Get Mystery Box with random crypto!

ሐዋርያት ተባበሩ፤ በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤ ቃሉን አስተማሩ። ካረገ በኋላ በአስረኛው ቀን፤ ወደ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

ካረገ በኋላ በአስረኛው ቀን፤
ወደ አለም ላከው ጰራቅሊጦስን።

በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ፤
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ።

ቀኑም ደረሰና በሃምሳኛው እለት፤
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ፀሎት፤
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት።

ያ የተነገረው ያ የተስፋ ቃል፤
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሳል።

ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት፤
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት።

ከሶስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን፤
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን።

ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox