Get Mystery Box with random crypto!

እንደ 'ቅራኔ መፍቻ' እኅቱን እየተቆጣ፣ እየሰደበና እየመታ ያደገ ወንድ፥ ሲያገባም 'ቅራኔ መፍቻ' | ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

እንደ "ቅራኔ መፍቻ" እኅቱን እየተቆጣ፣ እየሰደበና እየመታ ያደገ ወንድ፥ ሲያገባም "ቅራኔ መፍቻ" ዘዴው ሚስቱን መቆጣት፣ መስደብና መምታት ነው። ሌላ ቅራኔ መፍቻ ዘዴን አይቶ አያውቅማ፤ አልተለማመደማ!

አንዳች ችግር ሲፈጠር ወላጆቿን ወይም ታላቅ ወንድሟን እየዋሸች ያደገች ሴትም፥ ስታገባ ተመሳሳይ ነገር ሲገጥማት እንደ መፍትሔ የምታመጣው ዘዴ ውሸትን ነው። ለምን ሌላ ዘዴ ታመጣለች? ላምጣስ ብትል እንዴት ታመጣዋለች?

ገብረእግዚአብሔር ኪደ

ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም.