Get Mystery Box with random crypto!

#ላስታውስሽ ተስፋሽ ምን ያህል ለመበጠስ ለመቀደድ ቅርብ ነው?...ምን ያህል ጉዳት ያኮላሸዋል?. | ⛤Islamic Direction⛤

#ላስታውስሽ

ተስፋሽ ምን ያህል ለመበጠስ ለመቀደድ ቅርብ ነው?...ምን ያህል ጉዳት ያኮላሸዋል?...ምን ያህልስ የመንገድሽ መቃናት እያጠነከረው ይሄዳል?...ብየ ስልሽ አንዳች ፍርሀት ከልቤ ላይ ይርከፈከፋል...ምናልባትም ተስፋሽ ስስ እንዳይሆን እሰጋለሁ...ከነበርሽበት የአለሁ ስሜት ወደ የለሁም የምትቀርቢበት ሁናቴ ያስፈራኛል...የምትወጂው ስለገፋሽ፣ የኔ ያልሻት ጥላሽ ብን ስላለች ፣ ምርር ብለሽ እያለቀስሽ ካንቺ ውጭ አባባይ ሳይኖርሽ ፣ በጠና ታመሽ አስታማሚ ስታጪ ፣ አምላክሽን ጠይቀሽው ምላሹ እንደዘገየ ሲሰማሽ ( እንደማይዘገይ የታወቀ ቢሆንም እንደ ሰው የሚሰማን) ፣ መንገድሽ ሁሉ ሲቆላለፍ ፣ መከራ ሀያእ ሳያደርግ ሲከመርብሽና ብዙ ብዙ መሰል ፈተናወች ሲበዙብሽ ተስፋሽን ትኳረፊ እንደሁ አደራሽን እልሻለሁ...ተስፋሽን አትደምስሺ ፣ አታፍርሺ ፣ ከል አታልብሺ...በተቧጠጥሽ ቁጥር የሚፋፋ ተስፋ ይኑርሽ...በተጎዳሽ ቁጥር እሰይ ለተስፋየ አቀረቡኝ ማለትን ልመጂ......ለተስፋሽ አደራ በተስፋሽ ውስጥ ተስፋቸው መኖሩን አትርሺ...ላስታውስሽ ነባዋ!

@Islamic_direction