Get Mystery Box with random crypto!

ጀነትና ፀጋዋ ┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈ ውድ ወንድሜ…   የጀነት ፀጋዎች በቃላት የማይገለፁና | ⛤Islamic Direction⛤

ጀነትና ፀጋዋ
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

ውድ ወንድሜ…

  የጀነት ፀጋዎች በቃላት የማይገለፁና በሀሳብ የማይደረሱ ናቸው። የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች ነብዩን ሰለጀነት ሁኔታ እንዲነግሯቸው ጠየቋቸው።  ነብዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም) እንዲህ አሉ፦ ጠጠሮቹ ሉልና ያቁት ናቸው። አፈሩም ዛእፈራን ነው። የገቧት ይጠቃቀማሉ ፀጋ አይከዳቸውም፣ ልብሶቻቸው አያልቁም፣ ወጣትነታቸው አይከዳቸውም፣ በርሷም ዘውታሪ የማይሞቱ ሲሆኑ ሞት በነርሱ ላይ እርም ነች።

ህንፃዎቿና መኖሪያዎቿ ፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

ለአማኞች ምቹ የሆኑ ውብ መኖሪያዎች አሏት። አላህ እንዲህ ብሏል፦
لَـٰكِنِ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ لَهُمْ غُرَفٌ مِّن فَوْقِهَا غُرَفٌ مَّبْنِيَّةٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۖ وَعْدَ اللَّهِ ۖ لَا يُخْلِفُ اللَّهُ الْمِيعَادَ

( አል-ዙመር - 20)

ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለእነርሱ ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የኾኑ አልሏቸው፡፡ (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፡፡ አላህ ቃሉን አያፈርስም፡፡

ኢብኑ ከሲር (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ብሏል፦
【ልዕልናው የላቀውና ክብሩ የገነነው አላህ ደሰታን የተጎናፀፉት ሰዎች ጀነት ውስጥ ሰገነቶች እንዳላቸው ነግሮናል። እነዚህ ሰገነቶች እነርሱም አንዱ ከአንዱ የተነባበሩ ሲሆኑ በክእለትና በጥበብ የተገነቡ ህንፃዎች ናቸው።】

ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ግንባታውን ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል፦
لبنة من ذهب ولبنة من فضة ملاطها المسك الأذفر
《ግንባታቸው ከብርና ከወርቅ ሲሆን ቅባቸው ደግሞ ሚሰከል ኢዝፈር ነው።》

የጀነት ድንኳኖች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

አላህ ጀነት ውስጥ ድንኳኖች መኖራቸውን ተናግሯል።
حُورٌ مَّقْصُورَاتٌ فِي الْخِيَامِ
( ሱረቱ አል ረሕማን - 72)

በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡
ነብዩ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት
في الجنة خيمة من لؤلؤة مجوفة عرضها ستةن ميلا في كل زاوية منها إهل ما يرون الآ خرين يطوف عليهم المؤمن
«ጀነት ውስጥ ከሉል የተሰሩ ድንኳኖች አሉ የእያንዳንዱ ሰፋት 60 ማይል ሲሆን ከሰፋቱ የተነሳ በየማእዘኑ አማኞች የሚዘዋወሩባቸው የማይተያዩ ቤተሰቦች አሉ። »

የጀነት ዛፎች ፍራፍሬዎች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

አላህ ጀነት ውስጥ ብዙ ዓይነት ዛፎች እንዳሉ ነግሮናል ከነርሱ  የወይንና የሩማን ዛፍ እንዲሁም ዘንባባዎች ሲጠቀሱ ሌሎችም ቁርቁራ እና ሙዝ ዛፎች አሉ።

《ለጥንቁቆች መዳኛ ሰፍራ አላቸው አትክልቶችና ወይኖችም》

《የቀኝ ጓዶችም (ምንኛ የከበሩ) የቀኝ ጓዶች። በተቀፈቀፈ እሾህ በሌለው ቁርቁራ ውሰጥ ናቸው (ፍሬው) በተነባበረ ሙዝ ዛፍም።》

የጀነት እንሳትና አእዋፎቿ፦
•••✿❒ ❒✿•••

ጀነት ውስጥ አላህ ቢሆን እንጂ የማያውቃቸው እንሰሶችና አእዋፎች አሉ የጀነት ሰዎች ሰለሚያገኙት ፀጋ ሲገልፅ

አላህ እንዲህ ብሏል፦
《ከሚሹት በኾነ የበራሪ ሥጋ(ይዞሩባቸዋል)።》

ኢማም ሙስሊም ከኢብን መስኡድ ኢብን አንሳሪ እንደዘገቡት አንድ ሰው ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም) ዘንድ ልጓም ያላትን ግመል ይዞ መጣና ይህችን በአላህ መንገድ ላይ ትውል ዘንድ ጀብቻለሁ አለ። ነብዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም)
  «ሰባት መቶ የተለጎሙ ግመሎችን ተመነዳበታለህ» አሉት።

የጀነት ወንዞችና ጀረቶች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

ጀነት በሥሮቿ ወንዞች እንደሚፈሱ አላህ እንዲህ ሲል ነግሮናል፦

وَبَشِّرِ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ٌۖ
( አል-በቀራህ - 25)
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡

إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ
(ሱረቱ አል-ሒጅር - 45)
«እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡

የጀነት ነዋሪዎች አልባሳት፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••
የጀነት ነዋሪዎች እጅግ ማራኪና ውብ የሆኑ ልብሶችን ይለብሳሉ። በወርቅ፣ ብርና ሉል ይጋጌጣሉ። ልብሳቸውም ከሐር ነው።

يُحَلَّوْنَ فِيهَا مِنْ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٍ وَلُؤْلُؤًا ۖ وَلِبَاسُهُمْ فِيهَا حَرِيرٌ
( ሱረቱ አል-ሐጅ - 23)
በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ልብሶቻቸውም ሐር ናቸው፡፡

ምንጣፎቻቸውና አልጋዎቻቸው፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••

የጀነት ሰገነቶች ፣በመናፈሻዎቿ ውስጥ ያሉ መቀመጫዎችና የአትክልት ሰፍራዎቿ ውብ በሆኑ ቀለሞች ባሸበረቁ ምንጣፎች የተነጠፉ ናቸው።

《በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አሉ። በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም። የተደረደሩ መከዳዎችም። የተነጠፉ ሰጋጃዎችም አሉ።》
( ሱረቱ ጋሺያ 13_16)

የጀነት ነዋሪዎች አገልጋዮች፦
•••✿ ❒ ❒ ✿•••
የጀነት ነዋሪዎችን ያገለግሉ ዘንድ አላህ እጅግ መልከ መልካም የሆኑ ወጣቶች ልጆችን ፈጥሯል። በቁርአኑ ውስጥ አላህ እንዲህ ይላል።

《በነሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ። ከጠጂ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩሰኩሰቶ በፁዋም በነሱ ላይ ይዞራሉ።》

ይሁንና አላህ ሰለጀነት ፀጋዎች ያልገለፀልን እጅግ በጣም ብዙና አእምሮአችን ሊረዳው የማችልም፣ ጀሮዎች ያልሰሟቸውና በማንም አዕምሮ ውል ያላሉ ናቸው። ቡኻሪና ሙሰሊም እንደዘገቡት ነብዩ (ሰላለሁ ዐለይሂ ወስለም) አላህ እንዲህ ማለቱን ነግረውናል፦

《ለደጋጎች ባሮቼ ዓይባቸው ያላዩት፣ ጀሮዎች ያልሰሙትና በማንም ሰው አዕምሮ ውል ያላሉ ፀጋዎችን አዘጋጅቻለሁ》

فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
( ሱረቱ አል-ሰጅዳህ፣ - 17)
ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡

ሰለዚህ መንገደኛው ወንድሜ ወደዚህች ጀነት ለመግባት የሚያሰችልህን ካርድ ለማገኘት ወደ ቀጣዩ ፌርማታ አብረህን ግባ።

┄┄┉┉✽‌»‌ »‌✽‌┉┉┄┄
#ከምድራዊው_ዓለም_ወደ_መጨረሻው_ዓለም
አላህ ቀጥ ባለው በነብያት ጥሪ በተውሂድ ፀንተው ጀነትን ግቧት ከሚባሉት ያድርገን ያረብ

husnel_khuluk