Get Mystery Box with random crypto!

Gojo Bridge Housing

የቴሌግራም ቻናል አርማ gojo_bridgehousing — Gojo Bridge Housing G
የቴሌግራም ቻናል አርማ gojo_bridgehousing — Gojo Bridge Housing
የሰርጥ አድራሻ: @gojo_bridgehousing
ምድቦች: ግብይት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 31.27K
የሰርጥ መግለጫ

Gojo Bridge Housing - ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ
#gojobridge #ጎጆ #ጎጆሀውስ #gojoapartmenent #ጎጆሮስካ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-01-04 18:28:49
ውድ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ቤተሰብ ወደናንተ ተደራሽ ለመሆን በኢንስታግራም አካውንት መተናል ይቀላቀሉን...

https://www.instagram.com/gojobridgehousing/

#gojobridge #ጎጆ #ጎጆሀውስ #gojoapartmenent #gmark


@gojo_bridgehousing
7.3K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 11:58:13 ውድ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ቤተሰቦች

ጥር 2 ለሚወጣው የመጀመሪያው ዙር ሮስካ ሎካል እጣ ውስጥ የሚካተቱት አባላት ዝርዝር ላይ ለሚኖር ማንኛውም ቅሬታ ከስር በተዘረዘሩት ስልኮች ደውላችሁ ማሳወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

0948059613
0948059611

@gojo_bridgehousing
12.1K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 16:04:57 ውድ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ቤተሰቦች

ጥር 2 ለሚወጣው የመጀመሪያው ዙር ሮስካ ሎካል እጣ ውስጥ የሚካተቱት አባላት ዝርዝር እነሆ.።

በዝርዝሩ ላይ ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካላችሁ እስከ ታሕሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ሀያሁለት ትራፊክ ፅ/ቤት ጀርባ በሚገኘው ቢሮዋችን በመገኘት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

@gojo_bridgehousing
15.0K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 16:11:19
መልካም ዜና ለጎጆ ሮስካ አባላት

ለጎጆ ሮስካ የሀገር ውስጥ ተመዝጋቢዎች፣ ለረዥም ጊዜ የምዝገባ ማጣሪያ ሲደረግ ቆይቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ ቀደም የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርአቱን በተመለከተ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረም፣ በእጣ አወጣጡ ስነ-ስርአት ላይም እክል እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ተደርጎ በተሟላ መልክ ለማካሄድ ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቀን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ አማካኝነት የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ የቦርድ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ሀላፊዎች፣ እንዲሁም በታዛቢ እና ተቆጣጣሪነት ሀላፊነት የወሰዱ ሰዎች በተገኙበት እጣውን ጥር 02 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በግራን‍‍‍ድ ኤልያና ሆቴል የምናወጣ ይሆናል፡፡

ዕጣው በዩቲዩብ እና በፌስቡክ ገጽ ላይ በቀጥታ የምናሰራጭ ስለሚሆን በእለቱ ይከታተሉ።

ይህ መርሀ-ግብር የጎጆ ሮስካ ጤና ሠራተኞችን አያካትትም፡፡

ይህ የእጣ አወጣጥ ስነስርአት እጅግ በጥንቃቄ እና ሀላፊነት በተሞላበት፣ ተጠያቂነት በሰፈነበት መንገድ እንዲካሄድ ይህንን ያህል ጊዜ ለመውሰድ ተገደናል ሆኖም ፍፃሜው እንዲያምር በታላቅ ትህትና ለሰጣችሁን ጊዜ ከልብ እያመሰገንን በእለቱ በቀጥታ ለመከታተል ዝግጁ እንድትሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን።

@gojo_bridgehousing

#gojobridge #ጎጆ #ጎጆሀውስ #gojoapartmenent #ጎጆሮስካ
36.2K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 07:35:28

47.4K views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 10:39:23 ውድ የጎጆ ሮስካ የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢ አባላት፣

እንደሚታወቀው ድርጅታችን የመጀመሪያውን የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብር ለማካሄድ ታዛቢና ተቆጣጣሪዎችን የሚወክሏቸውን አባላት ጋር ደውለው አስፈላጊውን መረጃ ተቀብለው በማስፈረም መዝግበው መጨረሳቸው ይታወቃል ፡፡

ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ ያልተደወለላችሁ እና ተደውሎላችሁ በተለያየ ምክንያት መረጃችሁን ያላቀረባችሁ እስከ ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድርስ ሃያ ሁለት አካባቢ ከትራፊክ ፅ/ቤት ጀርባ የሚገኘው ቢሮአችን የተመዘገባችሁበትን ሰነድ እና ወርሀዊ ቁጠባውን የከፈላችሁበትን የሚታይ የባንክ ስሊፕ ይዛችሁ እንድትቀርቡ ስንል እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ፡፡
T.me/gojobh
60.1K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 12:57:41 ውድ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ታዛቢ እና ተቆጣጣሪ አባላት፣

በመጀመሪያ ከሰኞ ጀምሮ ሀላፊነታችሁን ተወጥታችሁ ላስረከባችሁን ምስጋና እያቀረብን፣ የተወሰናችሁት በተለያየ ምክንያት ማጠናቀቅ ላልቻላችሁ እስከ ነገ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰአቱ 12:00 ሰዐት ድረስ እንድታጠናቅቁ ስንል እናሳውቃለን:: የሚደወልላችሁም አባላት አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንድታደርጉላቸው እናሳስባለን::

እስከ ነገ ያልተደወለላችሁ አባላት ሰኞ ተደውሎላችሁ በቢሮ የምትሰተናገዱ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ፡፡
T.me/gojobh
52.9K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 16:37:38 ውድ የጎጆ ሮስካ የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢ አባላት፣
ድርጅታችን የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብርን ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ መሆናችንን እና የሚወክሏችሁ ታዛቢና ተቆጣጣሪዎች ደውለው ለሚጠይቋችሁ ነገሮች አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ ማሳሰባችን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በርካታ አባላት ወደ ቢሮ እየደወሉ አልተደወለልንም በማለት ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ መሰረት እስከ አርብ ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ድርስ ለሁሉም አባላት ስለሚደወል በትዕግስት እንድትጠባበቁ እየጠየቅን በቀጣይ ያለውን ነገር የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
T.me/gojobh
49.2K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 16:32:32 ለታዛቢና ተቆጣጣሪ አባላት በሙሉ፣

ከመጀመሪያው ክፍያ (55,000 ብር)ውጪ ያለ አባላቱ የከፈሉትን ማንኛውንም ክፍያ እንድትቀበሉ ስንል እናሳስባለን።

በተለያየ ምክንያት ክፍለ ሀገር ያሉ አባላት በቴሌግራም አማካኝነት ቅሬታም ካለ መቀበል የከፈሉበትንም ደረሰኝ እንዲልኩ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

የመጨረሻ የማስረከቢያ ቀን ሀሙስ 11:30 ድረስ እንደሆነ በድጋሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

አርብ ሕዳር 16 ቀን 2015ዓ.ም በእጣ አወጣጡ ዙሪያ ቀድመን በምናሳውቃችሁ ቦታ ስብሰባ ይኖረናል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
T.me/gojobh
45.9K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 15:35:40 ውድ የሮስካ ሎካል ተመዝጋቢ አባላት በሙሉ

እንደሚታወቀው ድርጅታችን የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብርን ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ለዕጣ ማውጣቱ ስነ-ስርዓት ታዛቢና ተቆጣጣሪዎች ጥቅምት19 እና ህዳር 11 ቀን 2015 አ.ም የስራ ኃላፊነታቸውን እና በጠቅላላው የሚኖራቸውን ሚና ገለፃ የወሰዱና የሚወክሏቸውን አባላት ስም የተረከቡ መሆኑን እየገለፅን በተሰጣቸው ዝርዝር መሰረት ደውለው ለሚጠይቋችሁ ነገሮች አስፈላገ‍ኢውን ትብብር እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
T.me/gojobh
37.1K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ