Get Mystery Box with random crypto!

ውድ የጎጆ ሮስካ የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢ አባላት፣ እንደሚታወቀው ድርጅታችን የመጀመሪያውን የዕ | Gojo Bridge Housing

ውድ የጎጆ ሮስካ የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢ አባላት፣

እንደሚታወቀው ድርጅታችን የመጀመሪያውን የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብር ለማካሄድ ታዛቢና ተቆጣጣሪዎችን የሚወክሏቸውን አባላት ጋር ደውለው አስፈላጊውን መረጃ ተቀብለው በማስፈረም መዝግበው መጨረሳቸው ይታወቃል ፡፡

ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ ያልተደወለላችሁ እና ተደውሎላችሁ በተለያየ ምክንያት መረጃችሁን ያላቀረባችሁ እስከ ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድርስ ሃያ ሁለት አካባቢ ከትራፊክ ፅ/ቤት ጀርባ የሚገኘው ቢሮአችን የተመዘገባችሁበትን ሰነድ እና ወርሀዊ ቁጠባውን የከፈላችሁበትን የሚታይ የባንክ ስሊፕ ይዛችሁ እንድትቀርቡ ስንል እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ፡፡
T.me/gojobh