Get Mystery Box with random crypto!

፬. አገናዛቢ ስም መራሕያን (Possessive Nouns) እነዚህ መራሕያን ባለንብረትነትን ይገ | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

፬. አገናዛቢ ስም መራሕያን
(Possessive Nouns)

እነዚህ መራሕያን ባለንብረትነትን ይገልጣሉ። ከላይ ካየናቸው አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን የሚለዩት ራሳቸውን ችለው የሚቆሙ ከስም በኋላ የሚገኙ መሆናቸው ነው።

፩) ዚአየ=የእኔ=Mine
፪) ዚአነ=የእኛ=Ours
፫) ዚአከ=የአንተ=Yours
፬) ዚአኪ=የአንቺ=Yours
፭) ዚአክሙ=የእናንተ(ወ)=Yours
፮) ዚአክን=የእናንተ(ሴ)=Yours
፯) ዚአሁ=የእሱ=His
፰) ዚአሃ=የእሷ=Hers
፱) ዚአሆሙ=የእነሱ(ወ)=Theirs
፲) ዚአሆን=የእነሱ(ሴ)=Theirs

እነዚህ መራሕያን ራሳቸው እንደ ስም ያገለግላሉ እንጅ ስም አይከተላቸውም፡፡

ምሳሌ
ሀ) ዝንቱ መጽሐፍ #ዚአሃ ውእቱ፡፡
ይህ መጽሐፍ #የእርሷ ነው
This book is #Hers.

ዚአሃ የሚለው መጽሐፍ ከሚለው በኋላ ራሱን ችሎ እንደ ስም አገልግሏል

ለ) ስመ ዚአየ == #የኔ ስም
ሐ) ዝ ግብር #ዚአሁ ውእቱ፡፡
ይህ ሥራ #የሱ ነው፡፡
መ) አነ ውእቱ ወልደ #ዚአከ፡፡
እኔ የእንተ #ልጅ ነኝ።

የሁለቱን መራሕያን ልዩነት ተመልከቱ
ስመ #ዚአየ = የኔ ስም (አገናዛቢ ስም)
#ዘዚአየ ስም = የኔ ስም (አገናዛቢ ቅጽል)
ዝንቱ መጽሐፍ #ዚአየ ውእቱ (አገናዛቢ ስም)
ይህ መጽሐፍ #የኔ ነው
this book is #mine

ዝንቱ ውእቱ #ዘዚአየ መጽሐፍ (አገናዛቢ ቅጽል)
This is #my book
#የኔ መጽሐፍ ይህ ነው


ማሳሰቢያ፦ ልሳነ እንግልጣር (የእንግሊዝ ቋንቋ) የተጠቀምሁት ብዙ ጊዜ በትምህርት ቤት ስለሚሰጥ ይቀላል ብየ ስላሰብሁ ነው። በአማርኛ ትምህርት ብዙ ጊዜ ስለዚህ ማለትም ስለ መራሕያን/ተውላጠ ስም ብዙ ጊዜ ትምህርቱ አይሰጥም ይልቁንም በእንግሊዝኛ በብዛት ስለሚሰጥ ነው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የሁለቱን ልዩነት ትረዱ ዘንድ....
በዚህ መሠረት የሚከተለውን ጥያቄ በአገናዛቢ ቅጽል እና በአገናዛቢ ስም መራሕያን ሦስት ሦስት ዐ. ነገር ሥሩ።

ሀ) ደብተር = ደብተር

ምሳሌ
አገናዛቢ ቅጽል
ዝ ውእቱ ዘዚአሁ ደብተር
ይህ የእርሱ ደብተር ነው

አገናዛቢ ስም
ዝ ደብተር ዚአሁ ውእቱ
ይህ ደብተር የእርሱ ነው