Get Mystery Box with random crypto!

በጦርነቱ ያጣነው ክርስቲያን ብዙ ነው፤ እርሱ ጋብ ያለ ሲመስል ደግሞ አሁንም ሌላ ፈተና መጣ። | ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

በጦርነቱ ያጣነው ክርስቲያን ብዙ ነው፤ እርሱ ጋብ ያለ ሲመስል ደግሞ አሁንም ሌላ ፈተና መጣ።

የመጀመሪያው ርግጡን ተጨማሪ ጥናት ቢፈልግም አፍአዊ ይመስል ነበር፤ የአሁኑ ግን ውስጣዊ ነው።

በዚያም አለ በዚህ አለመጠለፍና አለመውደቅ ግን ከእኛ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል። በመጀመሪያው፥ ከኾነ አካል ጋር ወግኖ ጦርነቱን ማፋፋም ትርፉ ክርስቲያኖችን ማስጨረስ ኾነ። በተግባር የታየ ነገር ስለ ኾነ ሌላ ምስክር አያሻውም። የአሁኑንም መደገፍ ወንጌልን ከማስፋፋት አንጻር ተብሎ ሊታይ አይችልም። ወንጌል እንዲስፋፋ መፈለግና ለዚያ መሥራት አንድ ነገር፥ ፓትሪያርክ እያለ በሌለ ሥልጣንና በሌለ መንበር ጵጵስና መሾምም ሌላ ነገር ነውና።

እንደ ታዘዝነው የእኛ ድርሻ መረጋጋት፣ መጸለይ ነው። በተለይም ለችግሩ መከሰት [በምንም ይገለፅ በምን] የእኔ ድርሻ አለበት ማለት እግዚአብሔር እንዲታረቀን ወሳኝ ነው።

የአበው ድርሻም ተሰብስበው ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ኾነው መወሰን ነው።