Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 30.02K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡
ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot
Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-16 12:32:24
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ቀደሳ ወአክበራ እምኵሎን መዋዕል አልዓላ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።
ቅዱስ ያሬድ

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
1.9K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 03:49:08 "ትንሣኤከ ለእለ አመነ
ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ"


በቀሲስ ይስሐቅ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.7K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, edited  00:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 03:49:07
ተነሥቷል!
Just risen!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.7K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 00:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 03:49:07 እንደሚመጡና ‘ሰማይና ምድር ያልፋል፤ ጌታ ይመጣል፤ ትንሣኤ ሙታን ይደረጋል፤ ያላችሁት የት አለ?’ እያሉ የሚክዱና የሚያስክዱ ሰዎች እንደሚመጡ አስቀድሞ ነግሮናል። (2ኛ ጴጥ 3፥1-18)።  እንዲሁም ጌታችን በወንጌሉ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ”(ዮሐ 11፥25)። ብሎ የሰበከውን ህያው ቃል ያልተገነዘቡ የቅዱስ ጴጥሮስንና የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት እንዳቃለሉና እንዳፌዙ ሁሉ ዛሬም በዘመናችን ስለትንሣኤ ሙታን፣ ስለ ዘላለማዊ ህይወት ሲነገራቸውና ሲሰበክላቸው የማያምኑ ብዙ ሰዎች መኖራቸው እንግዳ ነገር እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባናል። እኛ ግን ይልቁንም ቅዱሳት መጻፍትን በማንበብና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን በመጠየቅ ይበልጥ ስለትንሣኤ ልንረዳና በመጨረሻው ስዓት የክብር ትንሣኤ ባለቤት እንድንሆን መትጋት ይኖርብናል። በትንሣኤ የምናምንም የማያምኑም ለፍርድ መነሣታችን አይቀርምና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሙታን ትንሣኤ በሚገባ ቋንቋ አብራርቶ በምሳሌ ሲያስተምር «ነገር ግን ሰው፥ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል፡፡» ብሎ ከጠየቀ በኋላ፥ «አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፡፡» ብሏል፡፡ ከዚህም አያይዞ «የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው፡፡ በመበስበስ ይዘራል÷ ባለመበስበስ ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል÷ በኃይል ይነሣል፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል÷ መንፈሳዊ አካል ይነሣል ፤ ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ፡፡ እንዲሁ ደግሞ፡- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም (ክርስቶስ) ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው። ሁለተኛው ሰው ( ክርስቶስ ) ከሰማይ ነው፡፡ መሬታዊው እንደሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲህ ናቸው÷ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው ፡፡ የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን፡፡» ብሏል። ፩ኛቆሮ ፲፭÷፴፭-፵፱፡፡  በአጠቃላይ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እኛን የወደደበት ሕይወቱን እስከ መስጠት ደርሶ ቤዛ የሆነበትን ምሥጢር የሰው ሕሊና መርምሮ ሊደርስበት የሚችል አይደለም፡፡ ተነጻጻሪ ተወዳዳሪ አቻ ወይም አምሳያ የሌለው ልዩ ነውና፡፡ ስለሆነም የትንሣኤ ሙታንን ምሥጢር ተረድተን በክርስቲያናዊ ምግባር መኖር አለብን። በትንሳኤ ሙታን ጊዜ ስንነሣ በጌታችን ፊት እንዳናፍር በትዕዛዙና በሕጉ ጸንተን ጌታችን "ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፣ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ" (ዮሐ 6፥54)፤ እንዳለ የክብር ትንሣኤ አግኝተን ከምርጦቹ ጋር በቀኙ እንዲያቆመን የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን በመቀበል ለክብር ትንሣኤ ተዘጋጅተን ሊሆን ይገባል። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች እንደጻፈልን በ፩ኛቆሮ ፲፭÷፳-፳፫፡፡«አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል፡፡ ሞት በሰው (በቀዳማዊ አዳም) በኵል ስለመጣ፥ ትንሣኤ ሙታን በሰው (በተዋሕዶ ሰው በመሆኑ ዳግማዊ አዳም በተባለ በክርስቶስ) በኩል ሆኗልና፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኵራት ነው፤»  እንዲል የትንሣኤያቸን በኩር ክርስቶስን አብነት አድርገን፣ ቃሉን ሰምተን፣ ሕጉን ጠብቀን፣ ትዕዛዙን አክብረን፣ ትንሣኤ ልቡና ተነሥተን፣ ሥጋውን በልተን፣ ደሙን ጠጥተን፣ በንስሐ ተሸልመን፣ በፍቅረ እግዚአብሔርና በፍቅረ ቢፅ (ወንድምን በመውደድ) ጸንተን ብንኖር የትንሣኤውን ትርጉም አውቀነዋል፣ ገብቶናል ማለት ነው፡፡ ከትንሣኤ ሥጋ ትንሣኤ ልቡና ተነሥተን፣ በንስሐ ታጥበን ሥጋውና ደሙን ተቀብለን፣ ተዘጋጅተን እንድንኖር የአምላካችን ቸርነት የወላዲተ አምላክ የድንግል ማርያም፣ የቅዱሳንና የቅዱሳን መላእክት አማልጅነትና ተራዳኢነት አይለየን። አሜን!

መልካም በዓል!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.8K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 00:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 03:49:07 ትንሣኤ


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በከብቶች በረት ከተወለደበት ሰዓት ጀምሮ ለሰው ልጅ ድኅነት ሲል ከመሰደድ እስከ ሞት፤  ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልትና ግርፋትን ተቀብሎ፤ በጲላጦስ ከወንበዴዎች ጋር ተፈርዶበት፤ በቀራንዮ አደባባይ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፤ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ አዳምንና ዘሩን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከባርነት ወደ  ነፃነት መልሶ በሦስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል፤ በማቴ28፥5 ላይ “እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ወረደ፣ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፣ እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና። እንደ ተናገረው ተነስቷልና በዚህ የለም ኑና እዩ አላቸው።” ተብሎ እንደ ተገለጸው፤ ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ስልጣን በክብር ተነስቷል።  ማጽናናትና የምሥራችን ለሰው ልጆች ማብሰር ልማዳቸው የሆኑ መላእክት ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመለአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት አምላክን እንደምትወልድ እንዳበሰራት ሁሉ እነሆ ጌታም ሞቶ በተቀበረ በሦስተኛው ቀን የትንሣኤውን ብስራት በሌሊት ወደ መቃብሩ ስፍራ ለመጡ የገሊላ ሰዎች በእግዚአብሔር መለአክ አማካኝነት ተነገረ። አስቀድሞ በነብዩ ቅዱስ ዳዊት አማካኝነት ስለ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በመዝ.77፥6 “እግዚአብሔር ይነሣል ጠላቶቹም ይበተናሉ፤ እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው ጠላቶቹንም በኋላው መታ” እንዲሁም በመዝ.3፥5  “እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም እግዚአብሔር አሥነስቶኛልና ተነሣሁ” በማለት የክርስቶስን ከሙታን መነሣት  በትንቢት ተናግሯል፡፡   ሌሎች ነብያትም ክርስቶስ እንዲሞት በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ  በተለያየ ጊዜያት በትንቢትና በምሳሌ ገልጸዋል፡ ፡ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ስለትንሳኤው በምሳሌ አስተምሯል እንዲሁም በመጨረሻም እንደተናገረው በተግባር መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በስልጣኑ ተነስቷል። ሐዋርያትም በስብከታቸው እና በመጽሐፋቸው ስለ ትንሣኤው ምስክርነት በመስጠት አረጋግጠው አስፍተውና አምልተው አስተምረዋል፤ ጽፈዋል። (ዮና.2፥1፣ ሆሴ.13፥14፣ ማቴ.12፥4ዐ ማቴ 28፣ ማር 16፣ ሉቃ 24፣ ዮሐ 20 ወዘተ)። ይሁን እንጂ የጌታችን ትንሳኤ በነዚህ ሁሉ ትንቢታትና ምሳሌዎች፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት፣  እንዲሁም በጌታችን በራሱ በትምህርትም በተግባርም  የተገለፀ  ቢሆንም ስለ ትንሣኤው ለማመን ያዳግታቸው ብዙ ሰዎች ነበሩ። ከሐዋርያትም መካከል የሆነው ቅዱስ ቶማስ የተቸነከሩትን እጆቹንና እግሮቹን፣ በጦር የተውጋውን ጎኑን ካላየሁ፣ ካልዳሰስሁ የክርስቶስን መነሣት አላምንም ብሎ ጌታችን በዝግ ቤት ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ የተወጋውን ጎኑን አሳይቶ በክብር መነሣቱን እስከሚያረጋግጥለት ድረስ የጌታችንን ትንሣኤ ለማመን እንደተቸገረ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል (ዮሐ 20፥24) ይሁን እንጂ የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በስሙ ላመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ትንሣኤ ነው፡፡ ክርስቶስ ለሙታን ሁሉ በኲር ሆኖ ተነሥቶአል፡፡ የሙታንን ሁሉ መነሣት የሚያረጋግጥልን የጌታ ትንሣኤ ነው፡፡ የክርስቶስም ትንሣኤ መርገመ ሥጋ፥ መርገመ ነፍስ፤ ሞተ ሥጋ፥ ሞተ ነፍስ የተሻረበት ርደተ ገሃነም ጠፍቶ፥ በአዳም የተፈረደው ፍርድ ሁሉ ተደምስሶ፤ ፍጹም ነፃነት፣ የማይለወጥ ደስታ፣ የተገኝበት ስለሆነ ፋሲካ ይባላል፡፡ ፋሲካ ደስታ ነው እስራኤል ከግብጽ ባርነት ነፃ የወጡበትን ቀን ፋሲካ ብለውታል፡፡ የእርቅ፣ የሰላም፣ የድኅነት ቀን ነው። ከሞት ከመነሣት ከመቃብር ጨለማ ከመውጣት ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከመላቀቅ፥ ከሲኦል እስራት ከመፈታት የሚበልጥ ምንም ደስታ ሊኖር አይችልምና  ፋሲካችን እንለዋለን። ስለሆነም የጌታችን ትንሣኤ ለኛ በኩራችን ነው፡፡ እርሱን በኩር አድርገን እንነሣለንና። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች እንደጻፈው በ1ኛ ቆሮ.15፥20 “አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአል በሁለተኛው ሰው ትንሣኤ ሙታን ሆነ” እንዳለ የጌታችንን የትንሣኤውን በዓል ስናከብር የእኛም ትንሣኤያችን መሆኑን አውቀንና  ተረድተን በትንሣኤ ልቡና ተነሥተን መልካም ሥራ በመሥራት መሆን አለበት። እኛ ትንሣኤ ልቡናን ሳንነሣ በየዓመቱ ትንሣኤን ብናከብር ፈሪሳውያንን ወይም ትንሣኤ የለም ፈርሰን በስብሰን እንቀራለን ብለው የሚያምኑ ሰዱቃውያንን መምሰል ይሆናል፡፡ እንደሁም በቆላ.3፥1-4 “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኛ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ የላይኛውን አስቡ በምድር ያለውንም አይደለም እናንተ ፈጽማችሁ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ የተሠወረች ናትና ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ያን ጊዜ ከእርሱ ጋር በፍጹም ክብር ትገለጣላችሁ” ተብሎ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆላስያስ ሰዎች እንደተጻፈው የክርስቶስ ትንሣኤ ትንሣኤያችን ነው ብለን ለምናምን ሁሉ ከምድራዊ ሀሳብ ነጻ ሆነን ተስፋ የምናደርገው ትንሣኤ እንዳለን በማሰብ ከሞት በኋላ ሕይወት ከትንሣኤም በኋላ የዘለዓለም ሞት መኖሩን ሳንዘነጋ መኖር እንደሚገባን ይመክረናል፡፡ በተጨማሪም  በዮሐ.5፥28 እንደተገለጠው በትንሳኤ  ለማያምኑ ወይም ከሞት በኋላ ስላለ ሕይወት ስለማያስቡ፣ መልካም ሥራ ለማይሰሩ ሰዎች ትንሣኤ ምን እንደሚመስል ጌታችን መድኅኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር  “በመቃብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ስለዚህ አታድንቁ መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉ የሠሩም ለፍርድ ትንሣኤ ይነሣሉ” ብሏል፡፡ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የቅዱስ ቶማስን ዓይኖች ዓይኖቻችን አድርገን፤ የእርሱን ጆሮዎች ጆሮቻችን አድረገን፤ የእርሱን እጆች እጆቻችን አድርገን ትንሣኤውን በፍጹም ልባችን አምነን መኖር ይገባናል። እንዲሁም ጌታችን ለቶማስ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ብሎ እንደ ተናገረ እኛም ትንሣኤውን በመንፈስ የተረዳን ሁሉ ከትንሣኤው ብርሃን በረከትን ለማግኘት የጌታችንን ትንሣኤ ላልተረዱ ሁሉ እነርሱም እንደኛ የትንሣኤውን ብርሃን እንዲያዩ በሕይወታችን በቃልም በምግባርም ልንመሰክርላቸው ይገባል። በዘመናችንም በትንሳኤው የማያምኑ እንዳሉ ይልቁንም፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ትንሣኤ በአቴና ከተማ ሲያስተምር ትምህርቱን ባለመረዳት እንዳፌዙበት ሁሉ በአሁኑም ወቅት የሙታን ትንሣኤ ሲነገር የሚቀልዱና የሚዘብቱ ብዙዎች አሉ። (የሐዋ 17፥32)። ቅዱስ ጳውሎስ የአቴና ሰዎችን ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እንዲመለሱ፣ በጌታችን ትንሣኤ አምነው በትንሣኤው ክብርን እንዲወርሱ ቢያስተምራቸውም ብዙዎቹ ግን ድኅነትን ከመፈለግ ይልቅ ፌዝን መረጡ። ቅዱስ ጳውሎስ “ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?” (ገላ 3፥1)። ብሎ እንደ ተናገረው ዛሬም የትንሣኤውን እውነት መስማትም ሆነ መናገር የማይፈልጉ ተረፈ ሰዱቃውያን አሉ፤ ወደፊትም ይኖራሉ። እንደነዚህ ስላሉት ሰዎች ቅዱስ ጴጥሮስም በመጨረሻው በዚህ ዘመን ብዙዎች ዘባቾች
2.6K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 00:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 22:40:50
የሰሙነ ሕማማት ሰባተኛ ቀን-ቅዳሜ
ቀዳም ስዑር
ዐባይ ሰንበት
ቅዱስ ቅዳሜ
ለምለም ቅዳሜ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
1.9K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 22:40:50 የሰሙነ ሕማማት ሰባተኛ ቀን
ቅዳሜ

የማይሞተው አምላካችን በፈቃዱ ቅድስት ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላካችን እኛን ያስነሳ እና ነጻነት ይሰብከን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ነጻ ሲያወጣ በአካለ ሥጋም ያለመለያየት በመቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ሙስና መቃብር ሳያገኘው ቆይቷል።
ይህንን ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል"ነፍሱን በሲኦል አልተወም ሥጋውንም ሙስና መቃብርን አላየም መለኮቱ ከሁለቱም አልተለየም ሁለንተናው ከነፍስ ጋር በሲኦል ነበር በሲኦል ለጻድቃን የምሥራችን አበሰረ ሁለንተናው ከሥጋ ጋር በመቃብር ነበር እንጂ በቦታው ሁሉ ምሉዕ ነውና" (ሃይ. አበ ዘቄርሎስ ፸፩:፲፭-፲፮)
ለሁላችን የማያልፍ ድኅነትን ፣ ሥርየተ ኃጢአትን ፣ ቅድስናን ፣ አሸናፊነትን እና ይቅርታን ይሰጠን ዘንድ ሞታችንን ሞተ የነገረንን ትንቢት ፈጸመ" ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።" እንዲል። (ማቴ፲፪:፵)
ጌታችን ከዐርብ ሠርክ እስከ እሁድ መንፈቀ ሌሊት ድረስ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በመቃብር ዐርፏል። እነዚህ ቀንና ሌሊት የራሳቸው ትርጉም አላቸው። የነገረ ክርስቶስ መጽሐፍ ጸሐፊ መጋቤ ሐዲስ ክቡር ዶክተር ሮዳስ ስለ ሶስት ምክንያት እንደሆነ ይጠቅሳሉ:-
፩. ለአዳም ፣ ለሔዋን ፣ ለሕጻናቱ ሊክስ
፪. ለሥጋ ፣ ለነፍስ ፣ ለደመ ነፍስ ሊክስ
፫. ሞትን ፣ ፍዳን ፣ ኃጢአትን ሊያጠፋ ጌታችን ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በመቃብር ዐርፏል። (ነ.ክርስቶስ ገጽ፻፸፰)
አቆጣጠሩ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት የሚመጣው ስንል ከላይ እንዳየነው የተቀበረው በሠርክ (፲፩) ሰዓት ነው የተነሳው ደግሞ እሁድ መንፈቅ(፮) ሰዓት ነው።
አንደኛው ቀን ከአርብ ነግህ (ጠዋት) - ስድስት ሰዓት ቀን ሆኗል ፣ ከአርብ ስድስት - ዘጠኝ ሰዓት ጨልሟል ሌሊት ሆኗል ይህ አንድ ቀን ይባላል።
ሁለተኛው ቀን ከአርብ ዘጠኝ ሰዓት-ሠርክ ቀን ሆኗል ፣ የአርብ ሌሊት ሲደመር ይህ ሁለተኛ ቀን ይባላል።
ሦስተኛው ቀን ከቅዳሜ ነግህ እስከ ሠርክ ቀን ሆኗል ፣ የቅዳሜ መንፈቀ ሌሊት ሲደመር ሦስተኛው ቀን ይባላል

ቀዳም ስዑር
ጌታችን ቀድሞ አዳምን ሔዋንን አርብ ፈጥሮ ቅዳሜ እንዳረፈ ሁሉ አሁንም ያጡትን ገነትን ባጡበት አርብ ዕለት ሰጥቶ ቅዳሜ በመቃብር አርፎባታል ስለዚህም የተለየች ቅዳሜ ናት።

አራቱ ስያሜዎች

፩. ቀዳም ስዑር
ስዑር ማለት የግእዝ ግስ ሆኖ በአማረኛ የተሻረ ማለት ሲሆን በአንድ ላይ ሲነበብ የተሻረ ቅዳሜ የሚል ትርጓሜ እናገኛለን። ምክንያቱ እንደ ቀደመቺቱ ሰንበት የማናርፍባት ይልቁንም ደቀመዛሙርቱን አብነት አድርገን በጾም በሀዘን ህማሙን እያሰብንባት የምናሳልፋት ቀን በመሆኗ ቀዳም ስዑር ተብላለች።

፪. ዐባይ ሰንበት
አምላካችን ሃያ ሁለቱን ስነ ፍጥረት ፈጥሮ እንዳረፈባት የማዳኑንም ስራ በመስቀል ላይ ፈጽሞ በአዲስ መቃብር ዐርፎ ውሎባታልና ዐባይ ሰንበት ተብላለች።

፫.ቅዱስ ቅዳሜ
በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ ነፍሳትን አድኖበታል ፣ ሲዖልን በዝብዟል ፣ ምርኮን ለራሱ ጨምሯል ፣ ዲያብሎስን አሳፍሯል ፣ የዕዳ ደብዳቤያችንን ደምስሷል ከሌሎች ቀናት ሁሉ የተለየች በመሆኗ ቅዱስ ቅዳሜ ተብላለች።

፬. ለምለም ቅዳሜ
በዚህ ዕለት በኖኅ ዘመን የጥፋቱ ውኃ ማለቁን የሰላም አብሳሪ እርግብ ለኖኅ ቄጤማ እንዳመጣችለት አሁንም የጥፋቱ ሞት ራቀልን ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገርን ፣ አንቀጸ ገነት ተከፈተልን ሲሉ ካህናት አባቶቻችን የቅዳሜው የነግህ ጸሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ለምዕመኑ ለምለም ቄጤማ ስለሚሰጡ ምዕመናንም በግንባራችን ላይ አድርገን ትንሣኤውን ስለምናከብር ለምለም ቅዳሜ ተብላለች።

"ዲያብሎስ ታሰረ ጌታ ተመረመረ"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.1K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 14:47:24 አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ:
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ።

በዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
575 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 14:47:24
"...እራሳቸውን እንደ መሮ ወርዳቸውን እንደ ሞረድ ፬ ማዕዘን ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸውን እንደ ወስፌ ፭ ችንካር ሰርተው ሳዶር በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን አላዶር በሚባል ችንካር ግራ እጁን ከግማደ መስቀል አንድ አድርገው ቸነከሩት፤ አዴራ በሚባል ችንካር ማህል ልቡንቸነከሩት ዳናት በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ከ እግረ መስቀል ጋርቸነከሩት ሮዳስ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት..."
-ሕማማተ መስቀል

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
578 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 23:13:54 አገቱኒ ከለባት ብዙኃን

በዘማሪ ዲ/ን ዳዊት ፋንታዬ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.0K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ