Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ዜና ለጎጆ ሮስካ አባላት ለጎጆ ሮስካ የሀገር ውስጥ ተመዝጋቢዎች፣ ለረዥም ጊዜ የምዝገ | Gojo Bridge Housing

መልካም ዜና ለጎጆ ሮስካ አባላት

ለጎጆ ሮስካ የሀገር ውስጥ ተመዝጋቢዎች፣ ለረዥም ጊዜ የምዝገባ ማጣሪያ ሲደረግ ቆይቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ ቀደም የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርአቱን በተመለከተ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረም፣ በእጣ አወጣጡ ስነ-ስርአት ላይም እክል እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ተደርጎ በተሟላ መልክ ለማካሄድ ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቀን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ አማካኝነት የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ የቦርድ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ሀላፊዎች፣ እንዲሁም በታዛቢ እና ተቆጣጣሪነት ሀላፊነት የወሰዱ ሰዎች በተገኙበት እጣውን ጥር 02 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በግራን‍‍‍ድ ኤልያና ሆቴል የምናወጣ ይሆናል፡፡

ዕጣው በዩቲዩብ እና በፌስቡክ ገጽ ላይ በቀጥታ የምናሰራጭ ስለሚሆን በእለቱ ይከታተሉ።

ይህ መርሀ-ግብር የጎጆ ሮስካ ጤና ሠራተኞችን አያካትትም፡፡

ይህ የእጣ አወጣጥ ስነስርአት እጅግ በጥንቃቄ እና ሀላፊነት በተሞላበት፣ ተጠያቂነት በሰፈነበት መንገድ እንዲካሄድ ይህንን ያህል ጊዜ ለመውሰድ ተገደናል ሆኖም ፍፃሜው እንዲያምር በታላቅ ትህትና ለሰጣችሁን ጊዜ ከልብ እያመሰገንን በእለቱ በቀጥታ ለመከታተል ዝግጁ እንድትሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን።

@gojo_bridgehousing

#gojobridge #ጎጆ #ጎጆሀውስ #gojoapartmenent #ጎጆሮስካ