Get Mystery Box with random crypto!

የተመኘሽው ባይሳካ ጭንቅ ጥብብ ካለሽ የልብሽን ጭንቀት ሰብስቢና ወደ አላህ ውሰጂው ወደሱ ብቻ ሂ | ⛤Islamic Direction⛤

የተመኘሽው ባይሳካ ጭንቅ ጥብብ ካለሽ
የልብሽን ጭንቀት ሰብስቢና ወደ አላህ ውሰጂው
ወደሱ ብቻ ሂጂ ነጃን ታገኛለሽ
አትዘኚ አትፍሪም
የከበደሽ ነገር አላህ ጋር ቀላል ነው
ገዝፎ የታየሽ አላህ ጋር ትንሽ ነው
የማይቻል የመሰለሽ አላህ ጋር ገር ነው
ብቺ አንቺ በሩ ጋር ጠጋ በይ
በልብሽ ወደ ጌታሽ ተጓዢ
አንተ ለኔ የፈቀድከውም ያለፈቀድከውም ኸይር ነው ሁሌም አንተ ከራሴ በላይ መልካምን የምታስብልኝ ነህ እናም ወዳንተ እመጣለሁ በይው በርግጥም ያበረታሻል

{وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهْدِينِ}
"አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»"
                     [ሱረቱል ሷፋት:99]

@Islamic_direction