Get Mystery Box with random crypto!

የብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ 86ኛ ዓመት መታሰብያ ዝክር ላይ መገኘት በመቻሌ የተሰማኝ ደስታ ከፍተኛ ነው | Henok Abayneh Gebrehiwot

የብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ 86ኛ ዓመት መታሰብያ ዝክር ላይ መገኘት በመቻሌ የተሰማኝ ደስታ ከፍተኛ ነው። በርቀት የሚመለከቱትን ትዕይንት በአካል መታደል ዓለም ነው። የነፍስን አቅል ያስታል። '' የመጨረሻውን ቃል ለጀግናው ተውለት'' እንዲሉ አቡነ ጴጥሮስ በጥቂት ቃላቸው የሀገርን ፍቅርን ፣ ሀይማኖትን ፣ አርበኝነትን ፣ አባትነትን ቋጥረው ለታሪክ አልፈዋል። ለትውልድ ስላለፉ ፤ ትውልድ ይዘክራቸዋል። የጊዜው ትውልድ አካል ነንና ስንዘክራቸው በሙሉ ተድላ ነው።

አዎ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
ምጸናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሰጋሁ!"

­­­– ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኀን