Get Mystery Box with random crypto!

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gebregziabherkide — ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gebregziabherkide — ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
የሰርጥ አድራሻ: @gebregziabherkide
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.91K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ጽሑፎች ይቀርቡበታል !

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-27 18:41:26
#ለቅድመ_ጋብቻ_ትምህርት_ፈላጊዎች

በጥንድም ኾነ በቡድን መማር የምትፈልጉ ሌላ ዙር ሥልጠና አዘጋጅተናል።

ለበለጠ መረጃ 0912074575 መደወል ይችላሉ!

የክፍያ ኹኔታ፦
+ ለጥንዶች - 4,000 ብር
1.1K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, edited  15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:07:24 ስለ ኹሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።

ደጋግመን እንደምንለው ግን አስበን አስልተን ተቋማዊ በኾነ አሠራር መሥራት ያለብንን ሥራ ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል።

ከመግለጫው እንደምንመለከተውም ለምጣዱ ሲባል የታለፉ ብዙ አይጦች አሉ። እነዚህ አይጦች ግን እስከ ወዲያኛው እንዲያ ይታለፉ ማለት ሳይኾን በአንድነት በምንሠራው ሥራ አደብ የሚገዙ ናቸው። ካልሠራን ግን ነገም በዝተው ተባዝተው ምጣዱን በመስበር ብዙ ዋጋ ያስከፍሉናል።

መምራት የምትችሉና ሥልጣኑ ያላችሁ ምሩን! አሠሩን!
4.0K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 20:14:00 በሰሜን ቢሉ በደቡብ፥ በምሥራቅ ቢሉ በምዕራብ በመሃል አገርም፥ ሃይማኖትን ከራስ ብሔር በታች አድርጎ ወይም ሃይማኖትን የብሔረሰቡ ፖለቲካ መሣርያ አድርጎ ማየት ኑፋቄ ነው። የምሥጢረ ክህነትን ነገረ ሃይማኖታዊ ትምህርት የሚንድ ነው።

ሃይማኖት ባሕልን ቢያከብርም የባሕል ተገዢና ከእርሱ በታች ግን አይደለም። ሃይማኖት ሰማያዊ ባሕል ግን ምድራዊ፣ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ባሕል ግን የሰው ነውና።

የብሔራችን ተቆርቆሪዎች ኾነን ሃይማኖታችንን መሥዋዕት ካደረግነው፥ ወይም ሃይማኖትን ወደ ራስ ብሔርና መንደር ዝቅ ካደረግነው፥ ከማይጠፋው ዘር ወጥተን ወደሚጠፋው ዘር ገብተናል ማለት ነው።

በተለይ እንደ ወላጅ ይህንን ለልጆቻችን ማስተማር ማለት ቀጣዩ ትውልድ ላይ ሃይማኖታዊ ጭፍጨፋ የማድረግ ያህል ነው ብዬ አምናለሁ። ማስተማር በተለይም ለልጆች ከቃልም በላይ በገቢር ነው። ይህን ደግሞ የበለጠ በቤተሰብ ይጠነክራል።

እኔና እርሶ ታዲያ እንደ ቤተሰብ ለልጆቻችን ምን እያስተማርናቸው ይኾን?
4.9K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 20:50:14
ኹሉንም እንዲህ ይመልስልን!
4.8K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 21:48:31

4.3K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 21:18:46
ይህም ይመዝገብ!
5.0K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 19:56:51 በጦርነቱ ያጣነው ክርስቲያን ብዙ ነው፤ እርሱ ጋብ ያለ ሲመስል ደግሞ አሁንም ሌላ ፈተና መጣ።

የመጀመሪያው ርግጡን ተጨማሪ ጥናት ቢፈልግም አፍአዊ ይመስል ነበር፤ የአሁኑ ግን ውስጣዊ ነው።

በዚያም አለ በዚህ አለመጠለፍና አለመውደቅ ግን ከእኛ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል። በመጀመሪያው፥ ከኾነ አካል ጋር ወግኖ ጦርነቱን ማፋፋም ትርፉ ክርስቲያኖችን ማስጨረስ ኾነ። በተግባር የታየ ነገር ስለ ኾነ ሌላ ምስክር አያሻውም። የአሁኑንም መደገፍ ወንጌልን ከማስፋፋት አንጻር ተብሎ ሊታይ አይችልም። ወንጌል እንዲስፋፋ መፈለግና ለዚያ መሥራት አንድ ነገር፥ ፓትሪያርክ እያለ በሌለ ሥልጣንና በሌለ መንበር ጵጵስና መሾምም ሌላ ነገር ነውና።

እንደ ታዘዝነው የእኛ ድርሻ መረጋጋት፣ መጸለይ ነው። በተለይም ለችግሩ መከሰት [በምንም ይገለፅ በምን] የእኔ ድርሻ አለበት ማለት እግዚአብሔር እንዲታረቀን ወሳኝ ነው።

የአበው ድርሻም ተሰብስበው ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ኾነው መወሰን ነው።
3.5K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, edited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 21:54:20 † “ሃላኻህ”አዊ ሕይወት †

“ሃላኻህ” የሚል የዕብራይስጥ ቃል አለ፡፡ ትርጓሜውም አኗኗር፣ አካሔድ፣ ምልልስ ማለት ነው፡፡ የይሁዲ እምነት ከምንም በላይ “ሃላኻህ”አዊ ነው፡፡ ማለትም፥ አንድ የይሁዲ እምነት ተከታይ በአበላሉ፣ በአለባበሱ፣ ቀዳሚት ሰንበትን በሚያሳልፍበት አኳኋን ይለያል፡፡ አንድ ሰው ወደ ይሁዲ እምነት ገባ ማለት በሕይወት ምልልሱ በጠቅላላ እስከ ዘለቄታው ይለወጣል ማለት ነው፡፡ ከላይ በገለፅናቸው አኳኋኖች ራሱን እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ይገልፃል፡፡ በቀን አራት ጊዜ መጸለይ፣ እምነቱን ለልጆቹ ማስተማር ግዴታው ነው፡፡ አንድ አይሁዳዊ ቤተሰብ አይሁዳዊ ኾኖ ለመቆየት በዚህ መንገድ መመላለስ ግዴታው ነው፡፡

እኛም እንደ ኦርቶዶክሳውያን ይህ “ሃላኻህ”አዊ ሕይወት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ በተለይም እንደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ራሱን በቻለ አኗኗር፣ ራሱን በቻለ አካሔድ፣ ራሱን በቻለ ምልልስ የሚገለፅ ሕይወት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡

ርግጥ ነው፥ ስለ ብዙና ስለ ልዩ ልዩ ምክንያት ይህንን ቸለል ብለነዋል፡፡ ኦርቶዶክሳዊ እምነታችንን መሬት ላይ ማውረድ የምንችለው ግን በዚህ በቤተሰባዊ ሕይወት፣ አኗኗርና ምልልስ ነው፡፡ ለአንድ ቀን፣ ወይም ለአንድ ሳምንት፣ ወይም ለአንድ ወር በሞቅታ በመለወጥ አይደለም፡፡ ግጻዌውን በተከተለ መንገድ ከዓመት እስከ ዓመት ብሎም እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ በሚዘልቅ ለውጥ እንጂ፡፡

እንደ ቤተሰብ መጸለይ ብሎም ማስቀደስ፣ እንደ ቤተሰብ ከምሥጢራት መሳተፍ (መቊረብ)፣ እንደ ቤተሰብ ቃለ እግዚአብሔርን ማድመጥ፣ እንደ ቤተሰብ መጾም፣ እንደ ቤተሰብ መመጽወትና የመሳሰሉት ኹሉ የሥነ ምግባር ሰዎች እንድንኾን ሳይኾን ክርስቶሳውያን - ክርስቶስን እንድንለብሰው - ያደርገናልና ይህ እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ “ሃላኻህ” እያልነው ያለነው ይህን ነውና፡፡

ከቤተሰብ አባላት ለምሳሌ ልጆቻችን ነገረ መለኮትን አይረዱም፡፡ በመድረክ ላይ የሚሰጠውን ጥልቅ ትምህርት አይገነዘቡትም፡፡ እግዚአብሔር ማን እንደ ኾነና እንዴት እንደሚመለክ፣ ቅዱሳን እነማን እንደ ኾኑና እንዴት እንደሚከበሩ፣ ክርስቲያን ማለት ምን እንደ ኾነና እንዴት መኖር እንደሚገባው በቀላሉ የሚረዱት በዚህ “ሃላኻህ”አዊ ሕይወት ነው፡፡ ከመብላታችን በፊት ስንጸልይ፣ በልተን ስንጨርስ ስብሐት ስንል - እምነታቸውን ይማሩታል - የእነርሱ መድረክ ይህ ነው፡፡ ይማሩታል ብቻ ሳይኾን በተግባር መኖር ይለማመዱበታል - “ሃላኻህ”አዊ ሕይወት!

እናስ? እናማ ቤታችን እንዲሁ ተሰብስበን የምንኖርበት ብቻ እንዳይኾን እምነታችንን ወደ መሬት ማውረድ የምንችልበት ዓውድን መፍጠር እንዲችል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ስናደርግም እግዚአብሔር እንዲሁ ምናባዊና ሩቅ ሳይኾን ከእኛ በላይ ለእኛ ቅርብ የኾነ አምላክን እናደርገዋለን፡፡ ባልና ሚስት፣ ወላጆችና ልጆች በዚህ መንገድ ስንኖር ቤታችን መንፈሳዊ በዓት ይኾናል፡፡ በቤታችን ውስጥ ቃል ሥጋ ይኾናል፡፡ ዕርቅ ይደረጋል፡፡ ፍቅር ይጸናል፡፡ ድኅነት ይደረጋል፡፡

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
ጥር 13 – 2015 ዓ.ም.
-------
ሼር ብታደርጉት ደግሞ ብዙ ሰው ሊያተርፍ ይችላል!
------
5.3K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 22:59:07 ባልንና ሚስትን አንድ የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው። አንድ የሚያደርገውም በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚከናወነው ሥርዓት ነው። ሥርዓቱም ሥርዓተ ተክሊሉ ብሎም ሥርዓተ ቁርባኑ ነው።

ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በመጋባት ግን ባልና ሚስት አንድ አይኾኑም። መኝታ ተጋርተው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

ስለዚህም፦

አንደኛ፥ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን አንድ የኾኑበትን ምሥጢር በተግባር መካድ ነው።

ኹለተኛ፥ የተባረከ ትዳር አይደለም፤ የበረከት ምንጭ የኾነው እግዚአብሔር የለበትምና።

ሦስተኛ፥ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን መቋቋም አይችልም። መቋቋም የሚችልበትን ጸጋ አልተቀበለምና።

አራተኛ፥ ዝሙት ነው። ለምን ሲባል ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ የሚኾነው ቤተክርስቲያን ስትፈቅድ ብቻ ነውና።
------
ሼር ብታደርጉት መልእክቱ ለብዙ ሰው ይደርሳል!
------
ገብረእግዚአብሔር ኪደ
ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም.
5.7K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 20:26:53 እንደ "ቅራኔ መፍቻ" እኅቱን እየተቆጣ፣ እየሰደበና እየመታ ያደገ ወንድ፥ ሲያገባም "ቅራኔ መፍቻ" ዘዴው ሚስቱን መቆጣት፣ መስደብና መምታት ነው። ሌላ ቅራኔ መፍቻ ዘዴን አይቶ አያውቅማ፤ አልተለማመደማ!

አንዳች ችግር ሲፈጠር ወላጆቿን ወይም ታላቅ ወንድሟን እየዋሸች ያደገች ሴትም፥ ስታገባ ተመሳሳይ ነገር ሲገጥማት እንደ መፍትሔ የምታመጣው ዘዴ ውሸትን ነው። ለምን ሌላ ዘዴ ታመጣለች? ላምጣስ ብትል እንዴት ታመጣዋለች?

ገብረእግዚአብሔር ኪደ

ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም.
2.9K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ