Get Mystery Box with random crypto!

ባልንና ሚስትን አንድ የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው። አንድ የሚያደርገውም በቤተክርስቲያን ውስጥ በ | ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

ባልንና ሚስትን አንድ የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው። አንድ የሚያደርገውም በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚከናወነው ሥርዓት ነው። ሥርዓቱም ሥርዓተ ተክሊሉ ብሎም ሥርዓተ ቁርባኑ ነው።

ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በመጋባት ግን ባልና ሚስት አንድ አይኾኑም። መኝታ ተጋርተው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

ስለዚህም፦

አንደኛ፥ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን አንድ የኾኑበትን ምሥጢር በተግባር መካድ ነው።

ኹለተኛ፥ የተባረከ ትዳር አይደለም፤ የበረከት ምንጭ የኾነው እግዚአብሔር የለበትምና።

ሦስተኛ፥ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን መቋቋም አይችልም። መቋቋም የሚችልበትን ጸጋ አልተቀበለምና።

አራተኛ፥ ዝሙት ነው። ለምን ሲባል ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ የሚኾነው ቤተክርስቲያን ስትፈቅድ ብቻ ነውና።
------
ሼር ብታደርጉት መልእክቱ ለብዙ ሰው ይደርሳል!
------
ገብረእግዚአብሔር ኪደ
ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም.