Get Mystery Box with random crypto!

ግንቦት ፳፩ ደብረ ምጥማቅ ከሠላሳ ሶስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው። ደብረ ምጥማቅ በግብፅ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ግንቦት ፳፩
ደብረ ምጥማቅ


ከሠላሳ ሶስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው። ደብረ ምጥማቅ በግብፅ ሀገር በምኔተ ገምኑዲ አቅራቢያ የምትገኝ ቦታ ናት። እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ዐብይ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር። ይኸውም አልቀረ፤ በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል።

በዚህም ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበረ ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሷት ታይታለች። “እንዘ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኃምሰ ዕለታተ” እንዳለ ደራሲ በልጇ የመለኮት ብርሃን አሸብርቃ መላእክት: ሊቃነ መላእክት: ኪሩቤል: ሱራፌል ከበዋት ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ደናግላን: መነኮሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ይመጣሉ። ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው በእያንዳንዱ እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር። ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተከትሎ ቅዱስ መርቆርዮስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል።

ከፊቷ ብርሃን የተነሣ 5 ቀን ሌሊቱና ቀኑ አይታወቅም ነበር። በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ወደ ላይ ሲወረውሩላት የፈቀደችውን ተቀብላ ትልክላቸዋለች። ከዚያም ለበረከት ይካፈሉታል። ከተሰበሰቡትም እስኪ እገሌን አስነሺልን እያሉ ሲለምኗት አስነሥታ በሕይወተ ሥጋ ታሳያቸው ነበር። እንዲህ እየሆኑ በፍጹም ደስታ ሰንብተዋል። እስከ አምስት ቀንም ምዕመናኑን አረማውያኑንም አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች። ከዚህም በኋላ ምዕመናኑም አረማውያኑም በየዓመቱ እኚህን አምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል። የበዓሉ መታሰቢያ ከግንቦት 21 እስከ 25 ቀን ነው።

ግንቦት 21 በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡

ግንቦት 22 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 23 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 24 እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡

ግንቦት 25 ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡

በዚህ ዕለትም እናታችን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለ5 ቀን በግልጽ መታየቷ የሞቱት መነሳታቸው ብርሃን መሆኑ ጨለማ መጥፋቱ የሰውን ልመና መቀበሏ ወዘተ ይነገራል። የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፣ ጣዕሟን ፍቅሯን አይለይብን። የዓመት ሰው ይበለን፣ አሜን!

“ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል።” ቅዳሴ ማርያም

“ሰላም ለእለ ርእዩኪ ከመ ዐይነ ወለት ኀበ እማ፣
መዋዕል ኃምስ እስከ ይትፌጸማ፣
ማርያም ንግስት ዘደብረ ምጥማቅ ከተማ፣
ብፁዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ፣
ወብፁዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ።” እን ዐርኬ

ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ 2 ገጽ 87፣ መድብለ ታሪክ ገጽ 383

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox