Get Mystery Box with random crypto!

⛤Islamic Direction⛤

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_direction — ⛤Islamic Direction⛤ I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_direction — ⛤Islamic Direction⛤
የሰርጥ አድራሻ: @islamic_direction
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.14K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ አላህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ ;"እኔ ከሙስሊም ነኝ" ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
(ቁ_41:33)
☑ ኢንሻ አላህ ይሄ ቻናል
#ሀዲሶች
#ቂሳዎች
#ቁርአናዊ ምክሮች
#ግጥሞች
የምናካፍልበት ይሆናል
➡ አላህ ያወቅነውን የምናሳውቅ ባወቅነውም ሰርተን የምንጠቀም ያድርገን አሚን!!

"For any Comment
@nepiikaa

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-09 10:37:25
ቁርአን ለሁሉ ነገር መድሃኒት ነው
በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብትሆን ቁርአንን አስታውስ ጓደኛህም አድርገህ ያዘዉ የሁለቱም አለም መዳኛህ ነዉና"!


إِنَّ هَٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ وَيُبَشِّرُ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا كَبِيرًا

ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል፡፡

ልቤን በቁርኣን ፍቅር ሙላልኝ የዓለማቱ አምላክ አላህዬ

@Islamic_direction
380 viewsNizal Ümu ªň€s, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 10:37:01 رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

«ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱም አገር ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን»

@Islamic_direction
315 viewsNizal Ümu ªň€s, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 10:36:36 القارئ: حمزة بوديب
دعاء بخشوع

@Islamic_direction
281 viewsNizal Ümu ªň€s, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 10:20:28 አንዳንድ ጊዜ የዱዓችን ተቀባይነት በተግባር የሚረጋገጠው ለኛ ይጠቅመናል ብለን ያሰብነውንና በጣም የምንፈልገውን ነገር ስናጣ፣ ለኛ ይጎዳናል ብለን ያሰብነውንና እንዳያገኘን የፈራነውን የማንፈልገውን ነገር ስናገኝ ሊሆን ይችላል።


አላህ ጥበበኛና ለባሮቹ እጅግ በጣም አዛኝ ስለሆነ ከኛ በላይ ለኛ የሚጠቅመንና እኛን የሚጎዳንን ያውቃል። ስለሆነም የሆነ በጣም የፈለግነውንና የጓጓንለትን ነገር ስናጣ ከበሳጨት ይልቅ የአላህን ውሳኔ ወደን እንቀበል። «በቃ! ለበጎ ነው። ለኔ ባይለው ነው። የማይጠቅመኝ መሆኑን አላህ አውቆ ነው!» ብለን እንለፈው።

በተቃራኒው የማንፈልገውን ነገር ስናገኝ ደግሞ «ይሄም ለበጎ ነው። ምንም እንኳ እኔን ባይመስለኝም አላህ ጠቃሚዬ መሆኑን አውቆ ነው!» የሚሉ ምክንያቶችን ወደ ውስጣችን እናምጣ። ይህንን የምንለው ራሳችንን ለማጽናናት ሳይሆን ሐቂቃ የእውነትም ስለሆነ ነው። ለወዳው ባይመስለንም የዚያን ነገር እውነታ ከሆነ ጊዜ በኋላ በተጨባጭ እንረዳዋለን።


አላህ እንዲህ ብሎናል፦


(…وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ)

«…አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡»

[አል-በቀረህ: 216/٢١٦]


(… فَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَيَجْعَلَ اللَّهُ فِيهِ خَيْرًا كَثِيرًا)

«… አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡»
[አ-ን'ኒሳእ: 19/١٩]


አላህ ለሚወደው ተግባርና ንግግር ይወፍቀን።

@Islamic_direction
297 viewsNizal Ümu ªň€s, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 10:19:40
274 viewsNizal Ümu ªň€s, 07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 10:17:31 ትወደኝ የለ ....!
ጢኖ ኑረቴን
ግዝፈት ለግሳት፣
ብናኝ ሀያቴን
በመክበድ ካሳት ፣
ድኩሟ ቀልቤን
የትም ስትወድቅ
በሂክማህ አንሳት፣
ከጎኔ ተገኝ ሁሉ ሲገርፈኝ
በመሸሽ እሳት።

@Islamic_direction
274 viewsNizal Ümu ªň€s, 07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 07:26:05
       የማለዳ ስንቅ

    የአላህ  ፍቅር የእኛ ደስታ እና መታሰቢያ መተማመኛ  ነው።

   በህይወት ዘመንህ  ውስጥ በእድሜ ክልል እየበዛ ስሄድ ሁኔታዎች ሲቀያየሩ  በኢማን ላይ ኢማን በተስፋ  ላይ ተስፋ እየጨመረ የሚመራ ልብ
የአላህ ፍቅር ያደረበት
ልብ  ነው።
_ __

①አላህን ጠንቅቆ ያወቀ ልብ ነው ።

②የጀሊሉን ቃል ኪዳኖች ያወቀ
ልብ ነው ።

③ስልጣን ክብሩን የተረዳ ልብ ነው።

④ ራህመት እና እዝነቱን የተገነዘበ
ልብ ነው ።
   
   ሁሉም ነገር ደህና ይሆናል ያለ
ነገ ብርሀን እንዳለ የሚያውቀው ።

 

   °• እናም በእያንዳንዱ ቀን
ላይ  ወደ ተውባ ወደ ተስፋ የሚጠራኝ

  አላህዬ  የሚንከባከበኝ
የሚመግበኝ አላህ  ሆይ,እያለኝ
ከሀዘን በኋላ  ደስታ  ከድካም
በኋላ እረፍት እንዳለ ቃል የገባልኝ
አምላክ እያለኝ ተስፋ ለምን ልቁረጥ
  ……………… ለምን ተስፋ
ልቁረጥ 


ራሀቱል ቀልብ  ልባችንን እናረጋገው ሚያበላን የሚያጠጣንም የሚያኖረንም የሚገለንም አላህ ነው

አልሀምዱሊላህ ትልቁን ስጦታ ኢስላም ሰቶናል አልሀምዱሊላህ ።


አልሀምዱሊላህ

husnul_khuluk
345 viewsابن جمال, 04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 22:53:40
لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ

የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡

قَالُوا لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ عَلِيمٍ

«አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን» አሉት፡፡

አልሀምዱሊላህ

@Islamic_direction
434 viewsNizal Ümu ªň€s, 19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 18:09:39
(وَالسَّابِقُونَ السَّابِقُونَ)
" (ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለጀነት)
ቀዳሚዎች ናቸው ። "
[አል ዋቂዓህ 10]

@Islamic_direction
505 viewsNizal Ümu ªň€s, 15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 18:04:58
ከጀነት ጓዳ


ሑር- የጀነት ውስጥ ምርጥ ሴቶች

አዕራፍ- በጀነትና በጀሀነም መካከል ያለ ተራራ

ፍርደውስ - የጀነት ላእላዩ ክፍል

ረያን- ጾመኞች ብቻ የሚጠሩባት የጀነት በር

ሐሪር - የጀነት ሰዎች ልብስ

ሚስክ - የጀነት ውስጥ ሽቶ

ትልቁ ፀጋ - በጀነት ውስጥ የአላህ ውዴታ

አል- ከውሠር - የጀነት ውስጥ ወንዝ

ድሆች - አብዛኞቹ የጀነት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች

አላህ ከጀነት ሰዎች ያድርገን!!!



اللهــم صــــل وسلــــم
علـــى نبينـــا محمــــدﷺ

@Islamic_direction
488 viewsNizal Ümu ªň€s, 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ