Get Mystery Box with random crypto!

Henok Abayneh Gebrehiwot

የቴሌግራም ቻናል አርማ henokabayneh — Henok Abayneh Gebrehiwot H
የቴሌግራም ቻናል አርማ henokabayneh — Henok Abayneh Gebrehiwot
የሰርጥ አድራሻ: @henokabayneh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.39K
የሰርጥ መግለጫ

አሻም እንዴት ናችሁ ፤ በዚህ ቻናል ላይ ከሥነፅሁፍ እና ከሥነውበት ጋር የተገናኙ ጥሩ ሀሳቦችን ያገኛሉ ።
በFacebook ፣ በTiktok ፣በInstagram እና በTwitter :- Henok Abayneh Gebrehiwot ላይ ያገኙኛል።
ምናባቹህ የዳኘውን ሀሳብ እና አስተያየት ለማጋራት @henokpkን ይጠቀሙ።
''ኩሉ አመክሩ ወዘ ሰናይ አፅንዑ'' ( ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ)

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-07 20:51:12
ለሰው ክብር ለሚጨነቁ !

ርሃብ አይደለም ፣ ከፊትህ ያቆመኝ
ገንዘብም አይደለ ፣ ይበቃኛል ያለኝ
ካንተ ' ምጠይቀው መከበርን ብቻ
የነጻነት ክብር ፣ የሰው መሆን አቻ

- ዑመር ኻያሚ ( ጋሽ ተስፋዬ ገሰሰ እንደተረጎመው )

@henokpk @henokabayneh
4.0K viewsedited  17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 19:49:02 ለፈገግታ
.
.
ኑሮ በዚሁ ከቀጠለ የ15 ብር ካርድ 25 ብር መግዛታችን ነው።

@henokpk
4.0K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 20:44:48
"ሲመስለኝ ርጣቄ የለንም።

'ርጣቄ' አተኩሮ ማጥናት ነው።

እኛ አተኩረን ያጋጠመንን እናወራለን እንጂ አናጠናም።

አእምሮአችን ሰነፍ ስለሆነ ከሌላ ሰው ምላስ ነው እውነትን የምንቀበለው።

ከጠላታችንም ምላስ፤
ከሚያጠፋንም ምላስ።"

- አዳም ረታ

@henokpk @henokabayneh
4.3K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 19:32:45 ትዝታዬ ትዝታሽ ነው

አለ አይደል ንግግር ምንም ሳይፈይድ ሲቀር ግብሩ ጉንጭ ማልፋት ሲሆን ፣ ዝምታ በፀጥታ ተሞሽሮ ለመናገር ሲያጎበደድ ይህንን ባህሪ ባንቺ እመለከታለሁ ፡ ሳልናገር ወደ ደረትሽ አስጠግተሽ የብሶቴን ኑዛዜ በእቅፍሽ ስትፅፊ ። ወሬ እንኳን ከአፌ ሳይወጣ መደበሬን ስታውቂ ፣ እኔን ለማስደሰት ያለ አቅምሽ አቅም ለማበጀት ስትጣጣሪ የእውነት ውስጤን ይከፋዋል ፤ ታድያ የደስታ መከፋት ነው ። ሰውነቴ ግን ውሃ ይሆናል ። የግራ አይኔ ከቀኝ አይኔ ተሽቀዳድሞ የእንባ ዘለላ ከአይኑ ያወርዳል ። ግና ያንን እንባ ከአይኔ ላለማየት ዞረሽ ስትሸማቀቂ የእንባዬን ወኔ መቋቋም አቅቶሽ ዞረሽ በጣቶችሽ አይኔን ስትደባብሽ ከቀድሞው የባሰ ሆዴ ይባባል ፣ ለወጉ ፀሀፊ ነህ ይሉኛል ? እንዴት ልገለፀው ስሜትሽን ? እንዴት ልተርከው ወስጠትሽን ?

አንቺማ ምንሽ ሞኝ ? ... የማሳመም ረቂቅሽን መፃፍ የጀመርሽው እዚሁ ጋር ነው።.... ወዲያው ደግሞ ጣሪያው ማቃሰት ሲጀምር ዝናብ እንዳይሆን ? ብለሽ ተስፈንጥረሽ ስትነሺ ከተፈጥሮ ተፃረሽ ከዳመነው ሰማይ ገዝፈሽ ማንም ያልታዘበውን ህቡዕ ፈገግታ ስትችሪኝ ፤ ዝናቡ ማቃሰታዊ ስልቱን አቁሟ ዶፋዊ ስልቱን ሲጀመር ቆርቆሮው የጩኸት ግብሩን ሲፈፅም ....ሽሽሽሽሽ ሲል አሁን ድረስ በጆሮዬ አለ....ተሽቀዳድመሽ አንሶላውን ከታች ወደ ላይ በጣቶችሽ ዘውረሽ ወደ ውስጥ ስትገቢ ፡ የበረደው ሰው የሚወርደውን የመንቀጥቀጥ እስክስታ ስትወርጂ ጥርሶችሽን እያጋጨሽ ወደኔ ዞረሽ ስትፈግጊ ፡ ዝናቡም ተፈጥሮአዊ ወጉን ሳይለቅ በመብረቅ መባረቅ ሲታገዝ ወደ ደረቴ ተጠግተሽ እጄን በእጆችሽ ጨምቀሽ በለሆሳስ '' መብረቅ ፈራለሁ '' ስትይኝ እኔም የአብርሃም በግነት ተልኮዬን በመወጣት በደንብ ሳቅፍሽ ፡ በዝናቡ ውስጥ ሰው እንዳይሰማሽ ይመስል ወደ ጆሮዬ ተጠግተሽ '' ህይወት የትዝታ ማጥ ነች ባትፈልግም ትያዛለህ ተይዘኸል። '' ያልሽኝ ጊዜ ለካ ረቂቁ ፅሁፍሽ መፅሐፍ የሆነዘት ጊዜ ነበር ።

ቅጥል ነኝ ፣ ተላላ እኮ ነኝ መች ሊገባኝ ? ነግረሽኝ ነበር አልማስተዋሌ ፣ ገስፀሽኝ ነበር አለመገሰፄ ፣ መክረሽኝ ነበር አለመመከሬ ፤ ልትለይኝ ነገር ህመም ጣልሽብኝ ላጣሽ ነገር ንፁህነት ጨመርሽብኝ ፣ የውሃ ሽታ ሆነሽ መቅረትሽን እያወቅሽ ጨከንሽብኝ .....አስተክዘሽኝ ፡ ያለመድኩትን አስለምደሽ በረርሽብኝ ፣ ቀልደሽ ቀለድሽብኝ ፣ በንግግር ሳይግባቡኝ በዝምታ ተግባብተሽ ፤ በማውራት ሳያነቡኝ በእንባ አንብበሽ ጠፋሽብኝ። ... ለዘላለም አሸለብሽኝ.... እናማ በሽታ ይሉት ወናፍ ምክንያት አንቺነትሽን ገታው። እውነት ጨካኝ ነሽ ንፁህነትሽን ልቤ ላይ አትመሽ ላላይሽ ኮበለልሽ። አሁንማ ይገረምሽ መንገደኛው ሁሉ '' አብድ '' ነው ሚለኝ... እሰይ ፡ እንኳን አሉኝ ፤ .....በትዝታ ይዘሽኝ የለ ፣ ማበድ ሲያንሰኝ ነው።

– @henokpk

@henokabayneh
4.8K viewsedited  16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 14:56:45 "ኋላ ቀር ሕዝብ እርስ በርሱ ሲሽቀዳደም ጊዜ ራሱ ቀድሞ ያመልጠዋል፡፡ ጊዜ ያመለጠው ሕዝብ ደግሞ ከኁዋላው ሌላ ሕዝብ ሊኖር አይችልምና ኁዋላቀርነቱን ማንም ሊወስድበትም ሆነ ሊወሰድለት አይችልም"

— በዶ/ር ምህረት ደበበ

@henokpk @henokabayneh
4.9K viewsedited  11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 19:54:05 እያንዳንዱ ሰው ልክ እንደጨረቃ ነው ፤ ለማንም የማያሳየው ግማሽ ጎን አለው

- ማርክ ትዌይን

@henokabayneh @henokpk
6.2K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 13:47:35 ደራሲ - ይስማዕከ ወርቁ

@henokpk @henokabayneh
6.1K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 19:49:04 የቅፅበት ናፍቆት

ጠብቅኸለሁ ፣ ጠብቅኸለሁ . . . . የቀረብከኝ ለጥቅም ቢሆንም ፣ ጥግጊትህ ለውስለታ ቢጠጋጋም ፣ መቅረብህ ለመዳራት ቢቀርብም ፣ ውጥንህ ለውበቴ ለማደግደግ ቢቋምጥም ፣ እሽሩሩህ እስከ አልጋ ቢሾርም ፣ ውዴታህ እስከ አዳር ቢያክልም ፣ ሽኩሽኩታህ እስከ ስሜትህ ቢዘልቅም ፤ ጠብቅኸለሁ።

ሁሉም ነገርህ ውሸት ቢሆንም ውሸትህን አፍቅሬዋለሁ። ሁሉም ቅጥፈት ቢሆንም ከቅጥፈትህ ተለክፍያለሁ ፤ መወደዴ ግን እስከየት ድረስ ነው ? እሰከመዋሸት ፣ እስከመታለል ? ግን መቸም ተስፋ አልቆርም ፣ ባንተ ሳይሆን በፍቅር ተስፋ አልቆርም ፣ በተስፋ መቁረጥ ተስፋ አልቆርጥቅም ፣ በስሜቴ ተስፋ አልቆርጥም አንድ ቀን ትመጣለህ ፣ ትዝታዬ ግድ ይልኸል ፣ ጣዕሜ ግድ ይልኸል ፣ ለዛዬ ግድ ይልኽል !. . . .

አይገርምህም ? እስካሁን ጉንጬ ላይና ከንፈሬ ላይ የከንፈር ንኪት አለ። አእምሮዬ ላይ የምስልህ ታቦት ከትዕዛዛቱ ጋር በአቻነት ተማግዷል። ስላንተ ሳስብ ሰውነቴ ውሃ ይሆናል ፣ አስቀይመኸኝ በመቀየም ራሱ ተቀይምያለሁ ፣ ናፍቀኸኝ ከናፍቆት ተጣልቻለሁ ። ልለምነህ አይደለም ይህን ማለቴ ፣ ልሸነግልህም አይደለም መርገፍገፌ ፣ ልዕልናን ለማወጅ አይደለም መንተባተቤ ፤ የናፍቆት ስሜቴን ለማከበር ነው።

ምን አልባት ከናፍቆት ስሜቴ ስወጣ ምኔም ላትሆን ትችላለህ ። አሁን ግን የናፍቆት አውድ ውስጥ ነኝ . . . አሁን ናፍቀኸኛል ...አሁን ውል እያልክብኝ ነው. . ብታይ እኮ...አይኔ ናፍቆኸል ፣ ጥርሴ ናፍቆኸል ፣ ከንፈሬ ናፍቆኸል. . . ሁሉመናዬ ናፍቆኸል። . . .ከቻልክ ናና አሁኔን ፈንጭባት ፤ ነገዬን ግን ከናፍቆቴ ፣ ከፍቅሬ ፣ ከስሜቴ ውጪ ያለው እኔነቴ ይጠቀመው ...አንተ ግን ና

– በ @henokpk

@henokabayneh
7.0K viewsedited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ