Get Mystery Box with random crypto!

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ የተጣለውን ዕግድ እንዲያነሳ የመንበረ  | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ የተጣለውን ዕግድ እንዲያነሳ የመንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት  ጠየቀ !!!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም የማኅበረ ቅዱሳንን ቴሌቪዥን ማገዱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዕግዱ እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለባለሥልጣኑ አስገብቷል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን መንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብዳቤው ላይ እንደጠቀሱት የማኅበሩ ቴሌቪዥን የቤተክርስቲያኒቱ አንዱ ልሣን በመሆኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት በሙሉ በቤተክርስቲያን ሕግና ሥርዓት የሚዳኝ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል ።

በተጨማሪም ባለሥልጣኑ ማኅበሩን ምንም ዓይነት ማብራሪያ ሳይጠይቅና ማስጠንቀቂያም ሳይሰጥ ያደረገው ዕግድ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ ዕግሱ እንዲነሳም በቤተ ክርስቲያን ስም ጠይቀዋል።

ተሚማ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox