Get Mystery Box with random crypto!

ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ geezlisan — ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ geezlisan — ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)
የሰርጥ አድራሻ: @geezlisan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 344
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ምኅላፍ ጥንታዊውንና ምስጢራዊውን የግእዝ ቋንቋ የምንማማርበት ምኅላፍ ነው።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-06-24 13:04:18 የተሰጠንን የግእዝ ቊጥር ወደ አረብኛ መቀየር

የተሰጠንን ግእዝ ቊጥር ወደ አረብኛ ለመቀየር ከብዜቱ ወይም ከመቶኛው ቀድሞ የመጣውን ቁጥር ወደአረብኛ በመቀየር ፊትለ ለፊቱ ባለው የመቶ ብዜት እያባዙ መደመር ነው።

ምሳሌ፦ ፺፻፺
፺ | ፺
| ፻ |
90 90

፺×፻ + ፺
=90×100 +90
=9090


ምሳሌ ፪፦ ፫፼፸፬፻፷፰

፫ ፼ ፸፬ ፻ ፷፰
| × | × |
፫ ፸፬ ፷፰
| | |
3 74 68

፫ ×፼ + ፸፬×፻ + ፷፰

3×10,000 + 74×100 + 68

=37,468


በምሳሌው መሰሠት የሚቀተሉትን የግእዝ ቊጥሮች ወደ አረብኛ

ሀ) ፵፻፵
ለ) ፩፼፩
ሐ) ፳፻፳፪
መ) ፲፼፺፻፴፪
634 views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-24 13:03:57 ሰላም እንዴት አደራችሁ ፍቁራንና ፍቁራት?

መልመጃ መልስ

የአረብኛ ቊጥሮችን ወደ ግእዝ አኀዝ መቀየር

ሀ) 189

1 89
፩ | ፹፱


= ፩፻፹፱ = ፻፹፱ (አሐዱ ምእት ሰማንያ ወተሠዓቱ)

ለ) 325

3 25
፫ | ፳፭

= ፫፻፳፭ -- ሠልስቱ ምእት እሥራ ወኃምስቱ

ሐ) 402

4 02
፬ | ፪

= ፬፻፪ -- አርባዕቱ ምእት ወክልኤቱ

መ) 4002
40 02
፵ | ፪

= ፵፻፪ -- አርብዓ ምእት ወክልኤቱ

ሠ) 6875
68 75
፷፰ | ፸፭


=፷፰፻፸፭ -- ስድሳ ወስመንቱ ምእት ሰብዓ ወኃምስቱ

ረ) 8000

80 00
፹ | --

=፹፻ ሰማንያ ምእት
609 viewsedited  10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-19 18:57:34 ሰላም ለክሙ አኃውየ ወአኃትየ።

እስኪ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው

ምልማድ ፩

ትክክለኛ መልስ የያዘ ነው ብላችሁ
የምታስቡትን ፊደል ምረጡ።

፩. መሠረታዊ (መደበኛ) የግእዝ ፊደላት (አዕጹቃቸውን ሳይጨምር) ብዛት ስንት ነው?
አ) 182 (፻፹፪)
በ) 26 (፳፮)
ገ) 202 (፪፻፪)

፪. ከሚከተሉት ውስጥ የግእዝ ፊደላትን ብቻ ያልያዘው ስብስብ የቱ ነው

አ) ሀ፣ለ፣ሐ፣መ፣ሠ፣ረ
በ) ሸ፣ቨ፣ቸ፣ኘ፣ኸ፣ዠ፣ጀ፣ጨ
ገ) ቀ፣ ወ፣ ገ፣ ቐ፣ኧ፣ ቛ፣
ደ) ደ፣ ሐ፣ ዘ፣ ከ፣ ጸ፣ ዐ


፫. "አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን ይቅር በለን" ለማለት የቱን እንጠቀማለን?

አ) እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
በ) እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ

፬. "አበበ የቤት ሥራውን ጨረሰ" ለማለት ትክክለኛው የቱ ነው

አ) አበበ የቤት ሥራውን ፈጸመ
በ) አበበ የቤት ሥራውን ፈፀመ

፭. ከሚከተሉት ውስጥ በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?

አ) ቃለ ህይወት ያሰማልን
በ) ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ገ) ቃለ ኅይወት ያሰማልን

፮. "ክርስቶስ ከድንግል ተወለደ" የሚለው አቻ ትርጒሙ የቱ ነው?

አ) ክርስቶሰ ሰረቀ እምድንግል
በ) ክርስቶስ ሠረቀ እምድንግል
(እምድንግል = ከድንግል)

፯. የሰው ልጆች ሁሉ አባት፣ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረው ሰው ስም የቱ ነው?

አ) ዐዳም
በ) አዳም


፰.የፀሓይ መግቢያን የሚያመለክተው፦
አ) ምእራብ
በ) ምዕራብ

፱. በትክክል የተጻፈው ስመ ክርስትና የቱ ነው?

አ) ወለተ ስላሴ
በ) ወልደ መድህን
ገ) አመተ ሥላሴ
ደ) ዓመተ ሥላሴ

፲. የፀሓይ መውጫን የሚያመለክተው፦
አ) ምስራቅ
በ) ምሥራቅ


፲፩. ከታች የተሰጠን የሁለት ተጋቢዎች በጋብቻቸው ዕለት የተጻፈላቸው ጽሑፍ ነው እንበል። በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?

አ) የአቶ ዐምደወርቅ እና ወይዘሮ ሰብለወንጌል ሰርግ መርሐ ግብር

በ) የአቶ ዐምደወርቅ እና ወይዘሮ ሰብለወንጌል ሠርግ መርሐ ግብር


፲፪. በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?
አ) መድሀኔአለም
በ) መድኃኔዓለም
ገ) መድሐኔዓለም
ደ) መድሐኔአለም

፲፫. ሥዕል መሳልን የሚያመለክተው

አ) ሰአለ
በ) ሠዓለ


፲፬. እመቤታችን በየወሩ በ፲፮(16) ትከብራለች። የስሟ መጠሪያ በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?

አ)ኪዳነ ምኅረት
በ)ኪዳነ ምህረት
ገ)ኪዳነ ምሕረት
ደ)ኪዳነ ምኽረት


፲፭. በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?
አ) ሃይማኖት
በ) ሐይማኖት
ገ) ኀይማኖት
ደ) ሓይማኖት


፲፮. ሰው ስለ ኀጢአቱ ተጸጽቶ ወደ
እግዚአብሔር የሚመለስበት ምን ይባላል፦

አ) ንሥሀ
በ) ንስኀ
ገ) ንስሐ
ደ) ንሥኸ


፲፯. አባቶች የሚሰጡት ተግሳጽና ቡራኬ ምን ይባላል?
አ) ምዕዳን
በ) ምእዳን

አጭር መልስ ስጡ

፲፰. የ "የ"ን አዕጹቅ/ቅጥያ ከግእዝ እስከ ሳብዕ ጻፉ

፲፱. ግእዝ ማለት ምን ማለት ነው?

፳. የውስጣችሁን ስሜትና ምኞት መልሱ

ሀ) ግእዝ ቋንቋ ለመማርም ምን አነሳሳችሁ?
ለ)እናንተ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማዕከል ኃላፊ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?
ሐ) ወደፊት ቤተሰብ ስትመሠርቱ (የመሠረታችሁ ካላችሁም) በግእዝ ልሳን ጉዳይ ምን ለማድረግ ትመኛላችሁ
769 views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-03 16:16:44 ለግእዝ ትምህርት ፈላጊዎች:-

እነሆ በትምህርት ቤታችን ከአብነት ትምህርቱ በተጨማሪ የልሳነ ግእዝ ትምህርት ራሱን ችሎ ሊሰጥ ነው። ትምህርቱ ተከታታይ ሲሆን መመዘኛ ፈተናዎችም ይኖሩታል።


ለመማር የምትፈልጉ ሁሉ :-
ቀጥሎ ያለውን የመመዝገቢያ ቅጽ በመሙላት እና የሞላችሁትን

ወደ @kidanie

የውስጥ መስመር በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ።

የመመዝገቢያ ቅጽ

፩) ዓለማዊ ስም ---------
፪) የክርስትና ስም ----------
፫) የትውልድ አድራሻ---
፬) አሁን የሚሰሩት የስራ አይነት-----
የስራ ቦታ-------
፭) ስልክ ቁጥር (የሀገሩን ኮድ በማስቀደም ይጀምሩ) -------


ትምህርቱ ሰኔ ፯ ይጀመራል።

ከቤተ ያሬድ አብነት ትምህርት ቤት
1.1K viewsedited  13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-03 16:14:17 ለአብነት ትምህርት ፈላጊዎች:-

እነሆ የቤተ ያሬድ አብነት ትምህርት ቤት በቴሌግራም የአብነት ትምህርት ከውዳሴ ማርያም ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል።

ለመማር የምትፈልጉ ሁሉ :-
ቀጥሎ ያለውን የመመዝገቢያ ቅጽ በመሙላት እና የሞላችሁትን

ወደ @Dn_Lealem

የውስጥ መስመር በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ።

የመመዝገቢያ ቅጽ

፩) ዓለማዊ ስም ---------
፪) የክርስትና ስም ----------
፫) የትውልድ አድራሻ---
፬) አሁን የሚሰሩት የስራ አይነት----- የስራ ቦታ-------
፭) ስልክ ቁጥር (የሀገሩን ኮድ በማስቀደም ይጀምሩ) -------


ከቤተ ያሬድ አብነት ትምህርት ቤት
879 viewsedited  13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-02 08:40:01 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም



ሠናይ በዓለ ትንሣኤ ተመነይኩ ለክሙ
1.1K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-01 23:12:06 ንዜኑ ትንሣኤከ ቅድስት እግዚኦ.....

እንቋዕ አብጻሕክሙ ለበዓለ ትንሣኤ ቅድስት ለእግዚነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።


ትንሣኤ

ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በዘመነ ብሉይ ኹሉም የሰው ልጆች በአዳም ኃጢአት ምክንያት እየተኰነኑ በሞተ ነፍስ ተይዘው ለርደተ ሲዖል ይዳረጉ ነበር ። (፩ኛ ቆሮ ፲፭ ÷፳፪)

"ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ከዚያም እስከ ክርስቶስ ድረስ ሞት ነገሠ፤" ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ (ሮሜ ፭÷፲፬)

በዚኽም ምክንያት አበ ብዙኀን አብርሃም እና ሌሎች ደጋግ አባቶች እንኳ ሳይቀሩ የወረዱት ወደ ሲዖል ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ "ጽድቃችንም ኹሉ እንደመርገም ጨርቅ ነው፤" (ኢሳ ፷፬ ÷፮) ኤርምያስም "ለሥጋ ለባሽ ኹሉ ሰላም የለም፥ ስንዴን ዘሩ እሾኽንም አጨዱ፡፡" (ኤር ፲፪÷፲፫)ብለዋል።

በዚኽ ምክንያት የብሉይ ኪዳን ዘመን - ዘመነ ፍዳ፣ ዘመነ ኵነኔ፣ ዘመነ ጽልመት ተብሏል፡፡ በዚኽ ዘመን እነ ቅዱስ ዳዊት፡- "አንሥእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ፤ ኃይልኽን አንሣ እኛንም ለማዳን ና" እያሉ ወልድን ተማጽነዋል፡፡ (መዝ ፸፱÷ ፪)

ይኽም የሚያመለክተው በዚያ በጨለማ ዘመን ኾነው ተስፋቸው የክርስቶስ ትንሣኤ እንደነበረ ነው፡፡ በሞት አጠገብ ሕይወት÷ በመቃብር አጠገብ ትንሣኤ እንዳለ ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርጋቸው የክርስቶስ ትንሣኤ ነውና፡፡ ያን ጊዜ ከሲዖል እንደሚወጡ፥ የተዘጋች ገነትም እንደምትከፈትላቸው ያውቃሉና፡፡

የክርስቶስ ትንሣኤን፣ የአዳም ልጆች በጠቅላላ “ትንሣኤ ዘጉባኤን” በተስፋ እንዲጠብቁ ኾነዋል፡፡ ይኽም ተስፋ ሃይማኖት እንዲይዙ ምግባር እንዲሠሩ፣ ምድራዊውን ንቀው ሰማያዊውን እንዲናፍቁ አድርጓቸዋል፡፡

ዛሬ ከ፪ሺህ አዝማናት በላይ ቆይተን እንደ ነብየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት “አቤቱ ኃይልኽን አንሣ እኛንም ለማዳን ና” እያልን መጮኽ ያለብን ጊዜ ላይ ነን፡፡ በክርስቶስ ትንሣኤ ዘለዓለማዊ ብርሃን ወጥቶልናል፣ በመቃብር አጠገብ ትንሠኤን ዓይተናል፤ ነገር ግን ምግባራችን ስላልቀና ለመከራ ቸነፈር ተላልፈን ተሰጠን፡፡ "አቤቱ ማረን" እንበለው! እሱም በምሕረቱ ይጎበኘናል፣ በብሉይ የተዘጋው ገነት በሐዲስ ተከፍቷልና፤ በክፋታችን ልክ እንደተራራቅን በእግዚአብሔር ፍቅርና በልቡና መመለስ እንቀራረባለን፤ ክፉ የተናገረው አንደበት ከጨርቅ፣ ክፉ ያደረገ እጅ ከአጓንት እንዲላቀቅ፣ ለአንደበታችን መልካም ንግግርን ለእጃችንም መጽዋትን ልምድ እንድናደርግ ፈጠሪ ይርዳን፡፡

በክርስቶስ ትንሣኤ ያገኘነው ጸጋ ታላቅ ነው። ከጨለማ ወደ ብርሃን ወጥተናል ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋግረናል፣ ሙታን የነበርን ሕያዋን፣ ምድራውያን የነበርን ሰማያውያን፣ ሥጋውያን የነበርን መንፈሳውያን ኾነናል፡፡ "ሞት ኾይ÷ መውጊያኽ የት አለ? ሲዖል ኾይ ድል መንሣትኽ የት አለ?" የምንል ኾነናል፡፡ ሆሴ ፲፫÷፲፬ ፣ ፩ኛቆሮ ፲÷፶፭፡፡

በዘመናችንም ከመጣብን ሞት አምላከ ቅዱስ ያሬድ በቸርነቱ ትንሣኤውን እንዳሳየን - ከቸነፈሩም ጠብቆ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ እንዲያወጣን የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡



መልካም የትንሣኤ በዓል ይኹንልን

ምንጭ፦ ውሉደ ያሬድ ሰ/ት/ቤት
1.0K views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-13 08:56:16 ፩.፭. የፊደል ለውጥ በአንድ ቃል ውስጥ


#ሙባእ

የ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ቤተክርስቲያን አምድ የነበሩት #ሊቁ_መልአከ_ብርሃን_አድማሱ_ጀንበሬ_ዝክረ_ሊቃውንት በሚለው መጽሐፋቸው እንዲህ ብለው በገጠሙት ግጥም እንጀምራለን!!!


ባንዱ የሚጻፈው በሌላው ሲጻፍ፣
ቋንቋው ተበላሽቶ ይሆናል ጸያፍ።
የጸሐፊ ደዌ ያታሚ መከራ፣
ጠንቅቆ አለማወቅ የፊደልን ሥራ።
እንዳገኙ መጻፍ በድፍረት በመላ፣
የቋንቋ ደረመን የመጽሐፍ ቢስ ገላ።
ንባብ የሚያሳክክ ምስጢር የሚቆምጥ፣
መልክአ ትርጓሜ የሚለዋውጥ።


(የቅኔው አባት ሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ)

#ዘጠኙ_ፊደላተ_ግእዝ

በግእዝ ቋንቋ ተመሳሳይ ድምጸት እና አገልግሎት ያላቸው ፊደላት የሉም። እያንዳንዱ ፊደል የራሱ ድምጸት፣ ትርጉም እና አገልግሎት አለው።

በተለምዶ ሞክሼ ፊደላት እያልን የምንጠራቸው ዘጠኙ ፊደላት <<ሀ፣ሐ እና ኀ፤ አ እና ዐ ፣ ሰ እና ሠ፣ ጸ እና ፀ>> በተለምዶ አንድ አይነት ድምጸት እየሰጠን እንዲሁም ተመሳሳይ አገልግሎት ላይ እያቀያየርን እየተጠቀምን እንገኛለን። ይህ ፍጹም ስሕተት ነው! በግእዝ ሞግሼ ፊደል የሚባል ነገር የለም። ሞክሼ ማለት ተመሳሳ ማለት ነውና። እነዚህ ዘጠኙ ፊደላት በድምጽም በአገልግሎት የተለያዩ ናቸው።
እስካሁን ድረስ ያሉኝን ሁለት መረጃዎች ላቅርብ

፩) መምህር ዘርዓ ዳዊት በመርኆ ሰዋሰው በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ ፲፬ ላይ እነዚህን የፊደላት ድምጽ እንዲህ ብለው ጽፈዋል

ሀ እና አ---- ልል የጒሮሮ ድምጽ
ሐ እና ዐ--- ጠባቂ የጒሮሮ ድምጽ
ኀ ---- የታሕናግ ድምጽ

ሰ፣ሠ፣ጸ፣ፀ --- የጥርስ ድምጽ(በጥርስ የሚነገሩ)

፪) መምህር ደሴ ቀለብ ትንሳኤ ግእዝ በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ ፭ ላይ ሥርዓተ ድምጸታቸውን እንዲህ ብለው ጽፈዋል

አ---- ኢነዛሪ የማንቁርት እግድ
ዐ---- ነዛሪ የጒሮሮ ፍትግ
ሀ ----ኢነዛሪ የማንቁርት እግድ
ሐ----ኢነዛሪ የጉሮሮ ፍትግ
ኀ ----- ነዛሪ የትናሕግ ፍትግ
ሰ ---- ኢነዛሪ የድድ ፍትግ
ሠ --- ነዛሪ የድድ ፍትግ
ጸ ----ኅዩል ኢነዛሪ የድድ ፍትግ



ከላይ እንዳየነው ሁለቱ የግእዝ መምህራን ተመሳሳይ በሚባል ደረጃ አስቀምጠዋል። የመጀመሪያ ላይ የተቀመጠው ጠቅለል ያለ ሀሳብ ሲሆን ሁለተኛው ላይ ግን በዝርዝር የተቀመጠ ነው።
ምናልባት የጥንቱ አማርኛ፣ ትግርኛ እና ትግረ ቋንቋዎች ይህን ስለሚጠቀሙ በቀላሉ ሊገባቸው ይችላል። የጥንቱ አማርኛ እነዚህን ፊደላት በግእዙ አጠራር ነበር የሚጠራቸው። ከጊዜ ሂደት በኋላ አማርኛው እየተቀየረ አንድ አይነት ድምጽ ይዘው በሚገኙበት ወቅት ደረስን።
ትግርኛ እና ትግረ ግን እስካሁን አ እና ዐ ፣ ሀ እና ሐ የተለያየ ድምጽ ሰጥተው ይጠቀሙበታል።


#የግእዝ_ፊደላት_የቦታ_ለውጥና_የሚያመጣው_የትርጉም_ለውጥ

ከላይ የጠቀስናቸው ፊደላት አንዱ በአንዱ ሲተካ ፍጹም የሆነ የትርጉም ለውጥ ያመጣል።

ለምሳሌ፦
መሀረ = አስተማረ
መሐረ = ይቅር አለ

ኀለየ = ዘመረ፣ አመሰገነ
ሐለየ = አሰበ

ማኅሌት = ዝማሬ፣ምስጋና
ማሕሌት (ሕሊና) = ሐሳብ፣ እሳቤ

አመት = ሴት አገልጋይ
ዓመት = ዘመን፣ ጊዜ፣ እድሜ

ሰአለ = ለመነ
ሠዐለ = ሥዕል ሣለ
ሰአሊ ለነ = ለምኝልን
ሠዐሊ ለነ = ሥዕል ሣይልን

ሰርግ = ጋብቻ፣ ሽልማት
ሠርግ = የመስኖ ቦይ፣ መሥረግ

ፈጸመ = ጨረሰ
ፈፀመ = ነጨ
ፍጹም = መጨረሻ
ፍፁም = የተነጨ
ፍፅም = ግንባር

መአደ = ሰፈረ፣ ከነዳ
መዐደ = ገሰጸ፣ መከረ
ምዕዳን = ምክር፣ ተግሳጽ
ምእዳን = መስፈሪያ

መዐተ = ተቆጣ
መአተ = በዛ፣ ብዙ ሆነ
ምእት = መቶ

አደመ = አማረ፣ ተዋበ
ዐደመ = ሴራ አሴረ

ሰረቀ = ሌባሆነ፣ ሰረቀ
ሠረቀ = ወጣ፣ ተገኘ፣ ተወለደ
ምስራቅ = የሌባ መገኛ፣ ሌባ ያለበት ቦታ
ምሥራቅ = የብርሃን፣ የፀሐይ መውጫ

#ልብ_በሉ

ክርስቶስ #ሰረቀ እምድንግል ብሎ አንድ ሰው ቢጽፍ ክርስቶስ ከድንግል ሰረቀ፣ ቀማት፣ወሰደባት እያለ ነው
ሎቱ ስብሐት በትክክለኛው ሲጻፍ ክርስቶስ #ሠረቀ እምንድንግል ነው። ክርስቶስ ከድንግል ተገኘ፣ተወለደ ለማለት።
ስማችሁን #ምስራቅ ብላችሁ የምትጽፉ የሌባ መገኛ ነኝ እያላችሁ ነው ምሥራቅ ነው ትክክለኛው
እግዚኦ መሀረነ - አቤቱ አስተምረን
እግዚኦ መሐረነ = አቤቱ ይቅር በለን


#ማጠቃለያ

ከላይ እንዳየነው የፊደል ለውጥ ሲኖር እጅግ ብዙ ለውጥ አለው። ፊደል ሲቀየር የቤተክርስቲያንን ሥርዓትና ቀኖና የመቀየር እና የማጣመም አቅም አለውና እንጠንቀቅ፣ እንጠንቀቅ እንጠንቀቅ። ከላይ መግቢያ ላይ የተለጠፈውን የመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬን ግጥም ልብ በሉ።

ስለሃይማኖታችን ማወቅ ስንጀምር ከፊደል እጀምር። ንባብ ይገላል ትርጉም ያድናል ይላል ቅዱስ ጳውሎስ። ትርጉም ደግሞ ከፊደል ጠባይ እና አቀማመጥ እና ትርጉም ይጀምራል!!!!

#ማሳሰቢያ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሠለጠንሁ በሚለው የሀገር ውስጥ ማኅበረሰብ ዘንድ እና ከውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አማርኛን ቆፍረው እየቀበሩት እንደሆነ ይታወቃል።
እባካችሁ ትክክለኛውን ፊደል ተጠቀሙ እባካችሁ።
#አለሁ ለማለት #አለው፣ #መጣሁ ለማለት #መጣው፣ #በላሁ ለማለት #በላው የምትሉ፣ #ነህ ለማለት #ነክ የምትሉ!!!

አለሁ እና አለው በትርጒም የማይገናኙ ቃላት ናቸው።

አለሁ= አለኹ፣ ሀለውኩ(በግእዝ)፣ I am alive, I am present
አለው = ቦቱ (በግእዝ)፣ He has, He owns
አለሁ መኖር አለመኖርን
አለው እርሱ ባለቤት መሆን አለመሆኑን የሚያመለክት ነው።

እስኪ ድንግል የተናገረችውን ይህን እዩት

እነሆ የጌታ ባርያ አለሁ እና
እነሆ የጌታ ባርያ አለው
የትርጒም ልዩነቱን ተመልከቱ መርምሩ። ልዩነታቸው የ እና ነው። የትርጒም ለውጡ ግን ብዙ ነው።

ከ "" እና ከ "" ጋር የተጣላችሁ ታረቁ። አለአግባብ ከ "" እና "" ጋር ፍቅር ውስጥ የገባችሁ ፍቅራችሁን በልክ አድርጉት! የሚመጣውን ትውልድም በቋንቋ ከመግደል ራሳችንን እናቅብ!

።።።።፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ባንዱ የሚጻፈው በሌላው ሲጻፍ፣
ቋንቋው ተበላሽቶ ይሆናል ጸያፍ።
የጸሐፊ ደዌ ያታሚ መከራ፣
ጠንቅቆ አለማወቅ የፊደልን ሥራ።
እንዳገኙ መጻፍ በድፍረት በመላ፣
የቋንቋ ደረመን የመጽሐፍ ቢስ ገላ።
ንባብ የሚያሳክክ ምስጢር የሚቆምጥ፣
መልክአ ትርጓሜ የሚለዋውጥ።

(የቅኔው አባት ሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ)

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


#ምንጭ፦
ዝክረ ሊቃውን በሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ
መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በአለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ
ትንሳኤ ግእዝ በመምህር ደሴ ቀለብ
መርኆ ሰዋሰው ዘልሳነ ግእዝ በመምህር ዘርዓዳዊት አድሐና
የአማርኛ ሰዋሰው በብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ
የአማርኛ መዝገበ ቃላት በደስታ ተክለወልድ

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ፈጸምኩ ዘይእዜ ትምህርተ


@geezlisan
1.4K viewsedited  05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-11 12:15:11 @geezlisan
ጓደኞቻችሁን ጋብዙ እንብዛ
ቋንቋችንን እንወቅ
ታሪካችንን እንጠብቅ
874 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ