Get Mystery Box with random crypto!

የእግዚአብሔር ወንጌል

የቴሌግራም ቻናል አርማ gospel_of_god — የእግዚአብሔር ወንጌል
የቴሌግራም ቻናል አርማ gospel_of_god — የእግዚአብሔር ወንጌል
የሰርጥ አድራሻ: @gospel_of_god
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.04K
የሰርጥ መግለጫ

𝘍𝘰𝘳 𝘢𝘯𝘺 𝘘𝘶𝘦𝘴𝘵𝘪𝘰𝘯𝘴 𝘰𝘳 𝘚𝘶𝘨𝘨𝘦𝘴𝘵𝘪𝘰𝘯𝘴 𝘶𝘴𝘦፡
@pray_trust_wait0

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-04 12:19:07 ኀጢአተኛውና ጎስቋላው ሰው በክርስቶስ ፍጹም ስራ ነው የዳነው ። ከኀጢያቱ እድፈትም የነጻው ህያው ሆኖ በቀረበው መስዕዋት በክርስቶስ ደም ነው ። ተስፋቢስና በጨለማ ለነበረው ሰው ታላቅና ጽኑ ተስፋ ፣ የማይደበዝዝን ብርሃን ያገኘው በክርስቶስ ቤዝዎት ነው ። ነፍሱን በኀጢያት ገመድ ጠፍሮ ወደሞት ከሚነዳበት ከዚያ የጭንቅ ህይወት ያለአንዳች የራሱ አስተዋዕጾ እንዲያው በጸጋ ነው የዳነው ! የጠፋውን ፍለጋ የባሪያውን መልክ ይዞ ወደ ምድር የመጣው ጌታ ነው ፣ አስቀድሞ የወደደው ፣ ኀጢአተኛውን ሊያድነውም የመጣው ጌታ ነው ። ከዚያ ታላቅ ያ'ምላክ ቁጣ ያዳነው ራሱን በባሪያም ምትክ አኑሮ የኀጢያት በደሉን ቅጣት እስከሞት በሆነ ታላቅ ስቃይ ወስዶለት ነው ። የዚያን ጎስቋላ ሰው ኃፍረት ይሸፍንለት ዘንድ በአለም አደባባይ ርቃኑን በእንጨት መስቀል ተሰንጠልጥሎ ታየለት ። ሁሉን የፈጠረ ጌታ ለደካማው ሰው ነፍስ በፈጠራቸው እጅ ዝቅ ብሎ ተሰጠ ። ፍጡራን በፈጣሪ ላይ አላገጡ አፌዙበት ፤ በክፋታቸው ሚዛን ላይ ሰፍረውት ሊገዙትና ሊሸጡት ተመኑ ። ሁሉን ስለጎስቋላው ሰው ነፍስ ታገሰ ፣ ሁሉን ስለወደዳት ነፍስ ተቀበለ ፣ ሁሉን ስለፍቅር ተሸከመው ።

የዚያ ጎስቋላ ሰው ነፍስ ጽኑውና ብርቱው ተስፋዋ የአዳኟ ዳግም ምጽዓት ነው !

__

በጻድቅ ሰው ደም ከኀጢያታችን የዳንን ጎስቋሎች እኛ ነን !

#በጸጋው_ድነናል !

Have a nice Lord's day !
252 views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 11:17:53 ስድስት የማይቀሩ ነገሮች
1- ሕይወት አጭር ናት።
2- ሞት ኣይቀርም።
3- ከፍርድ ማምለጥ ኣይቻልም።
4- ኃጢአት እጅግ አስቀያሚ ነው።
5- ሲዖል እጅግ አስፈሪው እውነታ ነው።
6 - ሊያድን የሚችል ክርስቶስ ብቻ ነው።

       __ጄሲ ራይል

@Gospel_of_God @Gospel_of_God
@Gospel_of_God @Gospel_of_God
629 views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 22:28:15 ኢየሱስ በአጽናፉ ታሪክ አንድ ጊዜ ብልጭ ብሎ የከሰመ ብርሃን ሳይሆን ብርሃናት ሳይፈጠሩ በፊት ያለ: ብርሃናት ከጠፉ በኅላም የሚኖር ዘላለማዊ ብርሃን ነው!

__Alex Zetsa'at

@Gospel_of_God @Gospel_of_God
@Gospel_of_God @Gospel_of_God
1.3K views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 10:58:05 "እኛ ስለራሳችንን ማስታወስ ያለብን እግዚአብሔር የሚወደን የምንወደድ ስለሆንን ሳይሆን በክርስቶስ ስላለን ነው። እኛ በክርስቶስ ስላለን አብም ለልጁ ያለው ፍቅር በእርሱ በኩል ወደ እኛ ይፈሳል።"

    __JERRY BRIDGES

@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
1.5K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 09:41:32 "መዳንህ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ውሳኔ ላይ ያረፈ ሲሆን፥ በጸጋው ምህረቱን ሊያደርግልህ ስወስንም ባንተ ላይ ስላየው ነገር ሳይሆን፥ በልጁ ፍቅር ስላየው ነው። ክርስቲያን መሆኔም ከአብ የወልድ ስጦታ ከመሆኔ በስተቀር ከሰማይ በታች ያደረግሁት ምክንያት ወይም ላደርገው የምችለው ነገር ስላለ አይደለም።"
    
   __Robert Charles Sproul

@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
995 viewsedited  06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 20:24:56 "እግዚአብሔር በህይወቴ ያለው አላማ ለእርሱ ክብር የጋላ ፍቅር እንድኖረኝ እና በዚያም ክብር ደስታዬን እንዳገኝ ነው።
እናም እነዚህ ሁለቱ ነገሮች አንድ አምሮት ናቸው።"

    __Johnatan Edwards

@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
995 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 08:50:37 እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የተቃኙ የሕይወት ልምምዶቻችን በእግዚአብሔር ኃይል ተጠብቀን ተስፋ ያደረግነው የአዲሱ ሰው ሙላት ጥላ ናቸው። በበጎነት፣ በጽድቅና በእውነት ሁሉ የብርሃኑ ፍሬ ስታይብን፡ የአዲሱን ሰው ሙላት ጥላ እናጎላለን።

#Sabbath

@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
1.4K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 22:24:14 በብዙ ነገር ደክሜያለሁ ፤ ምን ሊያበረታኝ እንደሚችል አላውቅም ከድካሜ ወዲያ እማውቀው ያለ አይመስለኝም ። ትናንትን የኋሊት ሳየው መከፋት ደርሶ ነፍሴን ይረብባታል ፤ ነገን ሳስብ ደግሞ ምንም እሚታየኝ ተስፋ አላገኝም ፤ ከቀረኝ ዛሬውስ ስለትናንትናና ስለዛሬ እያሰብኩ እደክምበታለሁ ። እምደክምበት ምክንያት እልፍ ነው ለምን መላቀቅ እንዳልቻልኩ መረዳት እስኪሳነኝ ልቤ ዝሏል ። እምፈራው ነገር ቢሰደርና ስማቸውን ለመጥራት ብጀምር ከአንዱም አልዘልም እፈራቸዋለሁ ። ጓደኛ ሆኜ መቆየት ያስፈራኛል ፤ መውደድ ያደክመኛል እኔ ፍጹም የሆንኩ ይመስል የእነሱን ትንሽ ጥፋት ከመውደዴ አግዝፌ ጥያቸው ወደተለመደው የብቸኝነትና የድባቴ ጎጆዬ እመለሳለሁ። ጥሩ መሆን ይደክመኛል ፤ ጥሩነቴን አላወቁልኝም ሊረዱኝ አልቻሉም በሚል ምስጋናን የመቃረም መንገዴ ባዶ እጄን ሲሰደኝ ( attention seekerነቴ ) አግጥጦ ይወጣና ከንቱ መሆኔን ለኔው መስክሮ ያደክመኛል ። የኔው እንባ ለኔው ባዳ ሆኖ ሸሽቶኝ አይኔን እንዳላጥበው ይስቆነቆንብኛል ። መንገዴ ማለቂያ የለውም የሆነ ረዥም ነገር ነው ዳርቻው የማይታወቅን ሰማይን የመሰለ ..... መኖር ውሉ ምንድነው እሚል አንድ ገልቱ ጠያቂ ውስጤ ቱግ ብሎ ይነሳል ? መልሴን ፍለጋ ስማስን እንደገና እደክማለሁ .....


#እግዚአብሔር_አለ ! ይህ ብቻ ነው እውነት እሚያጽናናኝ !
723 views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 18:46:29 እግዚአብሔር፣ ኢ-ውሱን የቅርብ አምላክ

የእግዚአብሔር ኢ-ውሱንነትና ቅሩብነት (ይኽ የእርሱ ብቻ ነው)

እግዚአብሔር ሊገለጽ ከሚቻለው በላይ እጅግ የሁሉ ነገር የበላይና ከሁሉ ነገር ውጪ ነው። ማንኛውም ዓይነት ፍጡር ወደዚህ ግዙፍ ማንነቱ በፍጥነትም ይሁን በአዝጋሚ ሊመጣ አይችልም። የዚያኑ ያህል ከእኛ ከሰው ልጆች ጋር ደግሞ እዚህና አሁን ይስተጋበራል (ሪሌሽን) እኛም አካላዊ ፍጡራን ነንና ከእርሱ ጋር ኅብረት እናደርጋለን። ወደ እርሱ እንጸልያለን እርሱን አናመልካለን እንታዘዘዋለን እንወደዋለን፣ እርሱም እኛን ይናገራል፣ በእኛም ደስ ይለዋል ይህ የኢውሱኑ መስተጋብራዊ/ ግንኙነታዊ ባህርይ ከውሱኑ የሰው ልጅ ጋር መገናኘቱ መንፈሳዊ አካልነቱን ያሳያል።  ይህ ወሰን የለሹ ምጡቅ አምላክ ከእኛ ከውስኖቹ ጋር የሚገናኝበት መንፈሱን ስለሰጠን “አብ አባት” ብለን በተዋጀንበት የክርስቶስ ድፍረት በፊቱ እንቀርባለን።

የእግዚአብሔር ምጥቀት የዘላለማዊ ባሕርዩ ነው፣ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው ስንል ደግሞ “ሁልጊዜ” ማለታችን አይደለም የእግዚአብሔርን ዘላለማዊነት ስናስብ ጊዜ ቋንቋችን ውስጥ አይገባም። ጊዜ በእርሱ ማንነት ላይ፣ ፍጹምነት፣ ዓላማና ተስፋ ላይ ምንም ተጽእኖ አያመጣም፣ እርሱ አዲስን ነገር አይማርም፣ የሚያውቀውንም ነገር አይረሳም፤  “በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።” ያዕ 1:17 

እግዚአብሔር ሆይ በእውቀትህ ንዳን!

__በሳምሶን ጥላሁን

@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
1.5K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 08:07:36 "እውነተኛ ክርስቲያኖች ከሆንን ወደ መንግሥተ ሰማያት በምናደርገው ጉዞ ሁሉም ነገር ለስላሳ እንዲሆን መጠበቅ የለብንም። ልክ እንደሌሎች ሰዎች በሽታን፣ ኪሳራን፣ ሐዘንን እና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎችን መቋቋም እንደ እንግዳ ነገር ልንቆጥረው አይገባም። አዳኛችን በነፃ ይቅርታ በማድረግ በመንገዱ ላይ ላለው ፀጋን፣ በመጨረሻም ክብርን ሊሰጥ ቃል ገብቷል። ነገርግን ምንም ዓይነት መከራ እንደማይደርስብን ፈጽሞ ቃል አልገባልንም።"

__J.C. Ryle

#Sabbath

@Gospel_of_God @Gospel_of_God
@Gospel_of_God @Gospel_of_God
1.4K viewsedited  05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ