Get Mystery Box with random crypto!

ግሥ በአሥርቱ መራሕያን ሲዘረዘር አንድን ግሥ በመራሕያን ለማርባት የሚከተለውን ሕግ እንጠቀማለን። | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

ግሥ በአሥርቱ መራሕያን ሲዘረዘር

አንድን ግሥ በመራሕያን ለማርባት የሚከተለውን ሕግ እንጠቀማለን።


ምሳሌ የተሰጠን ግሥ ፣ ቀደሰ = አመሰገነ

የሦስተኛ መደብ መራሕያን

#ውእቱ ሲሆን ቅጥያ የለውም። ግሡ እንዳለ ይቀመጣል።
ምሳሌ፦ ውእቱ ቀደሰ= እርሱ አመሰገነ

#በይእቲ ጊዜ ግሡ ምንም ሳይቀየር #ት መጨመር ብቻ ነው። በአማርኛው ደግሞ #ች

ምሳሌ፦ ይእቲ ቀደሰት = እርሷ አመሰገነች

#በውእቶሙ ጊዜ የመጨረሻውን ፊደል ወደ #ካብዕ (ሁለተኛ) ፊደል መቀየር ነው።

ምሳሌ፦ ውእቶሙ ቀደሱ = እነርሱ ቀደሱ። (#ሰ ወደ #ሱ ይቀየራል)

#በውእቱን ጊዜ የመጨረሻ ፊደሉ ወደ #ራብዕ (አራተኛ) ፊደል ይሸየራል።

ምሳሌ፦ ውእቶን ቀደሳ = እነርሱ አመሰገኑ(ለሴቶች) (ሰ ወደ ሳ)

በእንደኛና ሁለተኛ መራሕያን መደብ መራሕያን ጊዜ የተሰጠንን ግስ የመጨረሻውን ፊደል ወደ ሳድስ ከቀየርን በኋላ ቅጥያዎችን እንደመራሕያኑ አይነት እንጨምራለን።

#በአነ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ #ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ኩ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ ቅጥያ አቻው #ሁ
ምሳሌ፦ አነ ቀደስኩ = እኔ አመሰገንሁ ( ሰ ወደ ስ፣ መጨረሳ ኩ መጨመር)

#በንሕነ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ነ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ን

ንሕነ ቀደስነ = እኛ አመሰገን

#በአንተ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ከ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ህ
ምሳሌ፦ አንተ ቀደስከ = አንተ ቀደስህ

#በአንቲ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ኪ ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ሽ
ምሳሌ፦ አንቲ ቀደስኪ = አንቺ አመሰገንሽ።

#በአንትሙ ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ክሙ ቅጥያ ይጨመራል።

ምሳሌ፦ አንትሙ ቀደስክሙ = እናንተ አመሰገናችሁ (ለብዙ ወንዶች)

#በአንትን ጊዜ የመጨረሻው ፊደል ወደ ስድስተኛ (ሳድስ) ፊደል ይቀየርና #ክን ቅጥያ ይጨመራል። የአማርኛ አቻ ቅጥያው #ችሁ
ምሳሌ፦ አንትን ቀደስክን= እናንተ አመሰገናችሁ (ለብዙ ሴቶች)


ምሳሌ ፩) ቀተለ = ገደለ
በ ፲ መራሕያን ሲረባ፦

በአንደኛና ሁለተኛ መደብ መራሕያን ጊዚ "ቀተለ" ከሚለው የመጨረሻ ፊደል #ለ ወደ #ል ትቀየራለች

፩) አነ ቀተልኩ= አኔ ገደልሁ
፪) ንሕነ ቀተልነ=እኛ ገደልን
፫) አንተ ቀተልከ=አንተ ገደልህ
፬) አንቲ ቀተልኪ=አንቺ ገደልሽ
፭) አንትሙ ቀተልክሙ= እናንተ ገደላችሁ
፮) አንትን ቀተልክን= እናንተ ገደላችሁ

በሦስተኛ መደብ መራሕያን
፯) ውእቱ ቀተለ= እርሱ ገደለ
፰) ይእቲ ቀተለት=እርሷ ገደለቺ
፱) ውእቶሙ ቀተሉ=እነርሱ ገደሉ
፲) ውእቶን ቀተላ= እነርሱ ገደሉ

በዚህ መሰረት የሚከተሉትን ግሶች በአሥሩ መራሕያን ዘርዝሩ።

ሀ) ወደሰ = አመሰገነ
ለ) ነበረ = ተቀመጠ
ሐ) ሀለወ = አለ፣ ኖረ