Get Mystery Box with random crypto!

Henok Abayneh Gebrehiwot

የቴሌግራም ቻናል አርማ henokabayneh — Henok Abayneh Gebrehiwot H
የቴሌግራም ቻናል አርማ henokabayneh — Henok Abayneh Gebrehiwot
የሰርጥ አድራሻ: @henokabayneh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.39K
የሰርጥ መግለጫ

አሻም እንዴት ናችሁ ፤ በዚህ ቻናል ላይ ከሥነፅሁፍ እና ከሥነውበት ጋር የተገናኙ ጥሩ ሀሳቦችን ያገኛሉ ።
በFacebook ፣ በTiktok ፣በInstagram እና በTwitter :- Henok Abayneh Gebrehiwot ላይ ያገኙኛል።
ምናባቹህ የዳኘውን ሀሳብ እና አስተያየት ለማጋራት @henokpkን ይጠቀሙ።
''ኩሉ አመክሩ ወዘ ሰናይ አፅንዑ'' ( ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ)

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-06 20:08:08
በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል '' ንባብ ለህይወት'' በተሰኘው የመጻሕፍትና የምርምር ጥናት አውደ ርዕይ ላይ በመገኘቴ በጣም ደስ ብሎኝ ሳያበቃ እጅግ ማደንቃቸውንና ማከብራቸውን ደራሲዎች በአካል ለማግኘት እና ለማውራት ችያለሁ።

ከመሐመድ አሊ ቡርሃን ጋር ጥቂት የመጨዋወትን እድል ባገኘንበት ቅጽበት ጅግጅጋ ላይ ስለምናስበው የስነጽሁፍ መድረክ አውርተን ስናዘጋጅ እንደሚገኝልን ቃሉን ሰጥቶኛል። መጽሐፉ ላይ ፊርማውን አኑሮ ፣ በፎቶ ደግሞ ቅጽበትን አስቀርተናል።

@henokabayneh @henokpk
3.8K viewsedited  17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 19:44:00
ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተከሰተው አሳዝኝ ዜና ብዙዎችን ሲያሳዝን ቆይቷል። የወጣት ኢየብን ህይወት መመለስ ባንችልም በተቻለን አቅም ለቤተሰቦቹ በመረባረብ እገዛ እናድርግ።

ሰሞኑን አዲስ ክፍለ ከተማ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ሳቢያ ግንብ ተደርምሶ የሰዎች ህይወት አልፏል። በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት አንዱ ወጣት ኢዮብ ወልደማርያም ሲሆን የሞተበት ሰብአዊነትን የተላበሰ ሁኔታ ብዙዎችን አሳዝኗል። የሰው ህይወት ለማትረፍ ሲል የራሱን ህይወት እንዳጣም ቤተሰቦቹ ገልፀዋል።

በአደጋው መኖሪያ ቤቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት የሟች እዮብ ቤተሰቦችም አሁን ላይም ለቅሶ የተቀመጡት ቤተዘመድ እንዲሁም ጎረቤት ቤት ነው። በቀጣይም ማረፊያቸውን እንደማይታወቅ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

የኢዮብን ወላጆች ማገዝ ለምትፈልጉ በእናት ራውዳ ጀማል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት (CBE) 1000010020011 እና በአባት ወልደማርያም ሸዋ የባንክ አካውንት (CBE) 1000291553749 ማገዝ ትችላላችሁ። በስልክ እናት ራውዳ ጀማልን በ0911225960 እንዲሁም ደግሞ አባት ወልደማርያም ሸዋን በ 0911137825 ላይ ማግኘች ይችላል።

@henokpk @henokabayneh
559 views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 15:28:18 ከአማርኛ ወደ አማርኛ

ርዕስ፦ ኣማርኛ መዝገበ ቃላት
ጸሐፊ/አዘጋጅ፦ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል አ.አ ዩኒቨርሲቲ
የገጽ ብዛት፦ 679
መጠን፦29.2MB

@henokpk @henokabayneh
4.6K viewsedited  12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 14:03:46 ደራሲ - ማዕበል ፈጠነ

@henokpk @henokabayneh
4.2K viewsedited  11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 20:56:04
የብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ 86ኛ ዓመት መታሰብያ ዝክር ላይ መገኘት በመቻሌ የተሰማኝ ደስታ ከፍተኛ ነው። በርቀት የሚመለከቱትን ትዕይንት በአካል መታደል ዓለም ነው። የነፍስን አቅል ያስታል። '' የመጨረሻውን ቃል ለጀግናው ተውለት'' እንዲሉ አቡነ ጴጥሮስ በጥቂት ቃላቸው የሀገርን ፍቅርን ፣ ሀይማኖትን ፣ አርበኝነትን ፣ አባትነትን ቋጥረው ለታሪክ አልፈዋል። ለትውልድ ስላለፉ ፤ ትውልድ ይዘክራቸዋል። የጊዜው ትውልድ አካል ነንና ስንዘክራቸው በሙሉ ተድላ ነው።

አዎ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
ምጸናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሰጋሁ!"

­­­– ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኀን
3.8K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 08:22:55 የሀሳብ ዝቋላ

ደስተኛም አይደለሁ ደግሞም አይከፋኝም ፣ መኸል ላይ ያለ መዋተት ምን ይባላል ፣ የሳቅ ጥጉን አልወደውም ፣ በብሶት መቆየትም የፍላጎቴ ጭፍራ አይደለም። በማውራት እና በዝምታ መኸል ያለውን መንገድ ወደዋለሁ ግን እንዳስረዳው የሀሳቤም የቃላቴም አቅም አይፈቅዱልኝም። በመጎዳት እና ባለመጎዳት መኸል ፣ በተስፋ እና በፀፀት ፣ በህጸጽ እና በልክነት ፣ በቅንነት እና በንፉግነት መኸል ነው ያለሁት።

ማንም ሊረዳልኝ ይድሃል ግን የመልሱን ጫፍ አልያዘውም። ዳፍንት እንደያዘው ሰው ከማንነቴ ጋር እዳክራለሁ ፣ እደናበራለሁ ቆይቶ ደግሞ ስለ ራሴ ለማወቅ ራሴን ሰልላለሁ። ቢሆንም የሆነ ነገር ሰብሮኛል ፣ የሆነ ነገር የቅዠት አለም ውስጥ ከቶኛል ፣ ሰመመን ለኔ ይጠጋል ፣ በንጋት እና በጨለማ ትግል ውስጥ ያለው የቅጽበት ሁኔታ ለኔ ስሜት ይቀርባል። በህልም ያየውን በህይወት የሚኖር የሚመለስለውን ስሜት ( De javu ) ስሜቴን ይመስላል። ስስቅ የሆነ ነገር ወደ ኋላ ይጎትተኛል ፣ ሳለቅስም ይጎትተኛል ፣ ልክም ነኝ ልክም አይደለሁም። በማወቅ እና ባለማወቅ ውስጥ ተሸጉጫለሁ። በህይወት ውስጥ የሰው ልጅ በአደጋ አልያም በተፈጥሮ ክስተት እጁን እግሩን የተለያዩ የሰውነት አካሉን ያጣል። እኔም የሆነ ማይታይ ስሜቴን አጥቻለሁ ፣ አለም ያለበየነልኝ ፣ ማህበረሰቡ ያልተገነዘበልኝ ውስጠቴን አጥቻለሁ። ማመዛዘኔን አጥቻለሁ ፣ የመኖር ትርጉም ሚሰጠኝን ህዋስ አጥቻለሁ። ደስታም ሀዘንም ሚሰጠኝን ህዋስ አጥቻለሁ ፣ ትውስታ ብቻ ነው ያለኝ ፣ ትናንት ብቻ።

አትችልም ሲሉኝ ፣ ባትፈጠር ይሻል ነበር ሲሉኝ ፣ ደደብ ሲሉኝ ፣ ሙትቻ ሲሉኝ ፣ አላፈቅርህም ስትለኝ ፣ ከዛ በኃላ እኔን አይደለሁም ፤
ማንነቴን ተሰርቂያለሁ ፣ የፍቅር ፣ የተስፋ ፣ የሞራል ማጣት በሽተኛ ነኝ። ከመኖር ብቻ ተቆንጥሮ የተሰጠኝ። ህክምናዬም ሚገኘው ያጣሁትን መልሼ በማግኘት ውስጥ ይሁን ? .....እንጃ። ይሄን ሁሉ ግን እንዴት አመዛዝኜ ፃፍኩት ? አላውቅም። .....ምን አልባት በድብቁ የአእምሮዬ ክፍል ይሁን ? ( Subconscious mind)... እስከዚያ ግን በዚህ ግጥም ልመሽግ።

ከመኖር መቃየም ፣ እንዴት ነው አመሉ ?
የምኞትን ህይወት ፣ ህይወቴ ነው ሲሉ ?
ብዙ እንባዎችን ፣ በሳቅ ሲያታልሉ ?
የሚያልፍን እስትንፋስ ፣ በመንፈስ ሲገሉ ?
እንዴት ነው ችንካሩ ፣ እንዴት ነው ህመሙ ?
የሞትን ትግል ፣ በኑሮ እስኪያደክሙ ?

– @henokpk

@henokabayneh
4.4K viewsedited  05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 19:15:32
እኔ ከሴት ልጅ ውበት ቀልቤን የሚያስተኝ ነገር ቢኖር የእግር ውበት ነው። ልክፍት አለብኝ። ቆንጆ የሴት እግር ካየሁ አብሾ ይነሳብኛል። አቤየየየየት የሴት እግር ፤ ቆንጆ የሴት እግር ማየት ስወድ። ብዙዎቹ እንዲህ ዓይነቱን ወንድ 'ልክስክስ ' ይሉታል። ድፍን የዓለም ሕዝብ ከኋላይ እየተከተለ በዓለም ቋንቋዎች ሁሉ '....አብርሃም ልክስክስ ፤ ለከስካሳ ውሻ !!' እያለ ቢጮህ እንኳን እግር ከማየት ፣ ቆንጆ የሴት ልጅ እግሬ ከማድነቅ ወደ ኋላ አልልም።

- አሌክስ አብርሃም ( ዙቤይዳ )

@henokpk @henokabayneh
3.6K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 08:47:39 ደራሲ - ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

@henokpk @henokabayneh
3.9K viewsedited  05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:42:42
ሀገር የምትራመደው በአንድ ሳንቲሜትር እውቀት ፣ በመቶ ሜትር ሥነሥርዓት ነው።

- አዳም ረታ

@henokpk @henokabayneh
1.7K viewsedited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:39:43
ቢኒያም ኢሳያስ ይባላል፤ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 5ኛ ዓመት የሕክምና ተማሪ ነዉ ፤ በተፈጥሮ ምክንያት አካል ጉዳተኛ ቢሆንም፤ በራሱ ጥረት በሕክምና ትምህርት እስከ 5ኛ ዓመት በትጋት ተምሩዋል፡፡ በህክምናው ያለው ውጤት CGPA 3.8 ነው።

ነገር ግን ሊመረቅ የሁለት ዓመት ጊዜ ሲቀረዉ ትምህርቱን መቀጠል እንደማይችልና ማቋረጥ እንዳለበት ዉሳኔ ከተቋሙ ይተላለፍበታል። እንደ ምክንያት የቀረበው ሀሳብ ተማሪው አካል ጉዳተኛ ስለሆነ ትምህርቱን በአግባቡ መውጣት እንደሚቸግረውና ትምህርቱን አቁሞ ሌላ ትምህርት መጀመር አለበት የሚል ነው። ይህ የስላቅ ምክንያት ከጅምሩ ያልተነሳ በማምሻው ላይ የተነሳ ጥያቄ መሆኑን ልብ ይሏል። በመደምደሚያው ጊዜ ይህን ማንሳት ምን አይነት ህሊና ቢስነት ነው ? የተማሪው ሞራል ፣ ድካም ፣ ችሎታ ከግምት ገብቷል ?

ይህ የመብት ጥሰት የአንድ ተማሪ ብቻ ሳይሆን የብዙ አካል ጉዳተኞች ነው ፤ ስለሆነም ይህ ልጅ በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታዉ እንዲመለስ በአፅንኦት እንጠይቃለን። በማስረጃ የተደገፈ የህግ ድጋፍ አለው። ይህ ተግባርም ጥቁር አንበሳን ከመሰለ አንጋፋ ተቋም ማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት ነው።

@henokpk @henokabayneh
3.0K viewsedited  16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ