Get Mystery Box with random crypto!

ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ geezlisan — ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ geezlisan — ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)
የሰርጥ አድራሻ: @geezlisan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 344
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ምኅላፍ ጥንታዊውንና ምስጢራዊውን የግእዝ ቋንቋ የምንማማርበት ምኅላፍ ነው።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-13 13:08:18 ሰላም ለክሙ አኃትነ ወአኃውየ.... እፎ ከረምክሙ።

በምዕራፍ የተከፋፈለ ተከታታይ ትምህርት ለማግኘት ከታች ባለው ምኅላፍ ገብታችሁ መከታተል ትችላላችሁ።

@Kedamie_lisanat1
216 viewsedited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 07:32:24
እስኩ አጽምዕዋ ለእምነ...
ኢንፍቀድ ከመ ንኵን ምዕራብያዊያነ አላ ንኅሥሥ ከመ ንኵን ከመ አበዊነ ዘቀደምት።

ምዕራባውያንን ለመኾን ከመጋጋጥ፣
የቀደሙ አባቶችን ኾነን መለወጥ!
361 views04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-29 08:37:01 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ለጀማሪዎች እና ለአዲስ ተመዝጋቢዎች

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይኹን እንኳን ደኅና መጣችሁ እያልን....

በዚህ ምኅላፍ #ቀዳሜ_ልሳናት፣ የልሳናት በኩር የሆነውን #ልሳነ_ግእዝን የምንወያይበት፣ የምንማማርበት፣ የምንጠያየቅበት ብሎም ቋንቋችንን አውቀን ባህላችንን፣ ሃይማኖታችንን የምናሳድግበት፣ ወደ ቀደመው ነገር የምንመለስበት፣ እንዲሁም የሀገራችንን አንድምታ እና ታሪክ እናውቅ ዘንድ መንገድ የኾነውን ልሳን የምንማማርበት ምኅላፍ ነው።

በድጋሚ እንኳን ደኅና መጣችሁ!!!

ትምህርቱን በቅርብ ቀን በይፋ እንጀምራለን። እስከዚያው ድረስ ጓደኞቻችሁ እወቀቱን ይገበዩ ዘንድ ከታች በምናስቀምጠው አድራሻ መማር የሚፈልጉ ጓደኞቻችሁን ኹሉ ጋብዙ

ይህን የምኅላፉን አድራሻ @kedamelisanat1 ነው መማር ለሚፈልጉ ጀማሪዎች እየላካችሁ ጠብቁን።

የምኅላፉ አድራሻ @kedamelisanat1 join

የመወያያ መድረኩ አድራሻ @kedamelisanat1g join
659 viewsedited  05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-21 11:35:06 ፬. አገናዛቢ ስም መራሕያን
(Possessive Nouns)

እነዚህ መራሕያን ባለንብረትነትን ይገልጣሉ። ከላይ ካየናቸው አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን የሚለዩት ራሳቸውን ችለው የሚቆሙ ከስም በኋላ የሚገኙ መሆናቸው ነው።

፩) ዚአየ=የእኔ=Mine
፪) ዚአነ=የእኛ=Ours
፫) ዚአከ=የአንተ=Yours
፬) ዚአኪ=የአንቺ=Yours
፭) ዚአክሙ=የእናንተ(ወ)=Yours
፮) ዚአክን=የእናንተ(ሴ)=Yours
፯) ዚአሁ=የእሱ=His
፰) ዚአሃ=የእሷ=Hers
፱) ዚአሆሙ=የእነሱ(ወ)=Theirs
፲) ዚአሆን=የእነሱ(ሴ)=Theirs

እነዚህ መራሕያን ራሳቸው እንደ ስም ያገለግላሉ እንጅ ስም አይከተላቸውም፡፡

ምሳሌ
ሀ) ዝንቱ መጽሐፍ #ዚአሃ ውእቱ፡፡
ይህ መጽሐፍ #የእርሷ ነው
This book is #Hers.

ዚአሃ የሚለው መጽሐፍ ከሚለው በኋላ ራሱን ችሎ እንደ ስም አገልግሏል

ለ) ስመ ዚአየ == #የኔ ስም
ሐ) ዝ ግብር #ዚአሁ ውእቱ፡፡
ይህ ሥራ #የሱ ነው፡፡
መ) አነ ውእቱ ወልደ #ዚአከ፡፡
እኔ የእንተ #ልጅ ነኝ።

የሁለቱን መራሕያን ልዩነት ተመልከቱ
ስመ #ዚአየ = የኔ ስም (አገናዛቢ ስም)
#ዘዚአየ ስም = የኔ ስም (አገናዛቢ ቅጽል)
ዝንቱ መጽሐፍ #ዚአየ ውእቱ (አገናዛቢ ስም)
ይህ መጽሐፍ #የኔ ነው
this book is #mine

ዝንቱ ውእቱ #ዘዚአየ መጽሐፍ (አገናዛቢ ቅጽል)
This is #my book
#የኔ መጽሐፍ ይህ ነው


ማሳሰቢያ፦ ልሳነ እንግልጣር (የእንግሊዝ ቋንቋ) የተጠቀምሁት ብዙ ጊዜ በትምህርት ቤት ስለሚሰጥ ይቀላል ብየ ስላሰብሁ ነው። በአማርኛ ትምህርት ብዙ ጊዜ ስለዚህ ማለትም ስለ መራሕያን/ተውላጠ ስም ብዙ ጊዜ ትምህርቱ አይሰጥም ይልቁንም በእንግሊዝኛ በብዛት ስለሚሰጥ ነው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የሁለቱን ልዩነት ትረዱ ዘንድ....
በዚህ መሠረት የሚከተለውን ጥያቄ በአገናዛቢ ቅጽል እና በአገናዛቢ ስም መራሕያን ሦስት ሦስት ዐ. ነገር ሥሩ።

ሀ) ደብተር = ደብተር

ምሳሌ
አገናዛቢ ቅጽል
ዝ ውእቱ ዘዚአሁ ደብተር
ይህ የእርሱ ደብተር ነው

አገናዛቢ ስም
ዝ ደብተር ዚአሁ ውእቱ
ይህ ደብተር የእርሱ ነው
973 viewsedited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-21 11:35:05 ፫. አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን (Possessive Objectives pronouns)

አገናዛቢ መራሕያን (possessive pronouns) ባለንብረትነትን ወይም ባለይዞታነትን ያመለክታሉ።

አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን (possessive adjective pronouns) ደግሞ ቅጽል (adjective) ሲሆኑ ከስም በፊት እየመጡ የባለቤትነትን ወይም ባለንብረትነትን ይገልጣሉ። ሁልጊዜ ከስም በፊት ይገኛሉ።

እሱም የሚከተሉት ናቸው ፦

፩) ዘዚአየ=የእኔ=My
፪) ዘዚአነ=የእኛ=Our
፫) ዘዚአከ=የአንተ=Your
፬) ዘዚአኪ=የአንቺ=Your
፭) ዘዚአክሙ=የእናንተ(ወ)=Your
፮) ዘዚአክን=የእናንተ(ሴ)=Your
፯) ዘዚአሁ=የእሱ=His
፰) ዘዚአሃ=የእሷ=Her
፱) ዘዚአሆሙ=የእነሱ(ወ)=Their
፲) ዘዚአሆን=የእነሱ(ሴ)=Their

ምሳሌ ፩፦ ወልድ=ልጅ (ስም)

ሀ) አነ ውእቱ #ዘዚአሃ ወልድ => እኔ #የእሷ ልጅ ነኝ፡፡
ለ) አንተ ውእቱ #ዘዚአየ ወልድ => አንተ #የእኔ ልጅ ነህ፡፡


ከምሳሌ ሀ) እንደምናየው "አነ ውእቱ ዘዚአሃ ወልድ".. ዘዚአሃ የሚለው አገናዛቢ መራሕያኑ "ወልድ" ከሚለው ስም በፊት ነው የመጣው።

በምሳሌው መሠረት ሦስት ዓረፍተ ነገር ሥሩ።
የተሰጠን ስም፦ ብዕር = ብዕር (እስከብሪቶ)፣ መጽሐፍ = መጽሐፍ

የተሰጠን ግስ፦ ወሰደ = ወሰደ


ውእቱ ወሰደ #ዘዚአየ ብዕር => እርሱ #የኔን እስክብሪቶ ወሰደ።

አነ ወሰድኩ #ዘዚአከ መጽሐፍ => እኔ #የአንተን መጽሐፍ ወሰድሁ

ሀ)
ለ)
ሐ)
672 views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-15 11:22:59 ፩) አፍቀረ= ወደደ

ሀ) አነ አፍቀርኩ #ኪያኪ ➳እኔ #አንቺን ወደድሁ።
ለ) አንትሙ አፍቀርክሙ #ኪያሆሙ ➳ አናንተ #እነርሱን ወደዳችሁ።
ሐ) አንተ አፍቀርከ #ኪያሃ➳ አንተ #እርሷን ወደድህ።
መ) ውእቱ አፍቀረ #ኬያሆን ➳እርሱ #እነርሱን ወደደ።
ሠ) ይእቲ አፍቀረት #ኪያሁ ➳እርሷ #እርሱን ወደደች።


፪) ጸልዐ=ጠላ

ሀ) አነ ጸላዕኩ #ኪያሁ ➳እኔ #እርሱን ጠላሁ።
ለ) ንሕነ ጸላዕነ #ኪያሆሙ ➳እኛ #እነርሱን ጠላን።
ሐ) አንቲ ጸላዕኪ# ኪያየ➳አንቺ #እኔን ጠላሽ።
መ) አንተ ጸላዕከ #ኪያነ ➳አንተ #እኛን ጠላህ።
ሠ) ውእቶሙ ጸልዑ #ኪያሃ ➳እነርሱ #እርሷን ጠሉ።


ሐ) ወሰደ = ወሰደ

ሀ) አነ ወሰድኩ #ኪያከ ➳እኔ #አንተን ወሰድሁ።
ለ) ንሕነ ወሰድነ #ኪያኪ➳ እኛ #አንቺን ወሰድን።
ሐ) ውእቱ ወሰደ #ኪያከ ➳ እርሱ #አንተን ወሰደ።
መ) ውእቶን ወሰዳ #ኪያክሙ ➳ እነርሱ #እናንተን ወሰዱ።
ሠ) ንሕነ ወሰድነ #ኪያሃ ➳ እኛ #እርሷን ወሰድን።


"ጸልዐ" የሚለው ግስ የተለየ አመል ያለው ግስ ነው። እርሱን በቀጣይ ትምህርት ጊዜያት እናየዋለን።
ሳትማሩት በስሕተት ነው የሰለጠፍሁት። ለዚህም እጅግ በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ
660 views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-11 09:21:28 ፪.፪ የመራሕያን አይነቶች


ስድስት ዓይነት መራሕያን አሉ፡፡ እነሱም፦
፩ ) ባለቤት/ሰዋዊ መራሕያን
፪ ) ተሳቢ መራሕያን
፫ ) አገናዛቢ ስም መራሕያን
፬ ) አገናዛቢ ቅፅል መራሕያን
፭ ) ድርብ መራሕያን
፮ ) ገላጭ መራሕያን


፩. ባለቤት መራሕያን
(personal pronouns)

ከላይ ያየናቸው ባለቤትን የሚያመለክቱ፣ በስም ቦታ እየገቡ የሚያገለግሉ ተውላጠ ስሞች ናቸው። እነሱም፦ አነ፣ ንሕነ፣ አንተ፣ አንቲ፣ አንትሙ፣ አንትን፣ ውእቱ፣ ይእቲ፣ ውእቶሙ እና ውእቶን ናቸው።


፪. ተስሐቢ መራሕያን
(objective pronouns)

ተሳቢ መራሕያን ድርጊቱ በላያቸው ላይ የተፈጸመ መሆኑን ይገልጻሉ። ማንን ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ተስሐቢ መራሕያንን ይሰጠናል።
ማንን? እኔን፣ አንተን፣ እኛን....

ለምሳሌ፦ አበበ #እኔን መታኝ። በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ የተመታው አካል #እኔ፣ መቺው አካል #አበበ ነው።


ተስሐቢ መራሕያን በቁጥር አስሥር ናቸው
እነሱም፦

፩) ኪያየ = እኔን
፪) ኪያነ = እኛን
፫) ኪያከ = አንተን
፬) ኪያኪ = አንቺን
፭) ኪያክሙ = እናንተን(ወ)
፮) ኪያክን = እናንቺን/እናንተን(ሴ)
፯) ኪያሁ = እሱን
፰) ኪያሃ = እሷን
፱) ኪያሆሙ = እነሱን(ወ)
፲) ኪያሆን = እነርሷን/እነሱን(ሴ)


ምሳሌ ፩፦ ተለወ=ተከተለ

ሀ) አነ ተለውኩ #ኪያከ => እኔ #አንተን ተከተልሁ፡፡
ለ) ንሕነ ተለውነ #ኪያሆሙ => እኛ #እነሱን ተከተልን፡፡
ሐ) አንተ ተለውከ #ኪያየ=>አንተ #እኔን ተከተልህ፡፡
መ) ውእቱ ተለወ #ኬያነ =>እሱ #እኛን ተከተለ፡፡
ሠ) ይእቲ ተለወት #ኪያሃ =>እርሷ #እሷን ተከተለች፡፡
ረ) ውእቶን ተለዋ #ኪያሆን => እነሱ #እነሱን ተከተሉ፡፡
ሰ) አንቲ ተለውኪ #ኪያሁ =>አንቺ #እሱን ተከተልሽ፡፡


ምሳሌ ፪፦ ዘበጠ = መታ

፩) አነ ዘበጥኩ #ኪያከ => እኔ #አንተን መታሁ፡፡
፪) ንሕነ ዘበጥነ #ኪያሆሙ => እኛ #እነሱን መታን፡፡
፫) አንተ ዘበጥከ #ኪያየ=>አንተ #እኔን መታህ፡፡
፬) ውእቱ ዘበጠ #ኬያነ =>እሱ #እኛን መታ፡፡
፭) ይእቲ ዘበጠት #ኪያሃ =>እርሷ #እሷን ተከተለች፡፡
፮) ውእቶን ዘበጣ #ኪያሆን => እነሱ #እነሱን መቱ፡፡ (ለቅርብ ሴቶች)
፯) አንቲ ዘበጥኪ #ኪያሁ =>አንቺ #እሱን መታሽ፡፡
፰) አንትሙ ዘበጥክሙ #ኪያሆሙ => እናንተ #እነሱን መታችሁ።


አነ ዘበጥኩ ኪያከ።
| | |
ባለቤት ግስ ተሳቢ


ጥያቄ፦ በምሳሌው መሠረት በሚከተሉት ቃላት አምስት አምስት ዐረፍተ ነገር ስሩ፡፡

ሀ) አፍቀረ=ወደደ
ለ) ጸልዐ=ጠላ
ሐ) ወሰደ=ወሰደ
756 views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-11 09:20:39 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ለተሰጠው መልመጃ መልስ

በእውነት ቃለ ሕይወት ያሰማልን እጅግ ጥሩ አድርጋችሁ ነው የሠራችሁት!!! በርቱልን!!!


በአንደኛ እና ሁለተኛ መደብ መራሕያን

ሀ) ወደሰ ➜አመሰገነ

፩) አነ ወደስ➜ እኔ አመሰገን
፪) ንሕነ ወደስ➜ እኛ አመሰገን
፫) አንተ ወደስ➜አንተ አመሰገን
፬) አንቲ ወደስ➜አንች አመሰገን
፭) አንትሙ ወደስክሙ➜እናንተ አመሰገናችሁ(ብዙ ወንዶች
፮) አንትን ወደስክን➜ እናንተ/እናንቺ አመሰገናችሁ(ብዙ ቅርብ ሴቶች)

በሦስተኛ መደብ መራሕያን

፯) ውእቱ ወደሰ ➜ እርሱ አመሰገነ
፰) ይእቲ ወደሰ➜እርሷ አመሰገነ
፱) ውእቶሙ ወደ➜ እነርሱ አመሰገኑ(ብዙ የሩቅ ወንዶች
፲) ውእቶን ወደ➜ እነርሱ/እነርሷ አመሰገኑ (ብዙ የሩቅ ሴቶች


ለ)ነበረ=ተቀመረ

በአንደኛና በሁለተኛ መደብ መራሕያን

፩) አነ ነበር➜እኔ ተቀመጥ
፪) ንሕነ ነበር➜እኛ ተቀመጥ
፫) አንተ ነበር➜አንተ ተቀመጥ
፬) አንቲ ነበር➜ አንቺ ተቀመጥ
፭) አንትሙ ነበርክሙ ➜እናንተ ተቀመጣችሁ
፮) አንትን ነበርክን➜ እናንተ/እናንቺ ተቀመጣችሁ

በሦስተኛ መደብ መራሕያን

፯) ውእቱ ነበረ➜ እሱ ተቀመጠ
፰) ይእቲ ነበረ ➜እሷ ተቀመጠች
፱) ውእቶሙ ነበ ➜እነሱ ተቀመጡ
፲) ውእቶን ነበ ➜ እነርሱ/እነርሷ ተቀመጡ


ሐ) ሀለወ= አለ፣ኖረ

በአንደኛ እና በሁለተኛ መደብ መራሕያን

፩) አነ ሀለው➜እኔ አለሁ
አለው
አለሁ

፪) ንሕነ ሀለው➜ እኛ አለን

፫) አንተ ሀለው➜አንተ አለህ
አለክ
አለህ

፬) አንቲ ሀለው➜አንች አለሽ

፭) አንትሙ ሀለውክሙ ➜እናንተ አላችሁ
አላቹ
አላችሁ

፮) አንትን ሀለውክን➜እናንተ/እናንቺ አላችሁ (ለብዙ ቅርብ ሴቶች)

በሦስተኛ መደብ መራሕያን

፯) ውእቱ ሀለወ➜ እሱ አለ
፰) ይእቲ ሀለወ ➜እሷ አለች

፱) ውእቶሙ ሀለ ➜እነርሱ አሉ
ሀለው
ሀለዉ

፲) ውእቶን ሀለ ➜እነርሱ/እነርሷ አሉ
631 views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-27 10:58:05 ግሥ በአሥርቱ መራሕያን ሲዘረዘር

አንድን ግሥ በመራሕያን ለማርባት የሚከተለውን ሕግ እንጠቀማለን።


ምሳሌ የተሰጠን ግሥ ፣ ቀደሰ = አመሰገነ

የሦስተኛ መደብ መራሕያን

#ውእቱ ሲሆን ቅጥያ የለውም። ግሡ እንዳለ ይቀመጣል።
ምሳሌ፦ ውእቱ ቀደሰ= እርሱ አመሰገነ

#በይእቲ ጊዜ ግሡ ምንም ሳይቀየር #ት መጨመር ብቻ ነው። በአማርኛው ደግሞ #ች

ምሳሌ፦ ይእቲ ቀደሰት = እርሷ አመሰገነች

#በውእቶሙ ጊዜ የመጨረሻውን ፊደል ወደ #ካብዕ (ሁለተኛ) ፊደል መቀየር ነው።

ምሳሌ፦ ውእቶሙ ቀደሱ = እነርሱ ቀደሱ። (#ሰ ወደ #ሱ ይቀየራል)

#በውእቱን ጊዜ የመጨረሻ ፊደሉ ወደ #ራብዕ (አራተኛ) ፊደል ይሸየራል።

ምሳሌ፦ ውእቶን ቀደሳ = እነርሱ አመሰገኑ(ለሴቶች) (ሰ ወደ ሳ)

በእንደኛና ሁለተኛ መራሕያን መደብ መራሕያን ጊዜ የተሰጠንን ግስ የመጨረሻውን ፊደል ወደ ሳድስ ከቀየርን በኋላ ቅጥያዎችን እንደመራሕያኑ አይነት እንጨምራለን።

#በአነ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ #ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ኩ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ ቅጥያ አቻው #ሁ
ምሳሌ፦ አነ ቀደስኩ = እኔ አመሰገንሁ ( ሰ ወደ ስ፣ መጨረሳ ኩ መጨመር)

#በንሕነ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ነ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ን

ንሕነ ቀደስነ = እኛ አመሰገን

#በአንተ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ከ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ህ
ምሳሌ፦ አንተ ቀደስከ = አንተ ቀደስህ

#በአንቲ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ኪ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ሽ
ምሳሌ፦ አንቲ ቀደስኪ = አንቺ አመሰገንሽ።

#በአንትሙ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ክሙ ቅጥያ ይጨመራል።

ምሳሌ፦ አንትሙ ቀደስክሙ = እናንተ አመሰገናችሁ (ለብዙ ወንዶች)

#በአንትን ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ክን ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ችሁ
ምሳሌ፦ አንትን ቀደስክን= እናንተ አመሰገናችሁ (ለብዙ ሴቶች)


ምሳሌ ፩) ቀተለ = ገደለ
በ ፲ መራሕያን ሲረባ፦

በአንደኛና ሁለተኛ መደብ መራሕያን ጊዚ "ቀተለ" ከሚለው የመጨረሻ ፊደል #ለ ወደ #ል ትቀየራለች

፩) አነ ቀተልኩ= አኔ ገደልሁ
፪) ንሕነ ቀተልነ=እኛ ገደልን
፫) አንተ ቀተልከ=አንተ ገደልህ
፬) አንቲ ቀተልኪ=አንቺ ገደልሽ
፭) አንትሙ ቀተልክሙ= እናንተ ገደላችሁ
፮) አንትን ቀተልክን= እናንተ ገደላችሁ

በሦስተኛ መደብ መራሕያን
፯) ውእቱ ቀተለ= እርሱ ገደለ
፰) ይእቲ ቀተለት=እርሷ ገደለቺ
፱) ውእቶሙ ቀተሉ=እነርሱ ገደሉ
፲) ውእቶን ቀተላ= እነርሱ ገደሉ

በዚህ መሰረት የሚከተሉትን ግሶች በአሥሩ መራሕያን ዘርዝሩ።

ሀ) ወደሰ = አመሰገነ
ለ) ነበረ = ተቀመጠ
ሐ) ሀለወ = አለ፣ ኖረ
929 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-26 08:42:12 የተሰጠንን የግእዝ ቊጥር ወደ አረብኛ መቀየር የተሰጠንን ግእዝ ቊጥር ወደ አረብኛ ለመቀየር ከብዜቱ ወይም ከመቶኛው ቀድሞ የመጣውን ቁጥር ወደአረብኛ በመቀየር ፊትለ ለፊቱ ባለው የመቶ ብዜት እያባዙ መደመር ነው። ምሳሌ፦ ፺፻፺ ፺ | ፺ | ፻ | 90 90 ፺×፻ + ፺ =90×100 +90 =9090 ምሳሌ ፪፦ ፫፼፸፬፻፷፰ ፫ ፼ ፸፬ ፻ ፷፰ | × …
653 views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ