን የምታስብልኝ ነህ እናም ወዳንተ እመጣለሁ በይው በርግጥም ያበረታሻል

{وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهْدِينِ}
"አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»"
                     [ሱረቱል ሷፋት:99]

@Islamic_direction
578 viewsNizal Ümu ªň€s, 20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 23:20:43 #ላስታውስሽ

ተስፋሽ ምን ያህል ለመበጠስ ለመቀደድ ቅርብ ነው?...ምን ያህል ጉዳት ያኮላሸዋል?...ምን ያህልስ የመንገድሽ መቃናት እያጠነከረው ይሄዳል?...ብየ ስልሽ አንዳች ፍርሀት ከልቤ ላይ ይርከፈከፋል...ምናልባትም ተስፋሽ ስስ እንዳይሆን እሰጋለሁ...ከነበርሽበት የአለሁ ስሜት ወደ የለሁም የምትቀርቢበት ሁናቴ ያስፈራኛል...የምትወጂው ስለገፋሽ፣ የኔ ያልሻት ጥላሽ ብን ስላለች ፣ ምርር ብለሽ እያለቀስሽ ካንቺ ውጭ አባባይ ሳይኖርሽ ፣ በጠና ታመሽ አስታማሚ ስታጪ ፣ አምላክሽን ጠይቀሽው ምላሹ እንደዘገየ ሲሰማሽ ( እንደማይዘገይ የታወቀ ቢሆንም እንደ ሰው የሚሰማን) ፣ መንገድሽ ሁሉ ሲቆላለፍ ፣ መከራ ሀያእ ሳያደርግ ሲከመርብሽና ብዙ ብዙ መሰል ፈተናወች ሲበዙብሽ ተስፋሽን ትኳረፊ እንደሁ አደራሽን እልሻለሁ...ተስፋሽን አትደምስሺ ፣ አታፍርሺ ፣ ከል አታልብሺ...በተቧጠጥሽ ቁጥር የሚፋፋ ተስፋ ይኑርሽ...በተጎዳሽ ቁጥር እሰይ ለተስፋየ አቀረቡኝ ማለትን ልመጂ......ለተስፋሽ አደራ በተስፋሽ ውስጥ ተስፋቸው መኖሩን አትርሺ...ላስታውስሽ ነባዋ!

@Islamic_direction
559 viewsNizal Ümu ªň€s, 20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 21:16:01
የዚና ጣዕም 5 ደቂቃ አይቆይም  ፀፀቱና የወንጀል ጠባሳው ግን በብዙ አመትም አይሽርም።
በዱኒያ በአኼራ ከመዋረድ #ሀላልን ተዳፍሮ ዱኒያ አኼራን ማሳመር።

@Ethio_Suna_Media
@Ethio_Suna_Media
562 viewsAbu Umar Ibnu Sadik, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 07:03:41 ነገሩ እንደሚሳካ ካመንክ እድሎችን ትመለከታለህ
ነገሩ እንደማይሳካ ካመንክ ብዙ መሰናክሎችን ትመለከታለህ!

@Ethio_Suna_Media
@Ethio_Suna_Media
643 viewsAbu Umar Ibnu Sadik, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ