Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ማለዳ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionews55 — ዜና ማለዳ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionews55 — ዜና ማለዳ
የሰርጥ አድራሻ: @ethionews55
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 472
የሰርጥ መግለጫ

ባሉበት ሆነው መረጃ ያግኙ ኣለም አቀፍ እና የሐገር ውስጥ ዜና ይዳሰስበታል አስትያየት በተለይ ጥቆማ ካልችሁ ቀጥሎ ባለው ሊንክ ይላኩልን @saruti97 ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ እንሆናለን

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-09 21:48:51 ETHIOPIA

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በማሸነፏ ፤ ማላዊ ደግሞ በጊኒ በመሸነፏ ምድቧን በአንደኛነት መምራት ጀምራለች።

ጊኒ እና ማላዊ ያደረጉት ጨዋታ ጊኒ 90+1' ደቂቃ ላይ በሊቨርፑሉ ተጫዋች ኬታ ባስቆጠረችው ጎል 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች።
@ethionews55
@Ethionews55
275 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 16:26:21 ብሔራዊ ባንክ የመመስረቻ መስፈርቱን ላሟሉ ስምንት ባንኮች ፈቃድ ሰጠ።

በብሔራዊ ባንኩ የባንክ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው በፋይናንስ ዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን ተከትሎ በርካታ ባንኮች የመመስረቻ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም ባንክ ለመመስረት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒል መጠንን ከ500 ሚሊዮን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ ማድረጉን አስታውሰው አጠቃላይ መስፈርቱን ላሟሉ ፈቃድ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚህ መሰረት የመመስረቻ ፈቃድ ከጠየቁ 25 አዳዲስ ባንኮች መካከል ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መስፈርት አሟልተው ለተገኙ ስምንት ባንኮች ፈቃድ መስጠቱን ተናግረዋል።

በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ካገኙ ስምንት ባንኮች በተጨማሪ ሦስት ባንኮች ፈቃድ የማግኘት ሂደቱን እያጠናቀቁ ሲሆን ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚያገኙ ገልጸዋል።

ብሔራዊ ባንክ ከቅድመ ማመልከቻ ሂደት ጀምሮ ፈቃድ ከተሰጠ በኋላ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጸው የምስርታ ሂደቱ ካልተሳካ ለባለአክሲዮኖች ገንዘባቸው ተመላሽ ይሆናል ብለዋል።

በተመሳሳይ አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ወደ ባንክ እንዲሸጋገሩ በ2012 ዓ.ም ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ ሦስት አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ወደ ባንክ መሸጋገራቸውን ገልጸዋል። (ENA)
@ethionews55
@Ethionews55
309 views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 12:11:15 "የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኹሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ ያደርጋል ብለን እናስባለን" የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ
ሰኔ 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኾነው የተሾሙት አምባሳደር ሽብሩ ማሞ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ አቅርበዋል።
አምባሰደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅትም የኹለቱን ሀገራት የረጅም ዘመናት ግንኙነትና ቀጣይ የትብብር መስኮችን በሚመለከት ከፕሬዝዳንቷ ጋር ሐሳብ ተለዋውጠዋል።
አምባሳደር ሽብሩ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና መንግሥት እየወሰዳቸው ስላለው እርምጃ እንዲሁም ስለ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለፕሬዝዳንቷ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
በታንዛኒያ እስር ቤት በአስከፊ ችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱም አምባሳደሩ ለፕሬዝዳንቷ ጥያቄ አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንትሳሚያ ሱሉሁ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታና በአምባሳደሩ ስለቀረበላቸው ገላጻ ምሥጋና አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ችግር ለመፍታት መንግሥት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚያደንቁም ተናግረዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በሚመለከትም ግድቡ ኹሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት መኾኑንም መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በአዲስ አበባ የሚገኘውን የታንዛኒያ ኤምባሲ መሬት ጉዳይ በቅርብ መፍትሔ እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ የኹለቱ ሀገራት ግንኙነት ዘመን በማይሸር ወዳጅነት የተሳሰረ በመኾኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በታንዛኒያ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ዜጎች እንዲለቀቁና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ መንግሥታቸው ቀና ውሳኔ እንደሚሰጥበትም አረጋግጠዋል።
ፕሬዚዳንት ሳሚያ የታንዛኒያ ዜጎች ኢትዮጵያ በአቬየሽን ዘርፍ ሥልጠና እየወሰዱ መኾናቸውን አስታውሰዋል። ለዚህም ኢትዮጵያ በዘርፉ ሙያ የአፍሪካ ተምሳሌት መኾኗን በመጥቀስ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
@Ethionews55
@ethionews55
261 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 21:15:24 የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት በቀጣዮቹ ዓመታት ጦርነት ቆሞ ሰላም እንደሚሰፍን ዘመኑም መልሶ ግንባታ ላይ ትኩረት የሚደረግበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የቀጣዩን አመት በጀት አስመልክቶ ባቀረቡት የበጀት መግለጫ እንደገለፁት ሰላም ሰፍኖ ኢኮኖሚው ከተግዳሮቶች የተላቀቀና ለቀጣይ የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋት ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠር ታሳቢ ተደርጓል ብለዋል።በዚህም ኢኮኖሚው ከነበረበት ችግሮች በማገገም በ2015 በ9.2 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ግምት መያዙን ገልፀዋል።የፌደራል መንግስት አጠቃላይ የ2015 በጀት 786.6 ቢሊየን ሆኖ የቀረበ ሲሆን በጀቱ ከአምናው አንጻር የ16.6 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተነግሯል።ከምክርቤቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ረቂቅ በጀቱ ለአንድ ወር ያህል የተለያዩ ውይይቶች ተደርገውበት በሰኔ 2014 መጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
@ethionews55
@Ethionews55
243 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 16:22:50 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2015 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ

ከ2014 በጀት ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የብር 111.94 ቢሊዮን ወይም የ16.59 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2015 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
view Bbc
@ethionews55
@ethionews55
372 views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 16:10:53 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶች ሰጥተዋል።

በዚሁ መሰረት፣
1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር

2. አቶ ካሊድ አብዱራህማን - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል

3. አቶ ወንድሙ ሴታ - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

4. አቶ ሄኖስ ወርቁ - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምከትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም የሚከተሉት ሸመቶች እንዲጸድቁ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቀዋል

1. ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር

2. አቶ አበራ ታደሰ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

@Ethionews55
@ethionews55
342 views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 19:12:10 የሀገራችንን መጥፋት የሚፈልጉ ሁሉ የጥፋት ዕቅዳቸው ወኪል አድርገው እንዲወስዱን ልንፈቅድ አይገባም

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

የሀገራችንን መጥፋት የሚፈልጉ ሁሉ የጥፋት ዕቅዳቸው ወኪል አድርገው እንዲወስዱን ልንፈቅድ አይገባም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡
እንደ ህዝብ ልዩነቶቻችንን አምነን ተቀብለን በብዙ ትውልዶች ዕድሜ በኁባሬ ተሣሥረን ኖረናል።

በጋራ ስፌታችን ውስጥ መቻቻል አንዱ አስፈላጊ ሰበዝ ነው።
እንደ አንድ ሕዝብ፣ የሀገራችንን መጥፋት የሚፈልጉ ሁሉ፣ የጥፋት ዕቅዳቸው ወኪል አድርገው እንዲወስዱን ልንፈቅድ አይገባም።

በአንዳንድ ማኅበረሰቦች ውስጥ እንዲሆን የምንፈቅድለት ክፋት ከእርስ በርስ ተዛምዷችን ጋር ካለው ቅርበት ይልቅ ለሌሎች የጥፋት ወኪሎች መጠቀሚያ የሚሆን ነው።

በማኅበረሰባችን ውስጥ የአስተዋዮችን ልቡና እንፈልግ እና ልዩነቶችን ከማጉላት ይልቅ ለማቀራረብ እንሥራ።
የምንጋራው ሰብአዊነት ይህንን እንድናደርግ ያስገድደናል።

ማንንም ለማጥፋት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ ጥቃት በሁላችን ላይ የሚደረግ ነው።
አጥፊውን አውግዘን ከተጠቂው ጋር እንቆማለን እንጂ ጥፋቱን በሌላ ጥፋት ለማባባስ መሞከር የለብንም።
ከኢትዮጵያ ሰላም እንጂ ከኢትዮጵያ ሑከት ማናችንም አናተርፍም።

@Ethionews55
@Ethionews55
692 views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 22:03:56 ከአሸባሪው የህወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰላምንና ጸጥታን ለማስፈን ሲባል ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ታወጀ

በአስችኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ ቁ.4 እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻዉን ባደረገው ስብሰባ የዐዋጁን አፈጻጸም ገምግሟል። በግምገማውም አዋጁን በመፈጸም ረገድ የሕዝቡ ተነሣሽነትና ቆራጥነት የሚደነቅ በመሆኑ ምስጋና አቅርቧል። ያገኘናቸውን ድሎች ጠብቆ ለማስቀጠል እንዲቻልም የሚከተሉትን ትእዛዞች አስተላልፏል።

1
ከአሸባሪው የሕወሐት እጅ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰላምንና ጸጥታን ለማስፈን እንዲሁም የሕዝብንና የንብረትን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ታውጇል።

2
ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች የታወጀውን የሰዓት እላፊ በተመለከተ ወደ አካባቢው የገቡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ፤ እንዲሁም የሰዓት እላፊውን እንዲያስፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷል።

3
ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ መንግሥት ከሚመደብ ሲቪል አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲቋቋም። በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት በአሸባሪው ወራሪ ኃይል በመንግሥት ተቋማት፣ በግለሰብ ንብረቶች፣ በማኅበራዊ ተቋማትና በመሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመትን የሚያሳዩ ማስረጃዎች እንዳይጠፉ እንዲጠበቁ፣ በተገቢው መንገድ እንዲመዘገቡ፣ ማስረጃዎችም እንዲሰነዱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዙ ትእዛዝ ሰጥቷል።

4
የፍትሕ አካላት በየቦታው ከተቋቋሙ ጥምር ኮሚቴዎች ማስረጃዎችን ተቀብለው በማደራጀት ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡ ታዝዟል።

@Ethionews55
@Ethionews55
1.7K viewsedited  19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 21:51:33 #BREAKING

ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " የጋሸናን ግንባር ምሽጎችን በመሰባበር የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጥረዋል " ብሏል።

በአሁን ሰዓት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው ሲልም አሳውቋል።
@ethionews55
@ethionews55
1.2K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 19:48:03 እልልልልልልልልል በይ ሃገሬ ደስታችንን ያዝልቅልን።
@ethionews
1.1K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ