Get Mystery Box with random crypto!

ቢኒያም ኢሳያስ ይባላል፤ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 5ኛ ዓመት | Henok Abayneh Gebrehiwot

ቢኒያም ኢሳያስ ይባላል፤ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 5ኛ ዓመት የሕክምና ተማሪ ነዉ ፤ በተፈጥሮ ምክንያት አካል ጉዳተኛ ቢሆንም፤ በራሱ ጥረት በሕክምና ትምህርት እስከ 5ኛ ዓመት በትጋት ተምሩዋል፡፡ በህክምናው ያለው ውጤት CGPA 3.8 ነው።

ነገር ግን ሊመረቅ የሁለት ዓመት ጊዜ ሲቀረዉ ትምህርቱን መቀጠል እንደማይችልና ማቋረጥ እንዳለበት ዉሳኔ ከተቋሙ ይተላለፍበታል። እንደ ምክንያት የቀረበው ሀሳብ ተማሪው አካል ጉዳተኛ ስለሆነ ትምህርቱን በአግባቡ መውጣት እንደሚቸግረውና ትምህርቱን አቁሞ ሌላ ትምህርት መጀመር አለበት የሚል ነው። ይህ የስላቅ ምክንያት ከጅምሩ ያልተነሳ በማምሻው ላይ የተነሳ ጥያቄ መሆኑን ልብ ይሏል። በመደምደሚያው ጊዜ ይህን ማንሳት ምን አይነት ህሊና ቢስነት ነው ? የተማሪው ሞራል ፣ ድካም ፣ ችሎታ ከግምት ገብቷል ?

ይህ የመብት ጥሰት የአንድ ተማሪ ብቻ ሳይሆን የብዙ አካል ጉዳተኞች ነው ፤ ስለሆነም ይህ ልጅ በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታዉ እንዲመለስ በአፅንኦት እንጠይቃለን። በማስረጃ የተደገፈ የህግ ድጋፍ አለው። ይህ ተግባርም ጥቁር አንበሳን ከመሰለ አንጋፋ ተቋም ማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት ነው።

@henokpk @henokabayneh