Get Mystery Box with random crypto!

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gebregziabherkide — ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gebregziabherkide — ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
የሰርጥ አድራሻ: @gebregziabherkide
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.91K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ጽሑፎች ይቀርቡበታል !

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-01-19 17:51:21 እግዚአብሔር የሁከትና የግጭት አምላክ አይደለም። ስለዚህ አንተም በእግዚአብሔርና በባልንጀራህ ላይ የምታደርገውን ሁከትንና ግጭትን አቁም። እግዚአብሔር እንደ ምን ባለ ባሕርዩ እንደ አዳነህ በማስተዋል ከሰው ኹሉ ጋር በሰላም ኑር። ለምን መሰለህ? "የሚያስተራርቁ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉ" ነው የሚለው (ማቴ. 5:9)። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ናቸው ወልደ እግዚአብሔርን የሚመስሉት፤ አንተም ይህን ብታደርግ እርሱን ትመስለዋለህና ከኹሉ ጋር በሰላም ኑር (ተራረቅ)።

ባልንጀራህ ጎድቶህ ይኾናል። ዳሩ ልንገርህ፥ አንተም ስማኝ! ወዳጄ የምትለው ሰው ሳይቀር በጎዳህ መጠን፥ ምንዳህም የዚያኑ ያህል ብዙ ነው። ክቡር ዳዊት ይህን አስመልክቶ ሲናገር አልሰማኸውምን? “ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ኖረች” ነው ያለው (መዝ.119፥6)። ይህ ፍቅር ነው፤ ይህ ፍቅርም ከሰዎች አስተሳሰብ የራቀ የመጠቀ ነው፤ ቅሩባነ እግዚአብሔር የሚያደርገንም እርሱ ነው። ክፋትን ካለማሰብ በላይ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝው ምንም ምን የለምና። እውነቱን ልንገርህ! ለበደልህ ኹሉ ሥርየትን የሚሰጥህ ይህ ነው፤ ከእስራትህ ኹሉ የሚፈታህ ይህ ነው። ግጭትንና አታካሮን የምንፈጥር ከኾንን ግን ከእግዚአብሔር እንርቃለን። ከግጭትና ከአታካሮ ጥላቻ፥ ከጥላቻም ተዘክሮተ እኪት ይከተላልና።

[ቅ. ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ፊልጵስ. ድር. ፲፬ ]
3.1K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, edited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 11:57:45 አንድ የምንኵስና ሕይወትን ለመኖር የሔደ ወጣት፥ የገዳም ሕይወት ምን ያህል ማራኪ እንደ ኾነ ለአባቱ ጻፈለት፡፡ በገዳሙ በየሰዓቱ ደወል ስለሚደወል እርሱም በየሰዓቱ ለጸሎት እንደሚነሣ፣ ሌሊትም ጭምር ይህ በትግሃ ሌሊት እንዲበረታ እንዳደረገውና እንዲህ እያሉ መኖር እንዴት እንደ ወደደው፥ በትዳር መኖር ግን ይህን ዕድል እንደማይሰጥ በሚያሳብቅ አኳኋን ጻፈለት፡፡ ብልህና አስተዋይ የነበረው አባቱም እንዲህ ሲል መልሶ ጻፈለት፡- “ልጄ! እኔና እናትህ መክሊትህን ስላገኘኸው እጅግ ደስ ብሎናል፡፡ ኹልጊዜ ግን አንድ ነገር አስታውስ፡- በዚህ ዓለም የምንኖር እኛና ሌሎች ብዙ ወላጆችም፥ የልጆቻችንን ዳይፐር ለመቀየር፣ ወተት ካስፈለጋቸው ወተት ለመስጠት ሌሊት ላይ በተደጋጋሚ እንነሣለን፡፡ በኋላ ሲገባን ለካስ የእኛ ቅዱስ ጥሪ ይህ ኖሯል፡፡” በርግጥም ቅዱስ ጥሪ!

ትዳርን እንደ አግባቡ ከኖርንበት፣ እግዚአብሔር የሰጠንን የትዳር አጋሮቻችንና ልጆቻችንን ክርስቶሳዊ በኾነ ፍቅር ከወደድንበት፣ ለቤተሰባችን የምናደርጋቸው ማናቸውም አገልግሎቶች ራሳችንንና ቤተሰባችንን በምግባር በሃይማኖት ለማነጽ ከተጠቀምንበት፥ ይህ ሕይወት ከገዳማዊ ሕይወት ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ እንዲያውም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንደሚነግረን፥ የትዳር ሕይወት ከገዳማዊ ሕይወት የሚከብድበት ማዕዘን አለው፡፡ እንዴት ቢባል ሳያገቡ መኖር እግዚአብሔር እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚገባ እንድናስብ ሲያደርግ፥ አግብተን ስንኖር ደግሞ እግዚአብሔርንም የትዳር አጋርንም እንዴት ደስ ማሰኘት እንዳለብን እንድናስብ ያደርገናልና፡፡ ሚስትንና ልጆችን ደስ ለማሰኘት እግዚአብሔርን ደስ ስለማድረግ ከማሰብ እንዳያናጥበን ብርቱ ትግልን ይጠይቃልና፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ፡- “[ሴት ግን] በመውለድ ትድናለች” ይላል (1ኛ ጢሞ.2፡15)፡፡ ይህ ቃል በብዙ መንገድ ሊተረጐም ቢችልም፥ አንዱ ግን ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ሚና የሚያስገነዝብ ነው፡፡ መውለድ ለዘጠኝ ወራት አርግዞ ከዚያም አምጦ ከመውለድ ይጀምራል፡፡ በዚያ ግን አያበቃም፡፡ ወላጆች ልጅን ወለዱ የሚባሉት በቃ ልጅን እንዲሁ ስለ ወለዱ አይደለምና፡፡ የወለዷቸውን ልጆች ዕለት ዕለት መውለድን ይጠይቃቸዋል፡፡ በየቀኑ በዋናዋና በትንሿ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በማሳደግ እግዚአብሔርን መስለው እንዲያድጉ ማድረግ ልጅን መውለድ ነው፡፡ ከዚህ በላይ መንፈሳዊ ግብር የለም፡፡ አንድ መነኵሴ በገዳም በጸሎትና በሥራ ተጠምዶ የሚሠራውን ቅዱስ ተግባር ያህል፥ በዚህ ዓለም አግብተው የሚኖሩ ክርስቲያኖችም በዚህ መንገድ ሕይወታቸውን ቢኖሩ ቤታቸው “መንፈሳዊ በዓት (ገዳም)” ነው፡፡

ልጆች አስቀድመው እግዚአብሔርን የሚያዩት ወይም የሚያጡት በወላጆቻቸው ነው፡፡ በመንፈሳዊው በዓታቸው ውስጥ እንደሚገባ ሲኖሩ ለልጆቻቸው የመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን ናቸው፤ እግዚአብሔርን በእነርሱ ውስጥ ያዩታል፡፡ በሥጋ ብቻ ሳይኾን በመንፈስም ሲያሳድጓቸው በዚያ ውስጥ ፈጣሪያቸውን ያውቃሉ፡፡ ወደዚህ ዓለም ብቻ ሳይኾን ወደ ዘለዓለማዊው ዓለምም ይወልዷቸዋል፡፡

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
ጥር 9/ 2015 ዓ.ም.
4.1K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 11:57:42
2.6K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 12:55:08
+++ እስከ ቃና ዘገሊላ ድረስ ባዘጋጀንላችሁ ፓኬጅ መጻሕፍትን ይሸምቱ +++

ከዛሬ ከጥር 2 አንሥቶ እስከ ጥር 12 ድረስ ልዩ ቅናሽ አድርገን እንጠብቃችኋለን። በዚሁ መሠረት፦

የሽፋን ዋጋቸው ተደምሮ 7,000 ብር የኾኑትን በ4,900

የሽፋን ዋጋቸው ተደምሮ 6,000 ብር የኾኑትን በ4,200

የሽፋን ዋጋቸው ተደምሮ 5,000 ብር የኾኑትን በ3,500

የሽፋን ዋጋቸው ተደምሮ 4,000 ብር የኾኑትን በ2,800

የሽፋን ዋጋቸው ተደምሮ 3,000 ብር የኾኑትን በ2,100

የሽፋን ዋጋቸው ተደምሮ 2,500 ብር የኾኑትን በ1,800 ብር አድርገን እንጠብቃችኋለን።

በተጨማሪም ትንሿ ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ የሽፋን ዋጋ ባልተጻፈባቸው መጻሕፍት ላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ ልዩ ቅናሽ ስላደረግን ተጠቃሚ ትኾኑ ዘንድ ጋብዘናችኋል።

-------
ባኮስ መጻሕፍት መደብር !

እንዳላነብ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
--------------
#አድራሻችን፦ አምስት ኪሎ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ
ስ.ቁ. 0920888887

https://t.me/Bakosbookstore
3.6K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 11:58:49
ወልድ፥ አምላክነቱን እንደ መቀማት ሳይቆጥረው ልጆቹን (ሰውን) ለማዳን - ስለ ፍቅር - ራሱን ባዶ አደረገ እንላለን (ፊልጵ2:6)። ጋብቻም እንዲህ ነው። ወላጅ ወላጅነቱን እንደ መቀማት ሳይቆጥረው ልጆቹን [እና ራሱን የትዳር አጋሩንም] ለማዳን - ስለ ፍቅር - ራሱን ባዶ የሚያደርግበት ምሥጢር ነው። ራሱን ባዶ በማድረጉ ብዙ መከራ ቢቀበልም ልጆቹን [እና ራሱን የትዳር አጋሩንም] ለማሳደግ መከራውን በደስታ በትዕግሥት የሚቀበልበት ምሥጢር ነው።
-------
3.4K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 19:44:14 በዓለ ልደትን በ "የወደቁት አንሡ የአረጋውያን ማእከል" አብረን እናክብር፡፡ ለማእከሉ ይጠቅማል ብለው የሚያስቡትን ይዘው በመምጣት በዓልዎትን በዓል ያድርጉት፡፡ መገናኛችን ከጠዋቱ 2:45 4 ኪሎ ማለዳ ካፌ ሲኾን፥ በጣም ቢበዛ እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ መርሐግብራችንን ፈጽመን እንመለሳለን!
3.7K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 13:32:48
4.3K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 08:44:31 የልደት በዓልን በወደቁት አንሡ የአረጋውያን ማዕከል

በኮቪድ ምክንያት ለ፪ ዓመታት አቋርጠነው የነበረውና በዓላትን ምክንያት በማድረግ ወደ የወደቁትን አንሡ የአረጋውያን ማዕከል እንሔድ የነበረው መርሐግብር ዘንድሮ እናከናውናለን።

በመኾኑም የምትችሉ በዕለቱ (ቅዳሜ ታኅሳስ 29 ቀን)፦

ጠዋት 2:45 ላይ

አራት ኪሎ ማለዳ ካፌ ተገናኝተን እንሒድ !
6.2K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 07:11:22

4.2K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 12:41:40

4.6K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ