Get Mystery Box with random crypto!

ኀጢአተኛውና ጎስቋላው ሰው በክርስቶስ ፍጹም ስራ ነው የዳነው ። ከኀጢያቱ እድፈትም የነጻው ህያው | የእግዚአብሔር ወንጌል

ኀጢአተኛውና ጎስቋላው ሰው በክርስቶስ ፍጹም ስራ ነው የዳነው ። ከኀጢያቱ እድፈትም የነጻው ህያው ሆኖ በቀረበው መስዕዋት በክርስቶስ ደም ነው ። ተስፋቢስና በጨለማ ለነበረው ሰው ታላቅና ጽኑ ተስፋ ፣ የማይደበዝዝን ብርሃን ያገኘው በክርስቶስ ቤዝዎት ነው ። ነፍሱን በኀጢያት ገመድ ጠፍሮ ወደሞት ከሚነዳበት ከዚያ የጭንቅ ህይወት ያለአንዳች የራሱ አስተዋዕጾ እንዲያው በጸጋ ነው የዳነው ! የጠፋውን ፍለጋ የባሪያውን መልክ ይዞ ወደ ምድር የመጣው ጌታ ነው ፣ አስቀድሞ የወደደው ፣ ኀጢአተኛውን ሊያድነውም የመጣው ጌታ ነው ። ከዚያ ታላቅ ያ'ምላክ ቁጣ ያዳነው ራሱን በባሪያም ምትክ አኑሮ የኀጢያት በደሉን ቅጣት እስከሞት በሆነ ታላቅ ስቃይ ወስዶለት ነው ። የዚያን ጎስቋላ ሰው ኃፍረት ይሸፍንለት ዘንድ በአለም አደባባይ ርቃኑን በእንጨት መስቀል ተሰንጠልጥሎ ታየለት ። ሁሉን የፈጠረ ጌታ ለደካማው ሰው ነፍስ በፈጠራቸው እጅ ዝቅ ብሎ ተሰጠ ። ፍጡራን በፈጣሪ ላይ አላገጡ አፌዙበት ፤ በክፋታቸው ሚዛን ላይ ሰፍረውት ሊገዙትና ሊሸጡት ተመኑ ። ሁሉን ስለጎስቋላው ሰው ነፍስ ታገሰ ፣ ሁሉን ስለወደዳት ነፍስ ተቀበለ ፣ ሁሉን ስለፍቅር ተሸከመው ።

የዚያ ጎስቋላ ሰው ነፍስ ጽኑውና ብርቱው ተስፋዋ የአዳኟ ዳግም ምጽዓት ነው !

__

በጻድቅ ሰው ደም ከኀጢያታችን የዳንን ጎስቋሎች እኛ ነን !

#በጸጋው_ድነናል !

Have a nice Lord's day !