Get Mystery Box with random crypto!

፫. አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን (Possessive Objectives pronouns) አገናዛቢ መራሕ | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

፫. አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን (Possessive Objectives pronouns)

አገናዛቢ መራሕያን (possessive pronouns) ባለንብረትነትን ወይም ባለይዞታነትን ያመለክታሉ።

አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን (possessive adjective pronouns) ደግሞ ቅጽል (adjective) ሲሆኑ ከስም በፊት እየመጡ የባለቤትነትን ወይም ባለንብረትነትን ይገልጣሉ። ሁልጊዜ ከስም በፊት ይገኛሉ።

እሱም የሚከተሉት ናቸው ፦

፩) ዘዚአየ=የእኔ=My
፪) ዘዚአነ=የእኛ=Our
፫) ዘዚአከ=የአንተ=Your
፬) ዘዚአኪ=የአንቺ=Your
፭) ዘዚአክሙ=የእናንተ(ወ)=Your
፮) ዘዚአክን=የእናንተ(ሴ)=Your
፯) ዘዚአሁ=የእሱ=His
፰) ዘዚአሃ=የእሷ=Her
፱) ዘዚአሆሙ=የእነሱ(ወ)=Their
፲) ዘዚአሆን=የእነሱ(ሴ)=Their

ምሳሌ ፩፦ ወልድ=ልጅ (ስም)

ሀ) አነ ውእቱ #ዘዚአሃ ወልድ => እኔ #የእሷ ልጅ ነኝ፡፡
ለ) አንተ ውእቱ #ዘዚአየ ወልድ => አንተ #የእኔ ልጅ ነህ፡፡


ከምሳሌ ሀ) እንደምናየው "አነ ውእቱ ዘዚአሃ ወልድ".. ዘዚአሃ የሚለው አገናዛቢ መራሕያኑ "ወልድ" ከሚለው ስም በፊት ነው የመጣው።

በምሳሌው መሠረት ሦስት ዓረፍተ ነገር ሥሩ።
የተሰጠን ስም፦ ብዕር = ብዕር (እስከብሪቶ)፣ መጽሐፍ = መጽሐፍ

የተሰጠን ግስ፦ ወሰደ = ወሰደ


ውእቱ ወሰደ #ዘዚአየ ብዕር => እርሱ #የኔን እስክብሪቶ ወሰደ።

አነ ወሰድኩ #ዘዚአከ መጽሐፍ => እኔ #የአንተን መጽሐፍ ወሰድሁ

ሀ)
ለ)
ሐ)