Get Mystery Box with random crypto!

በብዙ ነገር ደክሜያለሁ ፤ ምን ሊያበረታኝ እንደሚችል አላውቅም ከድካሜ ወዲያ እማውቀው ያለ አይመስ | የእግዚአብሔር ወንጌል

በብዙ ነገር ደክሜያለሁ ፤ ምን ሊያበረታኝ እንደሚችል አላውቅም ከድካሜ ወዲያ እማውቀው ያለ አይመስለኝም ። ትናንትን የኋሊት ሳየው መከፋት ደርሶ ነፍሴን ይረብባታል ፤ ነገን ሳስብ ደግሞ ምንም እሚታየኝ ተስፋ አላገኝም ፤ ከቀረኝ ዛሬውስ ስለትናንትናና ስለዛሬ እያሰብኩ እደክምበታለሁ ። እምደክምበት ምክንያት እልፍ ነው ለምን መላቀቅ እንዳልቻልኩ መረዳት እስኪሳነኝ ልቤ ዝሏል ። እምፈራው ነገር ቢሰደርና ስማቸውን ለመጥራት ብጀምር ከአንዱም አልዘልም እፈራቸዋለሁ ። ጓደኛ ሆኜ መቆየት ያስፈራኛል ፤ መውደድ ያደክመኛል እኔ ፍጹም የሆንኩ ይመስል የእነሱን ትንሽ ጥፋት ከመውደዴ አግዝፌ ጥያቸው ወደተለመደው የብቸኝነትና የድባቴ ጎጆዬ እመለሳለሁ። ጥሩ መሆን ይደክመኛል ፤ ጥሩነቴን አላወቁልኝም ሊረዱኝ አልቻሉም በሚል ምስጋናን የመቃረም መንገዴ ባዶ እጄን ሲሰደኝ ( attention seekerነቴ ) አግጥጦ ይወጣና ከንቱ መሆኔን ለኔው መስክሮ ያደክመኛል ። የኔው እንባ ለኔው ባዳ ሆኖ ሸሽቶኝ አይኔን እንዳላጥበው ይስቆነቆንብኛል ። መንገዴ ማለቂያ የለውም የሆነ ረዥም ነገር ነው ዳርቻው የማይታወቅን ሰማይን የመሰለ ..... መኖር ውሉ ምንድነው እሚል አንድ ገልቱ ጠያቂ ውስጤ ቱግ ብሎ ይነሳል ? መልሴን ፍለጋ ስማስን እንደገና እደክማለሁ .....


#እግዚአብሔር_አለ ! ይህ ብቻ ነው እውነት እሚያጽናናኝ !