Get Mystery Box with random crypto!

Fuad Muna (Fuya)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya) F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya)
የሰርጥ አድራሻ: @fuadmu
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.20K
የሰርጥ መግለጫ

የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 29

2022-09-22 16:30:51 ቀን 17 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
አሁን ትናንትና
ሌላ ሴት አቀፍኩኝ፣ ከሌላ ተጋደምኩ፣
ብዬሽ ስለነበር
ቀንተሽ እስክትመጪ፣ ቆሜ በር ጠበቅኩ።

አልመጣሽም አንቺ ....

የንፋሱ ሽታ
መሳቅሽን ነገረኝ፣ ገርሞሽ ሙከራዬ፣
ተፌዘብኝ አሉ
የአፍቃሪ እብድ ሆኖ፣ ነገረ ስራዬ።

ልብሽ ድሮ ሲያውቀው
በአይኑ አንቺን ያየ፣ እንዳያምረው ሌላ፣
አስቀናለሁ ብዬ
ማላገጫ ሆንኩኝ፣ የኋላ የኋላ።
ምናል ባልሞከርኩት!!

ግን አለሜ ውዴ ....

ይህን ሁሉ ቀናት
ልቤ ሲለጠለጥ፣ በናፍቆት አለንጋ፣
ሰንበሩ አያሳስብሽ
ጩኸቴ አይረብሽም?፣ ግን ተኝተሽ ነጋ?

ዋአአአአአአአይ!! ዋአአአአአአአአአአአአአአአአይ!!

እሪ ስለፍቅርሽ
እሪ ለፈገግታሽ፣ እሪ ለናፍቆቴ፣
መለመን ወደሻል
በምን ልማፀንሽ፣ ምን ልበልሽ እቴ?

አስሬ እየደማ
ሰላም የነሳኝን፣ የልቤ ላይ ቁስል፣
በምን ልጠግነው
ፈገግታሽ ነበረ፣ ጨርሶ የሚያሽል።

አሁን አሁንማ
ቀናት ተጭነውኝ፣ ያነጫንጨኛል፣
ሰላምታቸው እንኳ
የማሽሟጠጥ ቅኔ፣ ሾርኔ ይመስለኛል።

ሲቀኑ ስላየሁ፣ በሞከርኩት ዘዴ፣
ትንሽ ግን ከፍቶኛል፣ ባትቀኚልኝ ውዴ፣
ራቀኝ ‘ማይበት፣ አይኖችሽን ለአንዴ።

እንደው በምትወጂው
ኢዕተካፍ¹ የሚባል፣ በፈጠረው ጌታ፣
ናፍቆትሽን አልቻልኩም
ይብቃህ ብለሽ እዪኝ፣ እንዲያው ለሰላምታ።
በጌታ በረቢ²!!!

በጣም ተናፍቀሻል።

20 ቀን እኮ ብዙ ነው።

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!
***
አገባባዊ ፍቺ
¹ኢዕቲካፍ:– ከመስጂድ ሳይወጡ ለተወሰነ ጊዜ መቆየት፣ በረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ከመስጂድ ሳይወጡ በአምልኮ መጠመድ
²በረቢ:– በጌታ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.7K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 17:12:16 ቀን 16 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ስሚኝማ ፍቅሬ
ምንድነው ቅጣቱ፣ እንደው ለመጠየቅ፣
ባንቺ ወንጀል መቅጫ
ትዝታሽን ሽሽት፣ ከሌላ እቅፍ ብወድቅ?
ምንድነው ቅጣቱ???

በኔ ወንጀል መቅጫ
ነፍስና ስጋዬ፣ እስከሚላቀቁ፣
ዘይት ውስጥ
መንተክተክ ነው፣ የፍርዴ ትልቁ።

አንቺን ካለማየት
የሚበልጥ መንተክተክ፣ ስለማላውቅ እኔ፣
«ነፃ ነህ»
የሚል ነው፣ የፍርዱ ብያኔ።

ትዝታሽን ሽሽት
ያለመደብኝን፣ ተጋደምኩ አንዷ ጋ፣
ባየሽኝ አለሜ
ገላዬን ሰጥቻት፣ ነፍሴ አንቺን ሲያወጋ።

ባየሽኝ ባየሽኝ!!!

ባየሽኝ አለሜ
ፊቱን ሲያዞርባት፣ ወንድነቴ አኩርፎ፣
ከንፈሬ ስትቀፈው
ስንሰቀሰቅልሽ፣ ከማልቀስም አልፎ።

ባየሽኝ አለሜ
ላንቺ ያለኝ መውደድ፣ ሲጨምር ማፍቀሬ፣
የጠረንሽ ዋጋ
የከንፈርሽ ጣዕም፣ ሲታየኝ አስሬ።
ባየሽኝ ባየሽኝ!!!

ባየሽኝ ውዴዋ
ስረዳው ልክሽን፣ ሲገባኝ ልቀትሽ፣
ሌላ አቅፎ ከማደር
እርካታ ሲሆነኝ፣ ውዴ መሽኮርመምሽ።
ባየሽኝ ባየሽኝ!!

ሲያስጠላ ብታዪ፣ ካንቺ ውጪ ማቀፍ፣
ትራስ ሰው ተጋርቶ፣ በሀሳብ ወዲያ መክነፍ፣
ራበኝ ፈገግታሽ፣ ከዳበሰኝ መዳፍ።

ተይ ልቀቂው በያት!!!

ባልቸገረሽ መምጣት
ምናል ባትፈትኚኝ፣ ባትጥጂኝ ከእሳት፣
ምን ያስደስትሻል
ከክብሬ ብጎድል፣ ከሌላ ብሳሳት።

ምን ያደርግልሻል???

ናፍቀሽኛል በጣጣጣም!!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.9K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 18:47:16 ቀን 15 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ሰላም ለከንፈርሽ
ይጠራው ለነበር፣ ስሜን አቆላምጦ፣
ሰላም ለጉራዬ
ፍቅርሽን እያለ፣ ለቀረው ተድጦ።
ሰላም ለሁላችን!!!

አንድ ቀን ፍቅርሽን
በሌላው ቀን ክብሩን፣ ልቤ እያሰላ፣
ከአንዱ የማልፀና
ሁለት ዛፍ ተንጠልጣይ፣ ሆኛለሁ ነሁላላ።

ትዝታሽ ሲረግጠኝ
ሳስብ ናፍቆትሽን፣ ክብሬን ስጥል እዳ፣
ጭካኔሽ ሲመረኝ
አቋሜን ልቀይር፣ ስታገል ስጎዳ።

እንደ ዥዋዥዌ
አቋሜ ሲሳከር፣ ሲለዋወጥ ቃሌ፣
የሞቀበት መድመቅ
የሙንሺድ አቂዳ፣ ሆኖልሻል ውሌ።

ሰላም ለጉንጮችሽ
ቅላት ለወረሱት፣ ስትስቂልኝ ጊዜ፣
ሰላም ለናፍቆቴ
ሽንፈት ላወረሰኝ፣ ላጣላኝ ከወዜ።
ሰላም ለሁላችን!!!

ከእኔ መወላወል
ገዝፎ የገረመኝ፣ የጭካኔሽ ፅናት፣
ምናለ ብትራሪ
እናትም ባትሆኚ፣ ተወልደሻል ከእናት።

ናፍቀሽኛል ብሎ
አደባባይ ቆሞ፣ ፍቅር ለሚተርክ፣
ይህን ያህል ቅጣት
ለየትኛው ወንጀል፣ በምን ስራየ ልክ??

ሲሰቃይ እያየሽ፣ ፍቅርሽን ተርቦ፣
ትቅርብኝ ላይልሽ፣ ውስጡ ፍቅር ዘንቦ፣
ራርቶ መምጣቱን፣ ምን ያዘብሽ አቦ!!

ጅል አርጎኛል ፍቅርሽ ....

ጅል ሆኜልሻለሁ
እጠብቅሻለሁ፣ እያነባ ልቤ፣
ሲቃዬን አፍኜ፣
ጉንጭሽን ሳቅሽን፣ ፍቅርሽን ተርቤ።
እጠብቅሻለሁ።

አታርፍጂ ባክሽ!!

ናፍቀሽኛል እኮ!!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
2.1K viewsedited  15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 19:28:25 ቀን 14 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
እብደተ–ፍቅሬ
እያጣረሰው፣ ልቤን ከአዕምሮ፣
ዝቶብሽ ነበር
ሰካራም ቃሌ፣ ትናንት አምርሮ።

ዚክር አስክሮኝ
ሞቅታ ገፍቶኝ፣ ላወጣሁት ቃል፣
ይቅርታ ፍቅሬ
ልቤ እንዳይለው፣ ልብሽም ያውቃል።

ዛትኩብሽ አይደል??? ሳስቅ!!!

ናፍቆትሽ ፍሙ
ልቤን እንደ እሳት፣ እየረገጠው፣
ረሳሁሽ ብል
ፍቅርን ያየ፣ ምን ይለኛል ሰው??

እንኳን በቅፅበት
በአንዲት ሰለዋት፣ ልረሳሽ ቀርቶ፣
ድቤው ሲደቃ
ሙስበሀሽ ታየኝ፣ አይኔ ላይ መጥቶ።

ሰለዋት ሲደምቅ
ኑሩ ሲከበን፣ ሀድራ ሲደራ፣
አንቺን ፍለጋ
ሴቱን አሰስኩት፣ ተራ በተራ።

እንኳን ልረሳሽ
ራምሳ ሰምቼ፣ ትዝታሽ ባሰ፣
ዚክሩን ሁሉ
አንቺ ከንፈር ላይ፣ ልቤ አስታወሰ።

ረስቶኛል ብለሽ
ቅንጣት መጠርጠር፣ አይግባ ልብሽ፣
እንኳንስ አጥቶ
አብሮሽ ሆኖ እንኳ፣ አይኔ አይጠግብሽ።

ሲባል ሰምቼ፣ ላለፍኩት ድንበር፣
ትልቅ መሀርታ፣ በልብሽ ይደር፣
ራሪልኝ ውዴ፣ ቁጣሽ አይምረር።

እንደነገርኩሽ ....

እንኳን ልረሳሽ፣
ናፍቆት ጎጆውን፣ ቀልሶብኛል፣
የፍቅርሽ ረሀብ
እጅጉን ብሶ፣ አሳምሞኛል።

በጣጣም ናፍቀሽኛልልል!!!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው።

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
2.4K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 18:40:31 ቀን 13 ሳላይሽ
(ፉአድ ሙና)
.
ናፍቆትሽን ላረሳሳው
ተጥጄያለሁ፣ ሀድራ ደጃፍ፣
ይሽር ይዟል
ያሳመምሽኝ፣ የቁስሌ ጫፍ።

ሙሂቦቹ ሲንሳፈፉ
በሰለዋት፣ ሰርተው ታንኳ፣
ተሳፈርኩኝ
ረሳሁሽ፣ ትንሽ እንኳ።

የጎዳሽው ስሱ ልቤ
ፍቅር ጠጣ፣ ራምሳ ሰምቶ፣
የአይኑ ረሀብ
በረደለት፣ ወንድም አይቶ።

ቁጭ ብድግ
ከወንድም ጋር፣ ሩህ ገጥማ፣
መረቀነች
ናፋቂ ልብ፣ ዚክር ቅማ።

ሲታይ ቢመስል፣ የማልረሳሽ በቀላሉ፣
ትንሽ ዚክር፣ ሰጠኝ ጤና አጀብ በሉ፣
ራቀ ያልኩት ደስታ መጣ ነቢ ቢሉ።

በቀላሉ!!!

ነቢን ዘክሬ
ትንሽ እንኳን፣ ካሸነፍኩት ትዝታሽን፣
ተጠንቀቂ
በተስቢሁ እንዳልጠርገው ናፍቆትሽን።

ከልቤ ላይ
ድርሻሽ ቦታ እንዳያጣ፣
ኩራቱን ተይ
ልይሽና ሀሴት ይምጣ።

ናፍቀሽኛል ግን!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
2.6K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 18:48:27 ቀን 12 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ውበትሽን ፃፍኩ
ደግ ተባለ፣ ተመሰገነ፣
ባህሪሽን ሳልኩ
ሰዉ አፉ ላይ፣ እጆቹን ጫነ።

ናፍቆትሽን ደማሁ
ህመሙን ‘ሚያውቀው፣ አብሮኝ አነባ፣
እብደቴን ነገርኩ
ቀልዬ ታየሁ፣ እንደገለባ።

ላንቺ ነው ብዬ
ሁሉንም ቻልኩት፣ ሆዴን አስፍቼ፣
መች ያውቁትና
ምን እንደሆንኩኝ፣ በሬን ዘግቼ።

ሰው ያለሀፍረት
ሲያተራምሰው፣ ሴቱን በአይነቱ፣
ነብሴን ገታሁኝ
ፍቅሬን አክብሬ፣ ቀረሁ ከስንቱ።

ተራራ እኔነት
እግርሽ ስር ወድቆ፣ ሆነልሽ ትቢያ፣
ወግ ለምን ይቅር
ተሸንፌ አይደል፣ «ተነሳ» በያ።

ራሱን ሰጥቶ
አይንሽን ማየት፣ ሀሴት ለሆነው፣
የሚወድሽ ላይ
ክንድን ማበርታት፣ መኩራቱ ምነው?

ሲቃ ሮሮዬ፣ ከሆነሽ ደስታ፣
ትንሽ ካላዘንሽ፣ ካልሰጠሽ ዴንታ፣
ራቀኝ ብትይ፣ ሚዛን አትሞዪም የማታ ማታ።

ጉራ ብቻ!!!

አንቺን ርቄ
ላይቻለኝ፣ መሄድ ቆሞ፣
ዝቼ ቆዘምኩ
የዛተብሽ፣ ልቤ ታሞ።

ናፍቀሽኛል!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
3.0K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 16:25:57 ቀን 11 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
የልቤ ንግስት
የአይኔ ማረፊያ፣ የነገ ህልሜ፣
አታይኝም ወይ
በናፍቆት ደዌ፣ ነብሴን ታምሜ?

አታይኝም ወይ ....

አልታይም ወይ
ከሰው ከራሴ፣ ተኮራርፌ፣
ፍቅርሽን እያልኩ
ነብሴን ስወጋ፣ የስቃይ መርፌ።

ቀርተሻል  እንዴ?

ቀርተሻል እንዴ?
እንደፈራሁት፣ እንደ ስጋቴ፣
ረስተሽኛል?
ትዝ አላለሽም፣ ፍቅር ስስቴ?

እኔ ግን ውዴ ....

ያዕቁብን ሆኜ
ደጁን አያለሁ፣ ሆነሽ ዩሱፌ፣
እጨልፋለሁ
«ፈሰብሩን ጀሚል»¹፣ ከሚለው ብፌ።
አላሁ ሙስተዓን²!!

እኔ ግን ፍቅሬ ...

ጅል እስኪያሰኘኝ
የቂን³ ለሌለው፣ ቅርብ ጠርጣሪ፣
ጠረንሽ ቀርቦ
እየማግኩት ነው፣ መንገድ ጀምሪ።

ልክ እንደ ያዕቁብ
ከፊቴ ቆመሽ፣ ያየሁሽ ለታ፣
ይበራል አይኔ፣
ይቻልልኛል፣ ዳግም ፈገግታ።

ቶሎ ቶሎ ነይ ....

ቶሎ ነይልኝ
ምን ባልመጥንሽ፣ ባልሆንም መሪ፣
የፍቅርን ልኬት
ከረሱሉ ልጅ፣ ከዘይነብ ቅሪ።

ምናቤ ሰፍቶ ....

ሲቀራ ሰምተሽ፣ የፍቅር ኪታብ፣
ትገቢ እንደሆን፣ ከሙሂቦች ባብ፣
ራርተሽ ስትመጪ፣ ያይሻል በሀሳብ።
ቶሎ ቶሎ ነይ!!!

ሚሊየን ምክንያት
ቢቆም ከፊቴ፣ ሊነሳኝ ተስፋ፣
እጄን አልሰጥም
የእኔ እንድትሆኚ፣ በዱዓ ልልፋ!!

አልቆርጥም ተስፋ!!

ናፍቀሽኛል በጣም!!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው።

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
***
አገባባዊ ፍቺ
¹ ፈሰብሩን ጀሚል:– መልካም ትዕግስት (ከያዕቁብ ዐሰ ንግግር)
² አላሁ ሙስተዓን:– መታገዣዬ አላህ ነው (ከያዕቁብ ዐሰ ንግግር)
³ የቂን:– መመካት ላይ የተመሰረተ እርግጠኝነት
.
@Fuadmu
@Fuadmu
@Fuadmubot
3.2K viewsedited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 19:43:37 ቀን 10 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ናፍቆትሽ ብሶ
ቢነሳኝ ሰላም፣ ቢያሳጣኝ ጤና፣
እግሬን ሳላዘው
ወዳየሽ ቦታ፣ ተነስቶ አቀና።
ወደ ትዝታው ....

ካፌው ጋ ደረስኩ ....

ገና ከሩቁ፣
ጠረንሽ ገባኝ፣ ማግኩሽ በደስታ፣
ተንደረደርኩኝ፣
ቁጭ ወዳልሽበት፣ ወዳንቺ ቦታ።
ፍቅሬ አልነበርሽም።

ወንበሩ ነበር ....

ወንበሩ ነበር
ከእኔ ታድሎ፣ የነካካሽው፣
ውቡ ገላሽን
ቅንጣት ሳትሰጊ፣ ተቀበል ያልሽው።
ነበር ወንበሩ ....

ሳምኩት አቅፌ ....

ሳምኩት እንጨቱን
ገላሽን ነክቶ፣ ለብሷል ፀዓዳ፣
ጠረንሽ አለው
ናፍቆት ያብሳል፣ ገባሁኝ ዕዳ።

ሳቅኩኝ እየጮህኩ
አስተናጋጇ፣ መሰላት ያበድኩ፣
ተደፋሁና
ጠረጴዛው ላይ፣ መንሰቅሰቅ ጀመርኩ።

ትወደኛለች .... ትወደኛለች .... ታገኘኛለች ....

አጉተመተምኩኝ
አይኔ በእንባ፣ እየታጠበ፣
አንቺ ‘ምትወጂው
«ፋንታ ኦሬንጁ» ፣ ፊቴ ቀረበ።

ጠጣሁት በአንዴ ....

ጠጣሁት በአንዴ
ውበት ሀፍረትሽ፣ ከአይኔ ተስሎ፣
ከነብሴ ጅማት
ሳቅሽ ‘ሚያኖረው፣ ህይወቴ ጎድሎ።
ጠጣሁት በአፍታ ....

ያየኛል ሰዉ ....

ሲቀር ይቀራል፣ ይየኛ ደግሞ፣
ትንሽ አያውቅም፣ ህመሜን ታሞ፣
ራራ አዘነ፣ መች ያውቃል ጠቅሞ??
ይየኛ!!!

ጀመረኝ እንዴ?

ጀመረኝ እንዴ ....
አበድኩኝ መሰል፣ እንደታማሁት፣
በሀዘኔታ
ሰዉ አይኑን ተክሎ፣ ሲያየኝ አየሁት።
አበድኩኝ እንዴ??? 

አላበድኩም .... አላበድኩም .....

ናፍቃኛለች  ..... ትመጣለች .....

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
@Fuadmubot
3.1K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 17:52:21 ቀን 9 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ከእህል ሳልናካ
አየሁት ፎቶሽን፣ ገና ከመንጋቱ፣
አጃኢብ አሰኘኝ
ሺ ጊዜ እየታየ፣ አለመሰልቸቱ።

ፎቶሽን እያየሁ
ደነቀኝ ገረመኝ፣ የጌታዬ ስራ፣
በረቂቅ ጥበቡ፣
ትንሹ ገላሽ ላይ፣ እልፍ ውበት ሲዘራ!!

የጌታዬ ነገር
ቢሰማ ቢነገር፣ ቢከተብ አይበቃ፣
በምንድን ጥበቡ
ትንሿ ፊትሽ ላይ፣ ገጠመ ጨረቃ?

እንዴት ቢጠበበው
ይሁን ብሎ አዘዘ፣ ልብን እንዲነካ፣
ሳትኖሪ እንዲጨልም
ስትስቂ ስትስቂ፣ አለም እንድትፈካ።

ጥርስሽ ይገርመኛል ....

እንደ አሰካኩ
አይደረደሩም፣ መልዓክት ራሱ፣
እንደ አነጣጡ፣
አያጥበረብሩም፣ አንቺን ካልተዋሱ።

ሱብሀነላህ አልኩኝ ....

ይመስገን ኢላሂ
የውበቷን ንግስት፣ ላሳየኝ አውርዶ፣
ከሁረልአይን መሀል
ሊያውም አለቃዋን፣ ወደ ምድር ሰዶ።
ተመስገን ኢላሂ!

ፎቶሽን ዘጋሁት ....

እንባ ተናነቀኝ
ድምፅሽ የናፈቀው፣ ጮኸብኝ ጆሮዬ፣
አይኔ አመል አወጣ
ፊቷን አምጣ ብሎ፣ አለብኝ እዬዬ።

ናፈቅሽኝ መዓረይ¹!

ሲቀር ጨዋታው፣ በአንድ ላይ ሆነን የምንደምቅበት፣
ትናንት ሲናፍቅ፣ ገደብ ሳይዘን ያወራንበት፣
ራበኝ ነገ፣ ሳቅሽን አይቼ የምፈካበት።

ፍቅረይ²  ....

ናተይ ወርሂ ³፣
ልቤን አሞኝ፣ እያት ብለው አዘውኛል፣
ብርሀነይ⁴፣
ሳልሞትብሽ፣ አንዴ ባይሽ ይሻለኛል።

ናፍቀሽኛኛኛል!!!!! ዋዋዋይይይይ!!!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው።

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!
***
አገባባዊ ፍቺ
¹ መዓረይ:– ማሬ
² ፍቅረይ:– ፍቅሬ
³ ናተይ ወርሂ:– የኔ ጨረቃ
⁴ ብርሀነይ:– ብርሀኔ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
@Fuadmubot
3.3K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 18:10:10 ቀን 8 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ሳምንት ተሳበ
ጨረቃ ፊትሽ፣ ካበራኝ ደምቆ፣
የሳቅሽ ጨረር
ካጥለቀለቀኝ፣ ከጥርስሽ ፈልቆ።
አዘገመ ቀን!!!

ሳምንት አይመስልም
ከጎደልሽብኝ፣ ከጆሮ ከአይኔ፣
ክፍለ ዘመን ነው
በናፍቆት ሂሳብ፣ በመውደድ ቅኔ።

ፍቅርሽን ሳለቅስ
የሰማኝ አባሽ፣ ወሬ ዘዋሪ፣
ሌላ ሴት እንዳይ
ይጠቁመኛል፣ ድንብር መካሪ።

እንዴት ላስረዳ
ሽባ እንደሆንኩኝ፣ ፍላጎት ሸሽቶ፣
እንደማይችለው
ልቤን ማስከፈት፣ ሌላ አንኳኩቶ።
እንዴት ልናገር????

እሺ አልኳቸው ....

እሺ አልኩና
"ቆንጆ" ያሏትን፣ ቀረብኳት ለአፍታ፣
ጥፍርሽ ናፈቀኝ
ከሙሉ አካሏ፣ ከሰውነቷ።

እንደው ቢጨመቅ
ሺህ ሴቱ፣ በአንዴ፣
ሌላውን ተይው
ጥፍርሽን ማከል፣ ይችላል እንዴ?

ሀፍረትሽ ውዴ
ያንቺን መሽኮርመም፣ የቀመሰ አይኔ፣
ሴትነት ሲጎድል
እንዴት ይታገስ፣ በምንድን ወኔ?

ሺህ ሴት ከሚያገኝ
‘ሚወድሽ ልቤ፣ ካንቺ ተነጥቆ፣
ቢያይ ያረካዋል
አይንሽን ለአፍታ፣ መንገድ ጠብቆ።

ሲቀራ¹ የሰማ የመውደድ ኪታብ²፣
ትንሽ ያወቀ የፍቅርን ሂሳብ፣
ራርተሽ መጥተሽ ያይሻል በሀሳብ።
እንዳትቀሪ።

አልሆነልኝም
ሌላ ሊተካው፣ ያንቺውን ቦታ፣
ላግኝሽና
ዳዒም³ አይንካው፣ ልቤን ቅሬታ።
ጎጆ እንመስርታ!!!

ናፍቄሻለሁ!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!
****
አገባባዊ ፍቺ
¹ ሲቀራ:– ሲነበብ
² ኪታብ:– መፅሀፍ
³ ዳዒም:– ዘለዓለም
.
@Fuadmu
@Fuadmu
@Fuadmubot
3.7K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ