Get Mystery Box with random crypto!

።።።የጧት ስንቅ ...... በሕይወትህ  ለሚሆነው  ነገር  አትዘን። የተፈጠርነውም  ለመ | ⛤Islamic Direction⛤

።።።የጧት ስንቅ ......


በሕይወትህ  ለሚሆነው  ነገር  አትዘን።

የተፈጠርነውም  ለመሞከር  ነው።
አላህ የምንታገስና የማንታገስ መሆናችንን ለመለየት በዚህ ላይ እንድናልፍ አድርጎናል።

ነገሮችን አታካብድ።   የደስታ  ደመና  ቅርብ  በመሆኑ  እንደሚዘንብ    እርግጠኛ ሁን
#ዶ/ኢብራሒም_አልፈቂ



➵ ሰዎች በጩኽት ያልሰሙህን
☞ አላህ በዝምታህ ይሰማሀል ይረዳሀል
ምክንያቱም ልብህ ካንተ ይልቅ
ለሱ ቅርብ ናትና።
➵ ከሰዎች ዘንድ ፈልገህ ያጣኸውን
☞ ከአላህ ዘንድ ሳትፈልግ ታገኘዋለህ
ምክንያቱም አላህ ከምትፈልገው
ይልቅ የሚያስፈልግህን ያውቃልና።

"ደካማ ሰው ማለት ለስሜታዊ ዝንባሌ ተገዢ የሆነ (አንዳች የማይፈይድ ነገር ሳይሰራ) መልካምን ነገር የሚመኝና ከአላህ የሚጠብቅ ነው"
[Tirmizy]

:በጥረት  መልካም  ነገር  ሲሳካልህ  በአንተ  ጥረት  ሳይሆን  በአላህ እርዳታ  መሆኑን  አውቀህ   አመስግን።
ማንም ሰው በራሱ  አቅም ጭንቅላቱን ተሸክሞ  የሚሄድ የለም

   መልካም ውሎ


  husnul_khuluk