Get Mystery Box with random crypto!

፪.፪ የመራሕያን አይነቶች ስድስት ዓይነት መራሕያን አሉ፡፡ እነሱም፦ ፩ ) ባለቤት/ሰዋዊ መ | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

፪.፪ የመራሕያን አይነቶች


ስድስት ዓይነት መራሕያን አሉ፡፡ እነሱም፦
፩ ) ባለቤት/ሰዋዊ መራሕያን
፪ ) ተሳቢ መራሕያን
፫ ) አገናዛቢ ስም መራሕያን
፬ ) አገናዛቢ ቅፅል መራሕያን
፭ ) ድርብ መራሕያን
፮ ) ገላጭ መራሕያን


፩. ባለቤት መራሕያን
(personal pronouns)

ከላይ ያየናቸው ባለቤትን የሚያመለክቱ፣ በስም ቦታ እየገቡ የሚያገለግሉ ተውላጠ ስሞች ናቸው። እነሱም፦ አነ፣ ንሕነ፣ አንተ፣ አንቲ፣ አንትሙ፣ አንትን፣ ውእቱ፣ ይእቲ፣ ውእቶሙ እና ውእቶን ናቸው።


፪. ተስሐቢ መራሕያን
(objective pronouns)

ተሳቢ መራሕያን ድርጊቱ በላያቸው ላይ የተፈጸመ መሆኑን ይገልጻሉ። ማንን ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ተስሐቢ መራሕያንን ይሰጠናል።
ማንን? እኔን፣ አንተን፣ እኛን....

ለምሳሌ፦ አበበ #እኔን መታኝ። በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ የተመታው አካል #እኔ፣ መቺው አካል #አበበ ነው።


ተስሐቢ መራሕያን በቁጥር አስሥር ናቸው
እነሱም፦

፩) ኪያየ = እኔን
፪) ኪያነ = እኛን
፫) ኪያከ = አንተን
፬) ኪያኪ = አንቺን
፭) ኪያክሙ = እናንተን(ወ)
፮) ኪያክን = እናንቺን/እናንተን(ሴ)
፯) ኪያሁ = እሱን
፰) ኪያሃ = እሷን
፱) ኪያሆሙ = እነሱን(ወ)
፲) ኪያሆን = እነርሷን/እነሱን(ሴ)


ምሳሌ ፩፦ ተለወ=ተከተለ

ሀ) አነ ተለውኩ #ኪያከ => እኔ #አንተን ተከተልሁ፡፡
ለ) ንሕነ ተለውነ #ኪያሆሙ => እኛ #እነሱን ተከተልን፡፡
ሐ) አንተ ተለውከ #ኪያየ=>አንተ #እኔን ተከተልህ፡፡
መ) ውእቱ ተለወ #ኬያነ =>እሱ #እኛን ተከተለ፡፡
ሠ) ይእቲ ተለወት #ኪያሃ =>እርሷ #እሷን ተከተለች፡፡
ረ) ውእቶን ተለዋ #ኪያሆን => እነሱ #እነሱን ተከተሉ፡፡
ሰ) አንቲ ተለውኪ #ኪያሁ =>አንቺ #እሱን ተከተልሽ፡፡


ምሳሌ ፪፦ ዘበጠ = መታ

፩) አነ ዘበጥኩ #ኪያከ => እኔ #አንተን መታሁ፡፡
፪) ንሕነ ዘበጥነ #ኪያሆሙ => እኛ #እነሱን መታን፡፡
፫) አንተ ዘበጥከ #ኪያየ=>አንተ #እኔን መታህ፡፡
፬) ውእቱ ዘበጠ #ኬያነ =>እሱ #እኛን መታ፡፡
፭) ይእቲ ዘበጠት #ኪያሃ =>እርሷ #እሷን ተከተለች፡፡
፮) ውእቶን ዘበጣ #ኪያሆን => እነሱ #እነሱን መቱ፡፡ (ለቅርብ ሴቶች)
፯) አንቲ ዘበጥኪ #ኪያሁ =>አንቺ #እሱን መታሽ፡፡
፰) አንትሙ ዘበጥክሙ #ኪያሆሙ => እናንተ #እነሱን መታችሁ።


አነ ዘበጥኩ ኪያከ።
| | |
ባለቤት ግስ ተሳቢ


ጥያቄ፦ በምሳሌው መሠረት በሚከተሉት ቃላት አምስት አምስት ዐረፍተ ነገር ስሩ፡፡

ሀ) አፍቀረ=ወደደ
ለ) ጸልዐ=ጠላ
ሐ) ወሰደ=ወሰደ