Get Mystery Box with random crypto!

Henok Abayneh Gebrehiwot

የቴሌግራም ቻናል አርማ henokabayneh — Henok Abayneh Gebrehiwot H
የቴሌግራም ቻናል አርማ henokabayneh — Henok Abayneh Gebrehiwot
የሰርጥ አድራሻ: @henokabayneh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.39K
የሰርጥ መግለጫ

አሻም እንዴት ናችሁ ፤ በዚህ ቻናል ላይ ከሥነፅሁፍ እና ከሥነውበት ጋር የተገናኙ ጥሩ ሀሳቦችን ያገኛሉ ።
በFacebook ፣ በTiktok ፣በInstagram እና በTwitter :- Henok Abayneh Gebrehiwot ላይ ያገኙኛል።
ምናባቹህ የዳኘውን ሀሳብ እና አስተያየት ለማጋራት @henokpkን ይጠቀሙ።
''ኩሉ አመክሩ ወዘ ሰናይ አፅንዑ'' ( ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ)

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 21:02:10
ማንበብ ምን ይጠቅማል ? የሚያነቡ ሰዎች የሚያገኙት ጥቅም ምንድነው ? ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ ዶክተር ኢዮብ ማሞ በአምስት ጥሩ ነጥቦች እንደዚህ አስፍሮታል። በተለይ በሶስተኛነት ያስቀመጠውን ሀሳብ በጣም ወድጄዋለሁ።

1. ካለማቋረጥ ራሳቸውን ያሻሽላሉ።

2. ጊዜያቸውን በተራ ነገር ከማሳለፍ ይጠበቃሉ።

3. ጸሃፊዎቹ ብዙ ጊዜ ወስደው በልምምድና በጥናት ያገኙትን እውቀት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይቀስማሉ።

4. አእምሯቸው በንባብ ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ስለሚል ለተራ ወሬና ለወረዱ ነገሮች ጊዜውም ሆነ ፍላጎቱ አይኖራቸውም።

5. የውስጥ እርካታና መረጋጋትን ያዳብራሉ።

@henokpk @henokabayneh
207 views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:23:33
ቡና ለመጠጣት በዚያውም ትንሽ ገጽ ለማንበብ ተስይሜ ሳላውቀው በምስጠት ጨረስኩት። አንብቡት ይጣፍጣል ! ስለህይወት ብዙ ብዙ ይላቹኸል። . . .ተናግሬ ከማበላሸው አንብባችሁ ተደመሙበት። . . .እንደ ቡናው ይጥማል !

@henokpk @henokabayneh
1.3K viewsedited  16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:45:07 ምስጋና እና የመረጃ ማቃኛ!
___

ሰሞኑን አሜሪካ ወደሚገኘው IOWA ዩኒቨርስቲ ከማምራቴ ጋር ተያይዞ እዚሁ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሃሳቦች ሲንሸራሸሩ ሶስት ነገሮችን አስተዋልኩ።

የመጀመርያው በደግ ዐይናቸው የሚያዩኝና ስኬቴን የሚናፍቁ ሰዎች መብዛታቸው! የምሥራቹን ለማብሰር መጣደፋቸው! (ክብረት ይስጥልኝ ከማለት ውጪ ምን እላቸው ኖሯል?)

ሁለተኛው ማቃኛ የሚፈልጉ መረጃዎች በፍጥነት መራባታቸው። አንዳንድ ቦታ እንደተባለው ቆይታዬ ለአመታት አይደለም ለጥቂት ወራት እንጂ። IOWA ዩኒቨርስቲ ብቻ ለአስር ሳምንታት ስንቆይ ሶስት አራት ሳምንቱን ደግሞ ይህን በመሰለ በሌሎች ፕሮግራሞች እንጠመዳለን። እርግጥ  ለዚህ ፕሮግራም ተመራጭ ሆኖ መገኘት ይህን ለመሰለ ሌላ ዕድል በር የሚያስከፍት መሆኑን የቀደመ ተመክሯቸውን አንስተው ነግረውናል።

ሶስተኛው ደግሞ " አንተ ከሄድክ ዘወትር ቅዳሜ ከአስር እሰከ አስራሁለት ሰአት ከተለያዩ ደራስያን ጋር የምናደርገው (ዛጎል የመጻሕፍት ባንክና  ዋልያ መጻሕፍት አንድ ላይ የሚያሰናዱት) ቆይታስ? ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ መጻሕፍት እየሰበሰበ መልሶ በገጠር ከተማው የሚያሰራጨው  ነገርስ? በእጥልጥል ሊቀር?" የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱልኝ ነው። ከደራስያን ጋር የሚደረገው ውይይት እኔን ተክቶ ሌላ ሰው እንዲያወያየው ተወጥኖ የነበረ ቢሆንም ይህም በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሳይሆንልን ቢቀርም: ፕሮግራሙ ግን በተለመደው ሰአት በልዩ ልዩ ኪናዊ ስራዎች ዝግጅቱን ያቆዩታል። ውይይቶች ዲስኩሮችና የመጻሕፍት ምርቃቶች ይካሄዱበታል። የመጻሕፍት ባንካችን አገልግሎትም አይቋረጥም። (እስካሁን ከሰላሳ አራት ሺህ በላይ መጻሕፍት በገጠር ከተማው እንዲዳረስ ምክንያት በመሆናችን እና  ከዋልያ መጻሕፍት ጋር ሆነንም
ከሰባ  በላይ የሆኑ መጻሕፍት ላይ ትኩረት ማድረጋችን ደስታ ቢሰማንም ካደረግነው ይልቅ ልናደርግ ያሰብነው እንደሚልቅ ደግሞ ደጋግመን ልንነግራችሁ እንወዳለን)

በመጨረሻም አሸናፊ ስለሆንኩበት ፕሮግራም በአጭሩ! (ወደፊት ዘለግ አድርገን እስክናወጋ)

IOWA ዩኒቨርስቲ በየአመቱ ከየአለማቱ ደራስያንን መርጦ ፕሮግራም የማሰናዳት ልማድ አለው። ጉምቱ ጉምቱ የብዕር ሰዎችም የኖቤል ሽልማት ወሳጆችም የዕድሉ ተቋዳሽ ሆነዋል። እንዲህ ያለው አጋጣሚ ኢትዮጵያ ሊያልፋት አይገባም በማለት ሲብሰከሰክ የምናውቀው ጌዲዮን ማሞ እንዳጫወተኝ ኤምባሲው በየአመቱ ያለመታከት አወዳድሩልኝ ብሎ ምርጦቹን ቢልክም  እንደዘንድሮ ግን በለስ ቀንቶት አያውቅም።

የሆነው ሆኖ ዘንድሮ ውድድሩ የተከናወነው በሚከተለው መንገድ ነው። መጀመርያ እያንዳንዱ አገር ለዚህ ዕድል ብቁ ናቸው የሚላቸውን ደራስያን ስም ዝርዝር ላከ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲ ሶስት ደራስያንን መርጦ ስለሚጽፉበት ርዕሰጉዳይ ገልጾ "አርአያ ናቸው: ኢትዮጵያን ይወክሉልኛል: ቢያሸንፉ እነሱም እናንተም ደስታና ኩራት ውስጥ ትገባላችሁ!" ብሎ ዝርዝር መረጃ ላከላቸው። እነሱ ደግሞ ስለደራስያኑ የተባለውን በራሳቸው መንገድ አጠኑ። ከዚያም ከሶስቱ አንዱን ብቻ ለይተው ዕጩ አደረጉ። እንደገና እሱንና የሌሎች አገራት ዕጩዎቹን ደግሞ አወዳደሩ። መቶ አስራአምስት ገደማ(?) ደረሱ። የሚፈልጉትና እርስ በርስ ልምድ እንዲለዋወጡ የሚፈልጓቸው የደራስያን ቁጥር ደግሞ ከሰላሳ እስከ ሰላሳአምስት ባለው ቁጥር ቢወሰኑ  እንጂ እንዲበዙባቸው አይፈልጉም።
ስለዚህ የአሸናፊዎች አሸናፊን ለይቶ ለማውጣት ቃለመጠይቅ አደረጓቸው። መረጃዎቻቸውን አሰባሰቡ። ስለሚያተኩሩባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መረመሩ።

በመጨረሻም አሸናፊ ሆኖ ሲገኝ ለኤምባሲውም ለደራሲውም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ሙሉ ወጪውም በአሜሪካ ኤምባሲና በዩኒቨርስቲው እንደሚሸፈን አበሰሩ።

(እኛም ተደሰትነ!)

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ በዚህ ዩኔስኮ የሥነጽሑፍ ከተማ ብሎ በሰየማትና በየዓመቱ ታላላቅ የሥነጽሑፍና የቴአትር መሰናዶዎች በሚኮመኮምባት IOWA CiTY ስሟ ሲነሳ ይህ መጀመርያዋ አይደለም። እኤአ በ1967 ስመጥሩው ደራሲ ዳኛቸው ወርቁም (የ"አደፍርስ" ደራሲ) አሸናፊ ሆኗል::

ወደፊት ደግሞ እንበዛለን ብዬ አምናለሁ።

ሰላም!!!!!


ምንጭ :- ዋልያ የመጻሕፍት ባንክ

@henokpk @henokabayneh
1.9K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:45:02
1.6K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:58:10
ገጣሚ :- መዘክር ግርማ
የሥነግጥሙ ርዕስ - አንድ ልጅ አዝማሪ

@henokpk @henokabayneh
2.2K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 20:41:04
ሶልያና ' የተሰኘ ሥራው ከግጥሙም ጭምር ፍቅር ያስያዘኝ ግጥም ነው። ስሜቱን በግልጽ ሚከተብ ገጣሚ ነው። ሥራዎቹ  በፍቅር የተጎዳ ማንነት ያለው ፣ ትዝታ የለበለበው ፣ ፍቅር ማጣት የእግር እሳት የሆነበት የግልጽነት ስሜት ያለባቸው ናቸው። እኛኝ ሚመስሉ ናቸው። ብሶት አላቸው ፣ ህይወት አላቸው ፣ እውነት አላቸው ፣ ፍልስፍና አላቸው።

'' ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር '' ብሎ ትዝታን ያስታምማል። '' ውሸት ነው '' ብሎ ለምናብ የሚተው ሀሳብ ይዘይራል። በድምጽ ቀድቶ ያደረሰን ግጥሙ መመሸግያ ነው። ቆሌዬ ይወደዋል። ደግሞ አገኘሁት ፣ ጠየቅኩት ፣ አመሰገንሁት። አስበኸው ሳይሆን ሆነኸው ምታገኘው ደስታ አለ አይደል ? ...እንዲያ ነው የተሰማኝ።  

@henokpk @henokabayneh
2.8K viewsedited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 15:10:50 "ግጥም ያልተንዛዛ ፍልስፍና ነው"

በእውቀቱ ስዩም

- @henokpk @henokabayneh
2.4K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 15:16:52 @henokpk @henokabayneh
2.9K viewsedited  12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 22:28:23 Henok Abayneh Gebrehiwot pinned «የቅፅበት ናፍቆት ጠብቅኸለሁ ፣ ጠብቅኸለሁ . . . . የቀረብከኝ ለጥቅም ቢሆንም ፣ ጥግጊትህ ለውስለታ ቢጠጋጋም ፣ መቅረብህ ለመዳራት ቢቀርብም ፣ ውጥንህ ለውበቴ ለማደግደግ ቢቋምጥም ፣ እሽሩሩህ እስከ አልጋ ቢሾርም ፣ ውዴታህ እስከ አዳር ቢያክልም ፣ ሽኩሽኩታህ እስከ ስሜትህ ቢዘልቅም ፤ ጠብቅኸለሁ። ሁሉም ነገርህ ውሸት ቢሆንም ውሸትህን አፍቅሬዋለሁ። ሁሉም ቅጥፈት ቢሆንም ከቅጥፈትህ ተለክፍያለሁ…»
19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 19:02:17 @henokpk @henokabayneh
3.4K viewsedited  16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ