Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.97K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡
ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot
Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-04 05:58:51
ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

ካረገ በኋላ በአስረኛው ቀን፤
ወደ አለም ላከው ጰራቅሊጦስን።

በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ፤
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ።

ቀኑም ደረሰና በሃምሳኛው እለት፤
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ፀሎት፤
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት።

ያ የተነገረው ያ የተስፋ ቃል፤
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሳል።

ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት፤
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት።

ከሶስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን፤
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን።

ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.9K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 05:58:51
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.4K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 05:58:51 መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢተሰምየ ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ ጰራቅሊጦስሃ። ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ ……መንፈስ ቅዱስም ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት ጰራቅሊጦስ አልተባለም ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም ወልድ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)

በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን፡፡
ምንጮች፤

መዝገበ ታሪክ፣ ክፍል ፪፤ መምህር ኅሩይ ኤርምያስ፤ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም፤ ገጽ ፹፬-፹፭፡፡

መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፲፰ ቀን፣ መጽሐፈ ምሥጢር፡፡

መጽሐፈ ግጻዌ፡፡

ማኅቶተ ዘመን፣ መምህር በሙሉ አስፋው፤ ፳፻፩ ዓ.ም፤ ገጽ ፻፺፭-፪፻፬፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.3K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 05:58:51 በዓለ ጰራቅሊጦስ

መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ጰራቅሊጦስ ናዛዚ መጽንዒ መስተፍሥሒ፤ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ አጽናኝም የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‹‹አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ ‹‹እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል›› እንዲል። (ዮሐ.፲፬፥፳፮፤ ፲፭፥፲፮)

ጰራቅሊጦስ የሚለው የመንፈስ ቅዱስ ስም የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ መሆኑም ከማሳየት በላይ፤ ፍጹም አካል ያለው አምላክ እንደሆነ አመልካች ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጰራቅሊጦስ ማለት መሪ፣ አጽናኝ፣ ረጂ ማለት መሆኑን በስፋት ካስተማሩ ሊቃውንት በቀዳሚነት ይነሳል። ጰራቅሊጦሰ የተባለው መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ያላትን እምነቷን ስትገልጥ ‹‹ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረፀ እም አብ ንሰግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ››፤ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን፣ እናመሰግነዋለን፤›› የሚል ነው።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ፤ የቅድስናም ምንጭ ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ወስመ መንፈስ ቅዱስ ነቅዐ ቅድሳትየ፤ የመንፈስ ቅዱስም ስም የቅድስናየ መገኛ ነው›› በማለት ገልጾታል። (መጽሐፈ ምሥጢር)
ቅዱስ ባስልዮስም በቅዳሴው ‹‹ሃሌ ሉያ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ንጹሕ ክቡር ልዩ ነው›› በማለት አምላካዊ ስሙን ጠርቶ አመስግኖታል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ዕለት ዕለት በምታከናውነው ሥርዓተ ቅዳሴ ‹‹መንጽሒ ወመጽንዒ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ ክቡር ምስጉን ነው›› እያለች የአምላክነት ስሙን ጠርታ ታመሰግነዋለች።
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ሊያጸኑ ከሓድያንን ሊለዩ (ሊያወግዙ) ሲሰባሰቡ በመካከላቸው ተገኝቶ ውሳኔ ያስወስናቸው የነበረው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ሲገልጹ ጰራቅሊጦስ የተባለ ስሙን ጠርተው እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ወሀሎ ምስሌሆሙ ኅብረ መንፈስ ቅዱስ …. ጰራቅሊጦስ የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም በጉባኤያቸው ነበረ፡፡›› (መጽሐፈ ምሥጢር)
ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ አረፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ (ሐዋ.፪፥፩-፬)

ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይከበራል፡፡ የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ሆነው ሁሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚሆነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር፡፡
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለሆነባቸው ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ፣ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤››በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡ (ኢዩ.፪፥፳፰)
በትምህርቱም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን ሐዋርያት እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?››ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ንስሓ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል፡፡(ሐዋ.፪፥፩-፵፩)
ቅዱሳን ሐዋርያት፤ ‹‹በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤›› በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም የበዓሉን ታላቅነት ከመሰከሩ በኋላ ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ አዝዘዋል፤ በዚህ ወቅት መጾምና ማዘን ተገቢ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡ (ዲድስቅልያ ፴፥፴፰-፴፱፤ ፴፩፥፷፱-፸)
ቅዱሳን ሐዋርያትም ‹‹ከአብ የሠረፀ የሁላችንም መጽናኛ የሚሆን ዓለሙንም ሁሉ ያዳነ ከአብና ከወልድ ጋር ህልው የሚሆን መንፈስ ቅዱስን ላከልን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስም አንድ ነው›› ብለዋል። በሌላም ነቢዩ ዳዊት ስለመንፈስ ቅዱስ ‹‹መንፈስህን ከእኔ አታርቅ አለ፤ ዳግመኛም በሰውነቴ እውነተኛ መንፈስን አጽናልኝ፣ ከሁሉ በሆነ መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ አለ›› በማለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አጽናኝ መካሪ መባሉን አስተምሯል። (መዝ. ፶፥ ፲-፲፪፤ መጽሐፈ ምሥጢር)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ እግዚአብሔር
2.6K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, edited  02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 00:48:40 "በማእከለ አስዋክ"
በዘማሪት መቅደስ ዓለሙ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
5.3K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 00:43:02
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
4.5K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 21:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 00:42:47 ግንቦት ፳፩
ደብረ ምጥማቅ


ከሠላሳ ሶስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው። ደብረ ምጥማቅ በግብፅ ሀገር በምኔተ ገምኑዲ አቅራቢያ የምትገኝ ቦታ ናት። እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ዐብይ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር። ይኸውም አልቀረ፤ በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል።

በዚህም ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበረ ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሷት ታይታለች። “እንዘ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኃምሰ ዕለታተ” እንዳለ ደራሲ በልጇ የመለኮት ብርሃን አሸብርቃ መላእክት: ሊቃነ መላእክት: ኪሩቤል: ሱራፌል ከበዋት ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ደናግላን: መነኮሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ይመጣሉ። ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው በእያንዳንዱ እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር። ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተከትሎ ቅዱስ መርቆርዮስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል።

ከፊቷ ብርሃን የተነሣ 5 ቀን ሌሊቱና ቀኑ አይታወቅም ነበር። በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ወደ ላይ ሲወረውሩላት የፈቀደችውን ተቀብላ ትልክላቸዋለች። ከዚያም ለበረከት ይካፈሉታል። ከተሰበሰቡትም እስኪ እገሌን አስነሺልን እያሉ ሲለምኗት አስነሥታ በሕይወተ ሥጋ ታሳያቸው ነበር። እንዲህ እየሆኑ በፍጹም ደስታ ሰንብተዋል። እስከ አምስት ቀንም ምዕመናኑን አረማውያኑንም አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች። ከዚህም በኋላ ምዕመናኑም አረማውያኑም በየዓመቱ እኚህን አምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል። የበዓሉ መታሰቢያ ከግንቦት 21 እስከ 25 ቀን ነው።

ግንቦት 21 በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡

ግንቦት 22 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 23 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 24 እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡

ግንቦት 25 ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡

በዚህ ዕለትም እናታችን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለ5 ቀን በግልጽ መታየቷ የሞቱት መነሳታቸው ብርሃን መሆኑ ጨለማ መጥፋቱ የሰውን ልመና መቀበሏ ወዘተ ይነገራል። የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፣ ጣዕሟን ፍቅሯን አይለይብን። የዓመት ሰው ይበለን፣ አሜን!

“ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል።” ቅዳሴ ማርያም

“ሰላም ለእለ ርእዩኪ ከመ ዐይነ ወለት ኀበ እማ፣
መዋዕል ኃምስ እስከ ይትፌጸማ፣
ማርያም ንግስት ዘደብረ ምጥማቅ ከተማ፣
ብፁዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ፣
ወብፁዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ።” እን ዐርኬ

ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ 2 ገጽ 87፣ መድብለ ታሪክ ገጽ 383

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
4.6K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 21:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 11:34:44
የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ የተጣለውን ዕግድ እንዲያነሳ የመንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት  ጠየቀ !!!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም የማኅበረ ቅዱሳንን ቴሌቪዥን ማገዱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዕግዱ እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለባለሥልጣኑ አስገብቷል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን መንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብዳቤው ላይ እንደጠቀሱት የማኅበሩ ቴሌቪዥን የቤተክርስቲያኒቱ አንዱ ልሣን በመሆኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት በሙሉ በቤተክርስቲያን ሕግና ሥርዓት የሚዳኝ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል ።

በተጨማሪም ባለሥልጣኑ ማኅበሩን ምንም ዓይነት ማብራሪያ ሳይጠይቅና ማስጠንቀቂያም ሳይሰጥ ያደረገው ዕግድ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ ዕግሱ እንዲነሳም በቤተ ክርስቲያን ስም ጠይቀዋል።

ተሚማ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
5.4K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 06:30:15
ዐረገ በስብሀት ዐረገ በእልልታ :
ሞትን ድል አድርጎ የሠራዊት ጌታ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
5.2K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 06:30:15
ምስባክ፦
ዐረገ እግዚአብሔር በይባቤ ፤
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
4.4K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ