Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተከሰተው አሳዝኝ ዜና ብዙዎችን ሲያሳዝን ቆይቷል። የወጣት ኢየብን ህይወት | Henok Abayneh Gebrehiwot

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተከሰተው አሳዝኝ ዜና ብዙዎችን ሲያሳዝን ቆይቷል። የወጣት ኢየብን ህይወት መመለስ ባንችልም በተቻለን አቅም ለቤተሰቦቹ በመረባረብ እገዛ እናድርግ።

ሰሞኑን አዲስ ክፍለ ከተማ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ሳቢያ ግንብ ተደርምሶ የሰዎች ህይወት አልፏል። በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት አንዱ ወጣት ኢዮብ ወልደማርያም ሲሆን የሞተበት ሰብአዊነትን የተላበሰ ሁኔታ ብዙዎችን አሳዝኗል። የሰው ህይወት ለማትረፍ ሲል የራሱን ህይወት እንዳጣም ቤተሰቦቹ ገልፀዋል።

በአደጋው መኖሪያ ቤቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት የሟች እዮብ ቤተሰቦችም አሁን ላይም ለቅሶ የተቀመጡት ቤተዘመድ እንዲሁም ጎረቤት ቤት ነው። በቀጣይም ማረፊያቸውን እንደማይታወቅ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

የኢዮብን ወላጆች ማገዝ ለምትፈልጉ በእናት ራውዳ ጀማል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት (CBE) 1000010020011 እና በአባት ወልደማርያም ሸዋ የባንክ አካውንት (CBE) 1000291553749 ማገዝ ትችላላችሁ። በስልክ እናት ራውዳ ጀማልን በ0911225960 እንዲሁም ደግሞ አባት ወልደማርያም ሸዋን በ 0911137825 ላይ ማግኘች ይችላል።

@henokpk @henokabayneh