Get Mystery Box with random crypto!

፩) አፍቀረ= ወደደ ሀ) አነ አፍቀርኩ #ኪያኪ ➳እኔ #አንቺን ወደድሁ። ለ) አንትሙ አፍቀር | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

፩) አፍቀረ= ወደደ

ሀ) አነ አፍቀርኩ #ኪያኪ ➳እኔ #አንቺን ወደድሁ።
ለ) አንትሙ አፍቀርክሙ #ኪያሆሙ ➳ አናንተ #እነርሱን ወደዳችሁ።
ሐ) አንተ አፍቀርከ #ኪያሃ➳ አንተ #እርሷን ወደድህ።
መ) ውእቱ አፍቀረ #ኬያሆን ➳እርሱ #እነርሱን ወደደ።
ሠ) ይእቲ አፍቀረት #ኪያሁ ➳እርሷ #እርሱን ወደደች።


፪) ጸልዐ=ጠላ

ሀ) አነ ጸላዕኩ #ኪያሁ ➳እኔ #እርሱን ጠላሁ።
ለ) ንሕነ ጸላዕነ #ኪያሆሙ ➳እኛ #እነርሱን ጠላን።
ሐ) አንቲ ጸላዕኪ# ኪያየ➳አንቺ #እኔን ጠላሽ።
መ) አንተ ጸላዕከ #ኪያነ ➳አንተ #እኛን ጠላህ።
ሠ) ውእቶሙ ጸልዑ #ኪያሃ ➳እነርሱ #እርሷን ጠሉ።


ሐ) ወሰደ = ወሰደ

ሀ) አነ ወሰድኩ #ኪያከ ➳እኔ #አንተን ወሰድሁ።
ለ) ንሕነ ወሰድነ #ኪያኪ➳ እኛ #አንቺን ወሰድን።
ሐ) ውእቱ ወሰደ #ኪያከ ➳ እርሱ #አንተን ወሰደ።
መ) ውእቶን ወሰዳ #ኪያክሙ ➳ እነርሱ #እናንተን ወሰዱ።
ሠ) ንሕነ ወሰድነ #ኪያሃ ➳ እኛ #እርሷን ወሰድን።


"ጸልዐ" የሚለው ግስ የተለየ አመል ያለው ግስ ነው። እርሱን በቀጣይ ትምህርት ጊዜያት እናየዋለን።
ሳትማሩት በስሕተት ነው የሰለጠፍሁት። ለዚህም እጅግ በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ