Get Mystery Box with random crypto!

Fuad Muna (Fuya)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya) F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya)
የሰርጥ አድራሻ: @fuadmu
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.20K
የሰርጥ መግለጫ

የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2022-09-28 07:22:46 ቀን 3 ሳላወራሽ ....

በፉአድ ሙና
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
431 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 08:54:02 ቀን 2 ሳላወራሽ ....

በፉአድ ሙና
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
849 views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 18:01:36 ቀን 21 ....
(ፉአድ ሙና)
.
አልሀምዱሊላህ
ምንም ቢከብደው፣ ልቤ ስሜቱ፣
እንባዬ ቢረግፍ
እርግጥ ቢሆንም፣ ወዶ ማጣቱ።
አልሀምዱሊላህ!!!

አልሀምዱሊላህ
አላማርርም፣ አጣኋት ብዬ፣
ብዙ ሰው ሞልቶ
ለቅፅበት እንኳን፣ አይኗን ያላዬ።
አላማርርም!!!!

ዛሬ በጊዜ
አይኖቿን ላየው፣ ጉጉት ጎርሼ፣
ቀጠሮው ቦታ
በናፍቆት ፈረስ፣ መጣሁ ደርሼ።

አልሜ ነበር
ልቤን ሲያበራው፣ ፍካታም ፊቷ፣
እንባ አደለችኝ
ፍቅሬን ገፋችው፣ አወይ ክፋቷ።

ወገቤ ዛለ
ከአደባባዩ፣ ቆሜ የዋልኩበት፣
እግሬ በረከ
የማትመጣ ሴት፣ የጠበቅኩበት።

ምን ነበር እንደው
አግኝታኝ ቢሆን፣ ለአፍታ ብትመጣ፣
ባየሁት ፊቷን
የአይኔ ረሀብ፣ ቀዷ በወጣ።

ጨከነች ውዴ
ግድ አልሰጣትም፣ የፍቅሬ ሮሮ፣
ሌላ መርጣለች
አልይህ አለች፣ ቅጣቷ ከርሮ።

አልሀምዱሊላህ
አላማርርም፣ ሰጥቶኛል ብዙ፣
የእኔው ጥፋት ነው
ካላጣሁት ሴት፣ በእሷ መያዙ።
አልሀምዱሊላህ!!!

ይበለኝ እሰይ
ድሮም ላይሆነኝ፣ ሰው መውደድ ከቶ፣
ስቃይ ቀመሰ
ቆፍጣናው ልቤ፣ ዛሬ እጁን ሰጥቶ።

ጨክነሽብኝ
ብትፈርጂብኝም፣ ላትሆኚ የኔ፣
መልካም ይግጠምሽ
ባንቺ መጨከን፣ አልችልም እኔ።

ከሳቅሽ በላይ
ይመር ህይወትሽ፣ በረከት ይብዛ፣
የአይን ማረፊያ
ውብ ልጅ ይብዛበት፣ የፍቅርሽ ታዛ።

ባንቺ ተይዤ
ልቤን ባይሞላም፣ ሌላ ሴት ከቶ፣
አክመዋለሁ
በጌታዬ ስም፣ አይቀርም ሞቶ።

አንቺ የሌላ ከሆንሽ
አልፃፈኝምና፣ እኔን ላንቺ ብሎ፣
ደስ ብሎሽ ኑሪ
ህመሜን ላስታምም፣ እንዳይገለኝ ቶሎ።

ሲቀር ቢያመኝም፣ ያንቺ መሆኔ፣
ትልቅ ቢሆንም፣ ሰባሪ መቅኔ፣
ራሪው ጌታ፣ አላለም ለኔ።

አልሀምዱሊላህ
ናፈቅኩኝና፣ ዘገንኩኝ መርዶ፣
በእንባ ታጠብኩኝ
አፍቃሪ ልቤ፣ ያላቅሙ ወዶ።

ከእኔ መንገብገብ
የጌታዬን ቃል፣ አምናለሁና፣
እሞክራለሁ
በውሳኔው ውስጥ፣ ካገኘሁ ደህና።

ደህና ሁኚ!!!

20 ቀን ለእኔ በጣም ብዙ ነበር።

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
***
ተፈፀመ።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
952 views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 19:54:27 ቀን 20 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ለምነህ ለምነህ
ለይሉን አንግተህ .....
እንዲሁም አልተወህ
ጨረቃ ሰጠህ።

ለምነህ ለምነህ
አላሁ አላሁ ....
ለይሉን አንግተህ
አላሁ አላሁ ....
እንዲሁም አልተወህ
አላሁ አላሁ ....
ንግስቷን ሰጠህ።

መልዓክት ቀርበው
አጠቡት ገላየን፣ ገና በጠዋቱ፣
አርከፈከፉብኝ
የገነት ፀዓዳ፣ ሽቶ በየአይነቱ።

ልብስ አዘጋጁልኝ
ለክብርሽ እንዲሆን፣ አምሮ የተሰራ፣
መልዓክ የሰፋው
በጥበበ ሰማይ፣ ፊ አለመ ሰራ።

ከፈቱልኝ ኪታብ
ጥንት የተከተበ፣ ምድር ሳትሰራ፣
የደረቀ ቀለም
እሷን ላንተ ይላል፣ የኻሊቁ ስራ።

ለምነህ ለምነህ
በዱዓ ጦዘህ፣
አላሳፈረህም
ሽሽጓን ሰጠህ።

ነብስና ስጋዬ
እስኪነጣጠሉ፣ ከእንቅልፍ እስክፋታ፣
ሺ አመት ረዘመ
የሀያ ቀን ቅጣት፣ የልቤ ስሞታ።

ወዮልኝ ወዮልኝ
የፊትሽ ኑርማ፣ ሲደቀን ከፊቴ፣
መቅለጥ እፈራለሁ
ሻማ አርጎኛል ፍቅርሽ፣ ራሪልኝ እቴ።

ነገ ሊበራለት
ዛሬ እንዳላስቻለው፣ እንደ አይነ በሲሩ፣
የናፍቆትሽ እሳት
ሲደርስ የጠናብኝ፣ ምንድነው ሚስጥሩ?

መልዓክቱ እንኳን
ለነገ ቀጠሮ፣ አጣጠቡኝ ዛሬ፣
ቢወዱሽ ነው እንጂ
አርፍጄ አላውቅም፣ እኔ አንቺን ቀጥሬ።

ለምነህ ለምነህ
ለይሉን ተኝተህ፣
አዛኝ ነው ጌታህ፣
እሷን ጀባ አለህ።

ሲደርስ ጠና፣ ያንቺማ ነገር፣
ትንሽ አይቀንስ፣  ቆርጦልኝ አይቀር፣
ራደልሽ ልቤ፣ የሩሄ ማገር።

የናፍቆት ስሌት፣
ደስታ ደረሰ፣ ቀኑ ተሞላ፣
ነገ ነው ሀሴት
ከፊቷ እንጀራ፣ ፍቅር ‘ሚበላ።

ለምነህ ለምነህ
ቀን ሌት አልቅሰህ፣
አላዋረደህም
በእሷ አበሰልህ።

ናፍቀሽኛል ዛሬም ....

20 ቀን እኮ ብዙዙዙ ነው።

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
957 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 00:02:19 Live stream finished (1 hour)
21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 22:05:24 ተጀምሯል ሊልኩን በመንካት ይቀላቀሉ
https://t.me/fuadmu?livestream=0f75e64042f8675505
824 viewsedited  19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 22:04:55 Live stream started
19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 16:54:10 ቀን 19 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
የቀናት ቁልል
ፍርክስክስ አለ፣ በሰብር¹ ዶማ፣
ግርዶው ተነስቶ
አይኖቿን ላይ ነው፣ ያልሰማህ ስማ!!

ስልችትችት ካለኝ
የናፍቆት ለቅሶ፣ የመራብ ዜማ፣
ነጃ² ልባል ነው
ተስቢህ³ ይጀመር፣ ተክቢር⁴ ይሰማ!!

ሀሳብ ይዞኛል
ምን እንደማደርግ፣ ሲቀርበኝ ፊቷ፣
ሚስክ⁵ ጠረኗ
ዳግም ሲያውደኝ፣ ስሾር በስልቷ።

ከሁሉም ፀንቶ
እኔን ያሰጋኝ፣ ፍርሀት ያለብኝ፣
ስትደቅንብኝ
ጨረቃ ፊቷን፣ አተነፋፈስ እንዳይጠፋብኝ!!

ደግሞ እስላለሁ
ግንባሬ ሲረጥብ፣ ሊቆጣጠረው ተነስቶ ቁዋ⁶፣
አብሽር ስትለኝ
ስትጠርግልኝ፣ ፍርሀተ–ላቤን በአባያዋ⁷።

ይሰማኛል ቃሏ ....

«መለክተኒ⁸
ያ ፉአዲ⁹፣ መለክተኒ ፍቅሬ ሁቢ¹⁰፣
አነ ሲትሩክ¹¹
መሽግ በኔ፣ ልከልልህ ያ ሀቢቢ¹²።»

ምሽሽሽግ ነዋ!!!

አወይ ሀሴት
አቤት ደስታ፣ ስቆላመጥ በአንደበቷ፣
ስብለጨለጭ
ኑር¹³ ስቀባ፣ ሲጋባብኝ ደም ግባቷ።

ሲቃ አለው፣ ፌሽታ ራሱ፣
ትንሽ ቀርቶት፣ ለድግሱ፣
ራቀኝ ለኔ፣ የዕረፍት ትራስ መንተራሱ።

ሀቢበቲ¹⁴
ቁረተል አይን¹⁵፣ የልብ እረፍት፣
ናፍቆት ብሷል
ቀኑ ደርሶ፣ ጨንቋል ህይወት።
ክፉ ናፍቆት!!!

ናፍቀሽኛል ብዙ!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!
****
አገባባዊ ፍቺ
¹ሰብር:— ትዕግስት
²ነጃ:– ነፃ
³ተስቢህ:– አላህን ማወደስ
⁴ተክቢር:— አላህን ማላቅ
⁵ሚስክ:– የጀነት ሽቶ
⁶ቁዋ:– ሀይል
⁷በአባያዋ:– የሴቶች ልብስ
⁸መለክተኒ:– ያንተ ሆኛለሁ፣  ወስደኸኛል፣ እዘዝብኝ፣ ምሳሌ:– አስመልኬሀለሁ አ‘ርገው እንደሚሆን
⁹ያ ፉአዲ:– ልቤዋ፣ እንደ ፍቅር መግለጫ
¹⁰ሁቢ:– ውዴ
¹¹አነ ሲትሩክ:– መሸሸጊያህ ነኝ
¹²ሀቢቢ:– ውዴ
¹³ኑር:– ብርሀን
¹⁴ሀቢበቲ:– ውዴ
¹⅝ቁረተል አይን:– የአይን ማረፊያ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.4K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 08:59:38 በዛሬው የፈገግታ መጅሊሳችን
.
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን በተመለከተ ምን ታዝበዋል?

እርስዎ ባለቤትዎ ተጨማሪ ሚስት እንዲያገባ ይፈቅዳሉ?
ወንድ ከሆኑ ደግሞ ተጨማሪ የማግባት ፍላጎት አለዎት?

በዚህ ላይ በሰፊው እንወያያለን።

የስነ ፅሁፍ ስራዎች ይበረታታሉ።

ከምሽቱ 3:30 ላይ እንገናኝ።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
595 views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 17:02:19 ቀን 18 ሳላይሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
ቀኑ ቀረበ
የራበሽ አይኔ፣ ሊያገኝ ጤና፣
በድምፅሽ ተዓምር
የልቤ እጥፋት፣ ዳግም ሊቃና።
ቀረበልኝ ቀን!!!

ልክ እንደዩሱፍ ....

ቀናት ጠብቆ፣
እንዳከበረው፣ ከጉድጓድ ወስዶ፣
ሊያነግሰኝ ነው
በፍቅርሽ ዙፋን፣ መነጠል ወርዶ።

ልክ እንደ ኢሳ ....

ሁን በሚል ቃሉ
እንዳስቻለለት፣ የፈውስን ዘዴ፣
ሊያሽረው ነው
የልቤን ቁስል፣ በሳቅሽ ውዴ።

ልክ እንደ ኢብራሂም ....

እንደከለለው
ልጁን ከማረድ፣ ቃሉን ቢሞላ፣
ባንቺ ሊሻር ነው
የልቤ ላይ ቀስት፣ የአንገቴ ቢላ።

ደሞ እንደ አዩብ ....

እንደካሰለት
ሁሉ ነገሩን፣ ቢያፍር ለዱዓ፣
ሊነሳልኝ ነው
ሀጢዓት ቁስሌ፣ በፍቅርሽ ፅዋ።

ልክ እንደ ሀቢብ እንደ ሙስጠፋ ....

በውልደታቸው
እንዳስጠለለን፣ ከእሳት ዝናብ፣
ሊሸፍነኝ ነው
ከሀጢዓት ዶፍ፣ በፍቅርሽ ሂሳብ።

አልሀምዱሊላህ!!!

ደረሰ ቀኑ
ደግሞ ልንፈግግ፣ ደግሞ ልንፈካ፣
በራህማን ጥበብ
ህይወቴ ሊጥም፣ ባንቺ በረካ።

አልሀምዱሊላህ!!!

ሲቆይ ቢመስል፣ የማይደርስ ቀኑ፣
ትልቅ ቢሆንም፣ ስቃይ ውጥኑ፣
ራርቶ አቆየን፣ በእዝነት ጎኑ።

ጃኤል ኬይጊ¹
ቀኑ ደርሶም፣ ብሷል ናፍቆት፣
ጃኤል ጃኤል²
አለሁ በይኝ፣ የኔ ህይወት።

ዋን ኩጆጋ ኢገዴእ³!!!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
***
የሶማሊኛ ቃላት አገባባዊ ፍቺ:–
¹ጃኤል ኬይጊ:– የኔ ፍቅር
²ጃኤል:– ፍቅር
³ዋን ኩጆጋ ኢገዴእ:– አለውልህ በይኝ

ከላይ በተጠቀሱት ነብያቶች ላይ ሁሉ የአላህ ሰላም ይስፈን።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.3K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ