Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔር፣ ኢ-ውሱን የቅርብ አምላክ የእግዚአብሔር ኢ-ውሱንነትና ቅሩብነት (ይኽ የእርሱ ብቻ | የእግዚአብሔር ወንጌል

እግዚአብሔር፣ ኢ-ውሱን የቅርብ አምላክ

የእግዚአብሔር ኢ-ውሱንነትና ቅሩብነት (ይኽ የእርሱ ብቻ ነው)

እግዚአብሔር ሊገለጽ ከሚቻለው በላይ እጅግ የሁሉ ነገር የበላይና ከሁሉ ነገር ውጪ ነው። ማንኛውም ዓይነት ፍጡር ወደዚህ ግዙፍ ማንነቱ በፍጥነትም ይሁን በአዝጋሚ ሊመጣ አይችልም። የዚያኑ ያህል ከእኛ ከሰው ልጆች ጋር ደግሞ እዚህና አሁን ይስተጋበራል (ሪሌሽን) እኛም አካላዊ ፍጡራን ነንና ከእርሱ ጋር ኅብረት እናደርጋለን። ወደ እርሱ እንጸልያለን እርሱን አናመልካለን እንታዘዘዋለን እንወደዋለን፣ እርሱም እኛን ይናገራል፣ በእኛም ደስ ይለዋል ይህ የኢውሱኑ መስተጋብራዊ/ ግንኙነታዊ ባህርይ ከውሱኑ የሰው ልጅ ጋር መገናኘቱ መንፈሳዊ አካልነቱን ያሳያል።  ይህ ወሰን የለሹ ምጡቅ አምላክ ከእኛ ከውስኖቹ ጋር የሚገናኝበት መንፈሱን ስለሰጠን “አብ አባት” ብለን በተዋጀንበት የክርስቶስ ድፍረት በፊቱ እንቀርባለን።

የእግዚአብሔር ምጥቀት የዘላለማዊ ባሕርዩ ነው፣ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው ስንል ደግሞ “ሁልጊዜ” ማለታችን አይደለም የእግዚአብሔርን ዘላለማዊነት ስናስብ ጊዜ ቋንቋችን ውስጥ አይገባም። ጊዜ በእርሱ ማንነት ላይ፣ ፍጹምነት፣ ዓላማና ተስፋ ላይ ምንም ተጽእኖ አያመጣም፣ እርሱ አዲስን ነገር አይማርም፣ የሚያውቀውንም ነገር አይረሳም፤  “በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።” ያዕ 1:17 

እግዚአብሔር ሆይ በእውቀትህ ንዳን!

__በሳምሶን ጥላሁን

@Gospel_of_God   @Gospel_of_God
@Gospel_of_God   @Gospel_of_God