Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን ቢሉ በደቡብ፥ በምሥራቅ ቢሉ በምዕራብ በመሃል አገርም፥ ሃይማኖትን ከራስ ብሔር በታች አድር | ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

በሰሜን ቢሉ በደቡብ፥ በምሥራቅ ቢሉ በምዕራብ በመሃል አገርም፥ ሃይማኖትን ከራስ ብሔር በታች አድርጎ ወይም ሃይማኖትን የብሔረሰቡ ፖለቲካ መሣርያ አድርጎ ማየት ኑፋቄ ነው። የምሥጢረ ክህነትን ነገረ ሃይማኖታዊ ትምህርት የሚንድ ነው።

ሃይማኖት ባሕልን ቢያከብርም የባሕል ተገዢና ከእርሱ በታች ግን አይደለም። ሃይማኖት ሰማያዊ ባሕል ግን ምድራዊ፣ ሃይማኖት የእግዚአብሔር ባሕል ግን የሰው ነውና።

የብሔራችን ተቆርቆሪዎች ኾነን ሃይማኖታችንን መሥዋዕት ካደረግነው፥ ወይም ሃይማኖትን ወደ ራስ ብሔርና መንደር ዝቅ ካደረግነው፥ ከማይጠፋው ዘር ወጥተን ወደሚጠፋው ዘር ገብተናል ማለት ነው።

በተለይ እንደ ወላጅ ይህንን ለልጆቻችን ማስተማር ማለት ቀጣዩ ትውልድ ላይ ሃይማኖታዊ ጭፍጨፋ የማድረግ ያህል ነው ብዬ አምናለሁ። ማስተማር በተለይም ለልጆች ከቃልም በላይ በገቢር ነው። ይህን ደግሞ የበለጠ በቤተሰብ ይጠነክራል።

እኔና እርሶ ታዲያ እንደ ቤተሰብ ለልጆቻችን ምን እያስተማርናቸው ይኾን?