በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለተሰጠው መልመጃ መልስ በእውነት ቃለ ሕ | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ለተሰጠው መልመጃ መልስ
በእውነት ቃለ ሕይወት ያሰማልን እጅግ ጥሩ አድርጋችሁ ነው የሠራችሁት!!! በርቱልን!!!
በአንደኛ እና ሁለተኛ መደብ መራሕያን
ሀ) ወደሰ ➜አመሰገነ
፩) አነ ወደስኩ➜ እኔ አመሰገንሁ
፪) ንሕነ ወደስነ➜ እኛ አመሰገንን
፫) አንተ ወደስከ➜አንተ አመሰገንህ
፬) አንቲ ወደስኪ➜አንች አመሰገንሽ
፭) አንትሙ ወደስክሙ➜እናንተ አመሰገናችሁ(ብዙ ወንዶች
፮) አንትን ወደስክን➜ እናንተ/እናንቺ አመሰገናችሁ(ብዙ ቅርብ ሴቶች)
በሦስተኛ መደብ መራሕያን
፯) ውእቱ ወደሰ ➜ እርሱ አመሰገነ
፰) ይእቲ ወደሰት➜እርሷ አመሰገነች
፱) ውእቶሙ ወደሱ➜ እነርሱ አመሰገኑ(ብዙ የሩቅ ወንዶች
፲) ውእቶን ወደሳ➜ እነርሱ/እነርሷ አመሰገኑ (ብዙ የሩቅ ሴቶች
ለ)ነበረ=ተቀመረ
በአንደኛና በሁለተኛ መደብ መራሕያን
፩) አነ ነበርኩ➜እኔ ተቀመጥሁ
፪) ንሕነ ነበርነ➜እኛ ተቀመጥን
፫) አንተ ነበርከ➜አንተ ተቀመጥህ
፬) አንቲ ነበርኪ➜ አንቺ ተቀመጥሽ
፭) አንትሙ ነበርክሙ ➜እናንተ ተቀመጣችሁ
፮) አንትን ነበርክን➜ እናንተ/እናንቺ ተቀመጣችሁ
በሦስተኛ መደብ መራሕያን
፯) ውእቱ ነበረ➜ እሱ ተቀመጠ
፰) ይእቲ ነበረት ➜እሷ ተቀመጠች
፱) ውእቶሙ ነበሩ ➜እነሱ ተቀመጡ
፲) ውእቶን ነበራ ➜ እነርሱ/እነርሷ ተቀመጡ
ሐ) ሀለወ= አለ፣ኖረ
በአንደኛ እና በሁለተኛ መደብ መራሕያን
፩) አነ ሀለውኩ➜እኔ አለሁ
አለው
አለሁ
፪) ንሕነ ሀለውነ➜ እኛ አለን
፫) አንተ ሀለውከ➜አንተ አለህ
አለክ
አለህ
፬) አንቲ ሀለውኪ➜አንች አለሽ
፭) አንትሙ ሀለውክሙ ➜እናንተ አላችሁ
አላቹ
አላችሁ
፮) አንትን ሀለውክን➜እናንተ/እናንቺ አላችሁ (ለብዙ ቅርብ ሴቶች)
በሦስተኛ መደብ መራሕያን
፯) ውእቱ ሀለወ➜ እሱ አለ
፰) ይእቲ ሀለወት ➜እሷ አለች
፱) ውእቶሙ ሀለዉ ➜እነርሱ አሉ
ሀለው
ሀለዉ
፲) ውእቶን ሀለዋ ➜እነርሱ/እነርሷ አሉ