Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian News Hub 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewshubet — Ethiopian News Hub 🇪🇹 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewshubet — Ethiopian News Hub 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ethionewshubet
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ ቴሌግራም ቻናላችን በደህና መጡ
👉በአለም ላይ ያሉ አዳዲስ ክስተቶችን
👉ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው መድረሻ! ልምድ ባካበቱ ጋዜጠኞች
👉አዳዲስ ዜናዎችን
👉ጥልቅ ትንታኔዎችን እና አስተያየቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ ያለመታከት ይሰራል። በኛ ቻናል ምንም አያመልጥዎትም - ከፖለቲካ እስከ ንግድ ፣ ከመዝናኛ እስከ ሳይንስ ያለውን ሁሉ አንሸፍናለን

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-06 22:13:44 ኡጋንዳዊያን ሀብት ንብረታቸውን እየሸጡ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ መሆኑ ተሰምቷል። ኡጋንዳዊያኑ የአለም ፍፃሜ በመድረሱ ወደ ኢትዮጵያ እየገባን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የአለም ፍፃሜ ፈጥኖ አይደርስም ማለታቸው Africa News ከ KAMPALA, Uganda ዘግቧል:: https://www.aa.com.tr/en/africa/hundreds-of-ugandan-sect-members-flee-to-ethiopia-fearing-doomsday/2837933#
50 views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 21:18:50 ⨳blueprint for national exit examination to be held in 2015 E.c


ለዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ለእያንዳንዱ ዲፓርትመንት ለመውጫ ፈተና የተዘጋጀ(blue print)

ማሳሰቢያ፡-ከላይ ባለው ፋይል ያልተለቀቀ የትምህርት ክፍል ካለ ከዲፓርትመንት ሀላፊያችሁ ጋር በመነጋገር ሙሉ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።


ተመራቂ ተማሪዎች ራሳችሁን ለመውጫ ፈተና ከወዲሁ እንድታዘጋጁ  እናሳስባለን
50 viewsedited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 10:05:27
በህንድ ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር የሄደችበት ባል በበቀል ያፈቀረችውን ሰው ሚስት አገባ

በህንድ ቢሃር ግዛት ኔራጅ እና ሩቢ ዴቪ የተባሉ ጥንዶች እ.ኤ.አ በ2009 ጋብቻቸውን ፈፅመው አራት ልጆችን ወልደው ለመሳም በቅተዋል። በጊዜ ሂደት ግን የኔራጅ ሚስቱ ሙከሽ ከሚባል ሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት ትጀምራለች። ይህንን ግንኙነት ለመቁረጥ የከበዳት ሩቢ ባሏን ትታ ከሙከሽ ጋር ለመኖር ትወስናለች።

ኔራጅ ሽማግሌዎችን ልኮ ባለቤቱን እና ሙከሽ ቢያስመክርም ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም።ኔራጅ ለፖሊስ ክስ ቢመሰርትም ወዳና ፈቅዳ ወደ ሙከሽ ቤት መግባቷን ትናገርና ክሱ ውድቅ ይሆናል።

ኔራጅ ጥላው የሄደችው ሚስቱ ያገባት ግለሰብ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት መሆኑን እንደ ጥረ አጋጣሚ ይወስደዋል።ሚስቱ ወደ ቤት የመመለስ ፍላጎት እንደሌላት ካየ በኋላ የሙኬሽን ሚስት እንድታገባው ይጠይቃታል። እሷም በጥያቄው ተደስታ ጥንዶቹ ባለፈው ወር ጋብቻቸውን ፈፅመዋል።አስገራሚው የፍቅር ታሪክ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በካጋሪያ አውራጃ ውስጥ የከተማው መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ሁሉም ልጆች ወደ እናቶቻች በሚል ስምምነት ፈፅመዋል።
54 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 09:28:18
ታዋቂው ቲክቶከር በሪያሊቲ ሾው ሊመጣ ነው

ሴኔጋል ተወልዶ በጣሊያን ያደገው ታዋቂው ቲክቶከር ካቢ ላሜ በጣሊያን የሪያሪቲ ሾው ቴሌቪዥን ላይ የሚቀርበውን የጣሊያኑን ጎት ታለንት በዳኝነት ለመምራት መቀላቀሉን የአፍሪካን ላይፍስ መረጃ ያሳያል፡፡

ላሜ በአሁኑ ጊዜ በአለማችን ካሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን የተለያዩ ውስብስብ ዘልማዳዊ ድርጊቶችን እና አፈ-ታሪኮችን እንዴት ቀለል ባለ መንገድ ሊቀርቡ እንደሚገባ የሚያሳዩ አጫጭር ቪዲዮዎችን በማቅረብ ይታወቃል። 

ላሜ በ2020 የፋብሪካ ስራውን ካጣ በኋላ ወደ ቲክቶኩ ዓለም በመግባት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ150 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን ማፍራት የቻለ እና ዓመታዊ ገቢው 13 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ቲክቶከር ነው።
42 views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 09:27:38 " ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን " - የዳዋ ዞን አስተዳደር

በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ባጋጠመ ድርቅ በርካታ እንስሳት የሞቱ ሲሆን  የሰዎች ሕይወትም አደጋ ላይ መውደቁ ተገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር ያለው ሁኔታ ከአቅም በላይ መሆኑን አስታውቋል።

ከኦሮሚያ የቦረና ዞን ጋር የሚዋሰነው ዞኑ፣ በድርቅ የተነሳ ከሚሞቱ እንስሳት አልፎ ሰዎች #ለሆስፒታል እየተዳረጉ መሆኑን ገልጿል፡፡

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

" የድርቁ ጉዳት ከዞኑ አቅም በላይ ነው።

ዞናችን ከቦረና ጋር በሁለት ወረዳዎች በኩል ይዋሰናል፡፡ ወደ 700 ሺሕ የሚጠጋ አርብቶ አደር ነዋሪ ያለው ሲሆን፣ ለ3 ተከታታይ ዓመታት የደረሰው ድርቅ ከብቱን በሙሉ ጨርሶበታል።

በክልሉ አደጋ ሥጋት ቢሮና በተለያዩ የዕርዳታ ድርጅቶች ርብርብ ዘንድሮ ለድርቁ ተጎጂዎች ዕርዳታ እየቀረበ ነው ይሁን እንጂ ዕርዳታው በቂ አይደለም። ችግሩም ከአቅም በላይ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ለሚገኘው ለአጎራባቻችን ቦረና ዞን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንዳለው ሁሉ፣ ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን። "

ዳዋ ዞን በሥሩ ሞያሌ፣ ሙባረክ፣ ካደዱማና ሁደት የተባሉ አራት ወረዳዎች ያሉት ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ባለማግኘቱ ትልቁ የዳዋ ወንዝ ጭምር ደርቋል።

ድርቅ የሚቋቋሙ ግመሎችን ጨምሮ ከብቶችና ፍየሎች በከፍተኛ ቁጥር ማለቃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
43 views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 15:23:41
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ!

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እና በ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዳስታወቁት፤ሚኒስቴሩ የሥራ ገበያውን እና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መቁረጫ ነጥብን እንዳዘጋጀም ነው የጠቆሙት፡፡

በዚህም መሰረት ከቴክኒክና ሙያ ውጪ ባሉ ማዕከላት የሚስተናገዱትን ሳይጨምር በሥልጠና ዘመኑ 608,666 የሚሆኑ ሰልጣኞች ወደ ቴክኒክና ሙያ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትሯ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው፤ በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች ግን የሚስተናገዱት በ 2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል፡፡

የ2015 ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ላይ ተያይዟል።
86 viewsedited  12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 10:05:03
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መቀሌ ገቡ !!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ አቀኑ።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ተቀብለዋል ።

ምንጭ: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

#ዳጉ_ጆርናል
69 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 14:45:07
ቴዲ አፍሮ 1 ሚሊዮን ብር በቦረና ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች አደረገ !!

#ዓድዋ_127_ለቦረና

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ የዘንድሮን የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚፈልገው የቦረና ሕዝባችን የ1ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

Via :- ያሬድ ሹመቴ
88 views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 12:15:53 በአዲስ አበባ በአንድ ግቢው ውስጥ ጨቅላ ህጻን በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ተጥሎ ህይወቱ አልፎ ተገኘ

ከ15 ቀናት በፊት በዚሁ ግቢ ውስጥ መንታ ህጻናት ህይወታቸዉ አልፎ ተገኝቷል


ትላንት የካቲት 19 ከምሽት 5:43 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታዉ አባጃሌ በተባለዉ አካባቢ ጨቅላ ህጻን በመጸዳጃ ቤት ተጥሎ ህይወት አልፎ መገኘቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል ።

የህጻኑን አስከሬን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከመጸዳጃ ቤት ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብሰራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ህጻኑ በተጠለበት በዚሁ ግቢ ዉስጥ ከ15 ቀናት በፊት ሁለት መንታ ህጻናት ህይወታቸዉ አልፎ በመገኘቱ የህጻናቱን ወላጅ እናት በቁጥጥር ስር አዉሎ ፓሊስ እያጣራ ባለበት ሁኔታ ይህ ክስተት ማጋጠሙንም አቶ ንጋቱ ጨምረው ነግረውናል።

ትላንት ምሽት በመጸዳጃ ቤት ተጥሎ የተገኘዉን ጨቅላ ህጻን የማን እንደሆነ ጉዳይም ፖሊስ እያጣራ ይገኛል።
76 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 10:02:31 ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ላይ “ዕልቂትና ውድመት” ሊያስከትል ይችላል የተባለ የኬሚካል ክምችት መኖሩን መንግስት ራሱ አስታውቆ ነበር። ይህ አደገኛ የኬሚካል ክምችት አሁንም መፍትሄ አላገኘም። ዋዜማ ለምን ችግሩን ማስወገድ አልተቻለም? ስትል ጠይቃለች። አንብቡት

ዋዜማ – በግልና መንግስት ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው የመጠቀሚ ጊዜ ያለፈባቸውን ኬሚካሎችን ለማስወገድ ከሁለት አመት በፊት ተይዞ የነበረው አቅድ የዓለም ባንክና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች ሊሰጡ ቃል የገቡትን ገንዘብ ባለመልቀቃቸው ኬሚከሎቹ አሁንም አደጋ እንደደቀኑ መሆናቸውን የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ አስታወቀ፡፡
የኬሚካል ክምችቱ የተፈጠረው ከውጪ ሀገር ለተለያዩ አገልግሎቶች ተገዝተው በወቅቱ ጥቅም ላይ ባለመዋላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው በማለፉ ነው።
የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ ለዋዜማ እንደገለጹት የተከማቹ ኬሚካሎቹን ለማስወገድ በ 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አማካኝነት ጥናት ተደርጎ ለማስወገድ እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ገንዘቡን ማግኘት ባለመቻሉ ከእቅዱ ተግባራዊ መሆን አልቻለም።

‹‹ኬሚካሉን ለማስወገድ በጀት ይፈለጋል፤ ይህን በጀት ገንዘብ ሚንስቴር እፈልጋለሁ አለ፤ ነገር ግን ገንዘቡ አልተገኘም ጉዳዩም ባለበት ቆሟል›› ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ኬሚካሉን ለማስወገድ በጀት ከመንግስት መመደብ የማይቻል በመሆኑና ይህን ገንዝብ ማግኘት የሚቻለው ከአለም ባንክ እና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች ቢሆንም፤ እነዚህ ተቋማት ባለፉት ሁለት አመታት ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ጥሩ ባለመሆኑ ገንዘቡ ተገኝቶ ኬሚካሉ ሊወገድ አልቻለም ብለዋል፡፡

አቶ ሃጂ እንደተናገሩት በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በክምችት ላይ ያለው ኬሚካል ለማስወገድ የሚረዳውን ገንዘብ ለማግኘት በገንዘብ ሚንስቴር የኢኮኖሚክ ትብብር ሚንስቴር ዴእታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው ለሚመሩት ዘርፍ መመራቱን ተናግረዋል፡፡
ዋዜማ ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቃቸው ወ/ሮ ሰመሪታ ጉዳዩን እናጣራለን የሚል መልስ በመስጠት ስልካቸውን ዘግተዋል፡፡

የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ከፈነዱ በሰዎችና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ የተባሉት የግብርናና የኢንዱስትሪ ኬሚካሎች ሲሆኑ ዲዲቲ፣ ኦርጋኖ ፎስፌትና ኦርጋኖ ክሎሪን እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

የክምችቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ የጠየቅናቸው ባለሙያዎች አብዛኛው ክምችት አዲስ አበባ መሆኑንና ቀላል የማይባል ክምችት በክልል ከተሞች መኖሩን ነግረውናል። የክምችቱን መጠን በአሀዝ መግለፅ ግን አደጋውን የበለጠ አስፈሪ ከማድረግ በዘለለ ሌላ አደጋ ይጋብዛል በሚል ከማብራራት ተቆጥበዋል።

አቶ ሃጂ ከሁለት አመት በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ተከማችተው የሚገኙት ኬሚካሎች በቶሎ ካልተወገዱ አደጋቸው የከፋ ሊሆን እንደሚቸል ተናግረው ነበር፡፡

በነሃሴ 2012 ዓ.ም በመካከከለኛው ምስራቅ ውስጥ በምትገኘው ሊባኖስ – ቤይሩት ባጋጠመ የ2,700 ቶን አሞኒየም ናይትሬት የተሰኘ ከባድ የኬሚካል ክምችት ፍንዳታ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማለፉን፣ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸውና ከአስራ አምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የኢኮኖሚ ውድመት ማጋጠሙ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ተከማችተው የሚገኙ ዲዲቲ፣ ኦርጋኖ ፎስፌትና ኦርጋኖ ክሎሪን ኬሚካሎችን ለማስወገድ ከ4.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ፣ የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል፡፡

[ዋዜማ]
67 viewsedited  07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ