Get Mystery Box with random crypto!

Orthodox twahedo(@zelideta)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodocstewahdo — Orthodox twahedo(@zelideta) O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodocstewahdo — Orthodox twahedo(@zelideta)
የሰርጥ አድራሻ: @ortodocstewahdo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 630
የሰርጥ መግለጫ

Ortodocs tewahdo

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 10:46:12 ማቴዎስ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ፥ ከገሊላ ሄዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መጣ።
² ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፥ በዚያም ፈወሳቸው።
³ ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሲፈትኑት፦ ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን? አሉት።
⁴ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥
⁵ አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን?
⁶ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።
⁷ እነርሱም፦ እንኪያስ ሙሴ የፍችዋን ጽሕፈት ሰጥተው እንዲፈቱአት ስለ ምን አዘዘ? አሉት።
⁸ እርሱም፦ ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም።
⁹ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል አላቸው።
¹⁰ ደቀ መዛሙርቱም፦ የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም አሉት።
¹¹ እርሱ ግን፦ ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤
¹² በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው።
¹³ በዚያን ጊዜ እጁን እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው።
¹⁴ ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤
¹⁵ እጁንም ጫነባቸውና ከዚያ ሄደ።
¹⁶ እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ፦ መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው።
¹⁷ እርሱም፦ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው።
¹⁸ እርሱም፦ የትኞችን? አለው። ኢየሱስም፦ አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥
¹⁹ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።
²⁰ ጐበዙም፦ ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው? አለው።
²¹ ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።
²² ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ።
²³ ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው።
²⁴ ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።
²⁵ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና፦ እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል? አሉ።
²⁶ ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው።
²⁷ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው።
²⁸ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።
²⁹ ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።
³⁰ ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።
49 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 10:46:11 “ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።”
— ኢሳይያስ 55፥7
34 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 10:46:11 ሕዝቅኤል 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
² ስለ እስራኤል ምድር፦ አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ብላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድር ነው?
³ እኔ ሕያው ነኝና እንግዲህ ወዲህ ይህን ምሳሌ በእስራኤል ዘንድ አትመስሉትም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
⁴ እነሆ፥ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ደግሞ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።
⁵ ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥
⁶ በተራራም ላይ ባይበላ ዓይኞቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ አደፍም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ፤
⁷ ሰውንም ባያስጨንቅ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ ፈጽሞም ባይቀማ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ የተራቈተውንም በልብስ ቢያለብስ፤
⁸ በአራጣ ባያበድር፥ ትርፎቻም ባይወስድ፥ እጁንም ከኃጢአት ቢመልስ፥ በሰውና በሰው መካከልም የእውነትን ፍርድ ቢፈርድ፤
⁹ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እውነትንም ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፥ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
¹⁰ እርሱም ቀማኛና ደም አፍሳሽ ልጅ ከዚህም ሁሉ አንዳቸውን የሚያደርገውን ቢወልድ፥
¹¹ እርሱም ጻድቅ አባቱ የሠራውን ሁሉ ባይሠራ በተራራም ላይ ቢበላ የባልንጀራውንም ሚስት ቢያረክስ፥
¹² ድሀውንና ችግረኛውንም ቢያስጨንቅ ቢቀማም መያዣውንም ባይመልስ ዓይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ ርኩስን ነገር ቢያደርግ፥
¹³ በአራጣ ቢያበድር፥ ትርፎቻም ቢወስድ፥ በውኑ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም፤ ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል፤ ደሙ በላዩ ላይ ይሆናል።
¹⁴ እነሆም፥ ልጅ ቢወልድ፥ እርሱም አባቱ የሠራውን ኃጢአት አይቶ ቢፈራ እንዲህም ባይሠራ፥
¹⁵ በተራራ ላይ ባይበላ ዓይኖቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ፥
¹⁶ ሰውንም ባያስጨንቅ መያዣውን ባይወስድ ባይቀማም ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ ለተራቈተውም ልብስን ቢያለብስ፥
¹⁷ እጁንም ድሀን ከመበደል ቢመልስ አራጣን ትርፎቻንም ባይወስድ ፍርዴንም ቢያደርግ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።
¹⁸ አባቱ ግን ፈጽሞ በድሎአልና፥ ወንድሙንም ቀምቶአልና፥ በሕዝቡም መካከል ክፉን ነገር አድርጎአልና እነሆ፥ እርሱ በበደሉ ይሞታል።
¹⁹ እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኃጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን ባደረገ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና ባደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።
²⁰ ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤ ልጅ የአባቱን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጁን ኃጢአት አይሸከምም፤ የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የኃጢአተኛውም ኃጢአት በራሱ ላይ ይሆናል።
²¹ ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
²² የበደለው በደል ሁሉ አይታሰብበትም፤ በሠራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል።
²³ በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?
²⁴ ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ ኃጢአትንም ቢሠራ ኃጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም፤ ባደረገው ዓመፅና በሠራት ኃጢአት በዚያች ይሞታል።
²⁵ እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ መንገዴ የቀናች አይደለችምን? ይልቅስ የእናንተ መንገድ ያልቀናች አይደለችምን?
²⁶ ጻድቁ ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኃጢአትንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያም ቢሞት፥ እርሱ ባደረገው በደል ይሞታል።
²⁷ ኃጢአተኛውም ከሠራው ኃጢአት ቢመለስ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ነፍሱን ይጠብቃል።
²⁸ አስቦ ከሠራው በደል ሁሉ ተመልሶአልና ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
²⁹ ነገር ግን የእስራኤል ቤት፦ የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም ይላል። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በውኑ መንገዴ የቀናች አይደለችምን? ይልቅስ የእናንተ መንገድ ያልቀናች አይደለችምን?
³⁰ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
³¹ የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ?
³² የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።
40 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 05:41:58 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"

እንኳን በአተ ክረምት (ለክረምት መመግቢያ) ሁለተኛ ሳምንት (ዕለተ እሑድ) መታሰቢያ ቀን በሰላምና በጤና እግዚአብሔር አምላክ አደረሰን።

+ + +
የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "ይሠጠዎ ወይሰምዖ ጸሎቶ ለኵሉ በዘሰአሎ እግዚኣ ለሰንበት አምላክ ምሕረት ያርኁ ክረምተ በበዓመት ሰምዑ ቃሎ ደመናት። ትርጉም፦ የሰንበት ጌታ የምሕረት መገኛ እግዚአብሔር ለለመነው ሁሉ ጸሎቱን ሰምቶ ልመናውን ተቀብሎ የጠየቀውን ሁሉ ያደርግለታል። ክረምትን በየዓመቱ ይመልሳል፤ ያፈራርቃል። ደመናትም ድምፁን ሰምተው ትዕዛዙን በማክበር ጸንተው ይኖራሉ።

+ + +
በቅዱስ ያሬድ የዜማ ይትበሃል መሠረት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ወርኃ ክረምት በሦስት ዐበይት ክላት ይፈከላሉ፤ እነዚህም 1. በአተ ክርምት 2. ማዕከለ ክረምት 3. ፀአተ ክረምት ይባላሉ ለእነዚህ ደግሞ ለራሳቸው ንዑሳን ክፍሎች አሏቸው።

+ + +
1 በአተ ክረምት፦ የሚባለው ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 19 ያለው ወቅት ነው። በዚህ ወቅት ዝናምና ደመና ምድርን የሚያለመልሙበት፣ ዘር የሚዘራበት፣ የተዘራው የሚበቅልበት በፀሐይ ሐሩር የደረቁ ዛፎች ሁሉ ማቆጥቆጥ የሚጀምሩበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘርን፣ ደመናን፣ ዝናምንና ልምላሜን የሚዘክሩ ምንባባት ይነበባሉ፣ መዝሙራትም ይዘመራሉ።

ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ ወርኃ ክረምት እግዚአብሔር ፍጥረቱን የሚመግብበት ገበታ መሆኑን ሲናገር "ያርኁ ለነ ክረምተ ይገብር ለነ ምሕረተ ንሴብሕ ወንዜምር ለዘወሀበነ ዝናም ወጸገወነ ሰላም። ለእኛ ክረምትን ይከፍትልናል፣ ምሕረትንም ያደርግልናል ሰላምን ያደለን ዝናምን የሰጠን፤ እግዚአብሔር ፈጽመን እናመስግን"። ሲል ይመሰክራል። የሰማይ መስኮቶች የሚከፈቱት ዝናማት ጊዜውን ጠብቀው የሚዘንሙት በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሆኑን አምነን በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበውን ጌታ ማመስገን ይገባል።

ዳግመኛ ሊቁ እንዲህ አለ "የዐርጉ ደመናት እምአጽናፈ ምድር የዐርጉ ደመናት ለጊዜ ዝናም አርአየነ እግዚኦ ሣህለከ ወሀበነ አድኅኖተከ ከመ ይኅድር ስብሐቲሁ ውስተ ምድርነ። ደመናት ከምድር ዳርቻ ይወጣሉ፤ ደመናት በዝናም ጊዜ ይወጣሉ፤ አቤቱ ይቅርታህንና ምሕረትህን አሳየን ግለጥልን፤ ማዳንህን ስጠን፤ ክብሩ ምስጋናው በረከቱ በምድራችን ውስጥ ይኖር ዘንድ"። በማለት ተንቀሳቃሽ ሆድ ያለው ፍጡር ሁሉ በልቶ ማደሩ ጠግቦ መኖሩ የቸርነቱ ውጤት እንደሆነ ሊቁ መስክሯል። ድጓ ዘክረምት።

በዚህ ክፍል ውስጥ ሦስት ንዑሳን ክፍሎች አሉ እነርሱም፦ ሰሙነ ዘርእ፣ ሰሞነ ደመናና ሰሙነ መባርቅት ናቸው። ምንጭ፦ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ ፪ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

+ + +
የዕለቱ ምስባክ፦ "አርውዮ ለትለሚሃ። ወአሥምሮ ለሚእረራ። ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ። መዝ 64፥10። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 6፥7-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥8-15 እና ግብ፡ሐዋ 14፥8-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥1-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቅዱስ ቄርሎስ የዕረፍት በዓል፣ ዕለተ ሰንበትና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
47 viewsedited  02:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:30:35
47 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:30:35 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"

+ + +
"ሰላም ለቄርሎስ ወልደ አንበሳ ጽኑዕ፤ ነባቢ ምስጢረ ሥላሴ ቅድስት፤ ዘተናገረ ላዕለ መለኮት"። ትርጉም፦ በመለኮት ላይ የተናገረ፤ የቅድስት ሥላሴን ምስጢርን ተናጋሪ፤ ብርቱ (ጠንካራ) ለኾነ ለአንበሳው ልጅ ለቄርሎስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
46 viewsedited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:30:35
37 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:30:35 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"

ሐምሌ ፫ (3) ቀን።

እንኳን ለእስክድርያ ሃያ ሊቀ ጳጳስ ለአምደ ሃይማኖት ለታላቁ አባት ለአቡነ ቄርሎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልና ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ ለነበረው ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት ለአባ ክልስቲያኖስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።

+ + +
አባ ቄርሎስ፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ (ለግብጽ) ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ ነው። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው በአባ ቴዎፍሎስ ዘንድ አደገ፤ ጥቂት ከፍ ባለ ጊዜም ወደ አስቄጥስ ወደ መቃርስ ገዳም ላከው በዚያም አምላካውያን የሆኑ መጻሕፍትን ተማረ እግዚአብሔርም መጽሐፍትን አንድ ጊዜ አንብቦ እስከሚአጸናው ድረስ ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጠው።

ከዚህም በኋላ ደግሞ ያስተምረው ዘንድ ለአባ ሰራብዮን ሰጠው ከእርሱም ዘንድ ያለውን ትምህርትን በፈጸመ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ መለሰው። እርሱም እጅግ ደስ ተሰኘበት እግዚአብሔርንም አመሰገነው።

ከዚህም በኋላ ሁል ጊዜ መጻሕፍትን እንዲያነብና ሕዝቡን እንዲያስተምር ለሊቀ ጵጵስና ሥራ ውስጥ ሾመው። ከትምህርቱም ጣዕም የተነሣ ዝም ይል ዘንድ ማንም አይወድም ነበር።

አባ ቴዎፍሎስ በዐረፈ በኋላ በእስክንድርያ ከተማ ላይ ይህን አባ ቄርሎስነ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም በትምህርቱ ቤተ ክርስቲያን በራች። ይኸው አባት ቄርሎስ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ንስጥሮስ በካደ ጊዜ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ማኅበርን በኤፌሶን ከተማ ሰበሰበ። ይህ አባት ቄርሎስን መረጠው ሊቀ ጉባኤ አደረጉት ንስጥሮስንም ተከራከረው ስህተቱንም ገለጠለት ከስህተቱም ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ከመንበረ ሲመት አሳደዱት።

ይህም አባት ቄርሎስ አሥራ ሁለት አንቀጾችን ደረሰ። በውስጣቸውም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ። ከዚህም በኋላ ግን ብዙዎች ድንሳናትን ተግሳጻትንና መልእክቶችን ደረሰ። እሊህም በሁሉ ቦታ በመምእመናን እጆች ይገኛሉ።

ይህም አባት ቄርሎስ እግዚአብሔር ቃል ከትሥብእቱ ጋራ ከተዋሐደ በኋላ በሥራ ሁሉ በምንም በምን የማይለያይ አንድ አካል አንድ ባሕሪይ እንደሆነ አስረዳ። ይህም አባት ቄርሎስ ሃይማኖታቸው ከቀና ከሦስት መቶ አሥራ ስምንት አባቶ ሃይማኖት ወጥተው ክርስቶስ ወደ ሁለት የሚከፍሉት መናፍቃንን ሁሉንም አውግዞ ለያቸው።

ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ መልካም የሆነው ሥራውም ፈጽሞ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቄርሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን።

+ + +
የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ክልስቲያኖስ፦ ይህ አባ ዮናክንዲዮስ በሚያርፍበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ክልስቲያኖስን ሊቀ ጵጵስና እንዲሾሙት አዘዘ እርሱንም አባ ክልስቲያኖስን "በሮሜ አገር ነጣቂ ተኩላዎች አሉና ልጄ ሆይ ተጠበቅ" ብሎ አዘዘ።

ከዚህም በኋላ አባ ዮናክንዲዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ክልስቲያኖስን በእርሱ ፈንታ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በዚያ ወራት ደግ ንጉሥ አኖርዮስ ነበር ከእርሱም በኋላ አመጸኛ ሉልያኖስ ነገሠ እርሱም ክርስቲያኖስን ከመንበሩ አሳድዶ መናፍቁን ንስጥሮስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው። የከተማ ሰዎች ግን አባረሩት እንጂ አልተቀበሉትም በከሀዲው ንጉሥም ልብ በክርስቲያስ ላይ ቂም ነበረ ሊገድለውም ይሻ ነበር። እርሱ አባ ክልስቲያኖስ ግን በሮሜ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በንዱ ገብቶ ኖረ እግዚአብሔርም ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቹ ያደርግ ነበር።

ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጦርነት ሆደ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤልን ለክልስቲያኖስ ተገለጠለት ወደ አንጾክያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ድምትርያኖስ ይሔድ ዘንድ አዘዘው "በዚያም ኑር" አለው። "ንጉሡ ከጦርነት እንደተመለሰ ይገድልህ ዘንድ በልቡ አስባልና"። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ከዚያ ገዳም ወጣ ከእርሱም ጋራም ሁለት መነኰሳት ነበሩ ወደ አንጾኪያ ከተማ ወደርሶ ቅዱስ ድምትርያኖስ አገኘው ከአመጸኛው ንጉሥም የደረሰበትን ሁሉ ነገረው እርሱም በአንጾኪያ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም አኖረው።

ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሊቃ ጳጳሳት አግናጥዮስና ዮናክንዲዮስ በሌሊት ዕራይ ለንጉሡ ተገለጡለት ከእርሳቸውም ጋራ የነበረው አንዱ እጅግ የሚያስፈራና ግሩም ነበር። እርሱም ንጉሡን እንዲህ አለው "ሊቀ ጳጳሳቱን ክልስቲያኖስን አገሩን ለምን አስተውከው እነሆ እግዚአብሔር ነፍስህን ከአንተ ይወስዳል በጠላቶችህም እጅ ትሞታለህ"። ንጉሥም ጌታዬ "ምን ላድርግ" አለው እነዚያም ሁለትም አባቶች "በእግዚአብሔር ልጅ ሕማም በመቀበሉ ታምናለህን" ብለው መለሱለት "እኔ አምናለሁ" አላቸው "ዳግመኛም መልእክትን ልከህ ልጃችን ክልስቲያኖስ ወደ መንበሩ መልሰው" አሉት።

ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ መልክትን ጽፌ ወደ ድምትራያኖስ እንዲህ ብሎ ላከ "ስለ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ በእኔ ላይ አትዘን ወደ መንበረ ሲመቱ ይመልሱት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ ያለበትን በመላእክተኞቼ ታመላክታቸውና ታደርሳቸው ዘንድ እለምንሀለሁ"። መልአክተኞችም በሔዱ ጊዜ አገኙትና መለሱት ሕዝቡም በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ተቀበሉት በዚያም ወራት ንጉሡ ከጦርነት በደና ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም በዕረፍትና በሰላም ኖረች።

የንስጥሮስም ክህደቱ በተገለጠ ጊዜ በእርሱ ምንክያት አንድነት ያላቸው ማኅበር ተሰበሰቡ ይህ አባት ክልስቲያኖስ በደዌውና በእርጅናው ምክንያት ወደ ጉባኤው መምጣት አልተቻላቸውም ነገር ግን ንስጥሮስን ከሚያወግዝ ደብዳቤ ጋር ሁለት ቀሳውስትን ላከ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው በፈቀደ ጊዜ ዮናክንዲዮስና አትናስዮስ ተገለጡለት እንዲህም አሉት "ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት ጠርተሀልና አንተ ወደ እኛ ስለምትመጣ አስጠንቅቃቸው" አሉት። ከእንቅልፉ ነቅቶ ወገኖቹን ጠራቸው እንዲህም አላቸው "ተኩላዎች ወደዚች ከተማ ይገቡ ዘንድ አላቸውና ተጠንቀቁ"።

ይህንም ከተናገረ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አለ "እንነሳና እንሂድ እነሆ ቅዱሳን ይሹኛልና ሁለቱ ሌሎች ናቸው በዚችም ሰዓት በዚች ዓለም በአንድነት እንወጣለን እነርሱም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስና የፃን አገር ኤጲስቆጶስ ሉቅያስ ናቸው" ይህንንም ብሎ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 3 ሰንክሳር።

+ + +
"ሰላም ለቄርሎስ ለቃለ መጻሕፍት ዘዴገኖ። ቴዎፍሎስ ድኅረ ሐፀኖ ሊቀ ማኅበር ከዊኖ፡፡ ሃይማኖተ ንስጡር ለተቃርኖ፡፡ መሰለ ፀምረ መለኮተ ዘጥምዐተሕብር ከደኖ። ወትስብእተ በኀፂን ዘእሳት አርሰኖ"። ትርጉም፦ የማኅበር አለቃ ኾኖ ቴዎፍሎስ ካሳደገው በኋላ የመጻሕፍትን ቃል የተከተለ ለኾነ ለቄርሎስ ሰላምታ ይገባል፤ የንስጥሮስን የክሕደት እምነት ለመቃወም መለኮትን ቀለም በሸፈነው ፀምር፤ ትስብእትንም እሳት ባጋለው በብረት መሰለው። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ3።
55 viewsedited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:30:35
51 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:09:49
65 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ