Get Mystery Box with random crypto!

ታዋቂው ቲክቶከር በሪያሊቲ ሾው ሊመጣ ነው ሴኔጋል ተወልዶ በጣሊያን ያደገው ታዋቂው ቲክቶከር ካ | Ethiopian News Hub 🇪🇹

ታዋቂው ቲክቶከር በሪያሊቲ ሾው ሊመጣ ነው

ሴኔጋል ተወልዶ በጣሊያን ያደገው ታዋቂው ቲክቶከር ካቢ ላሜ በጣሊያን የሪያሪቲ ሾው ቴሌቪዥን ላይ የሚቀርበውን የጣሊያኑን ጎት ታለንት በዳኝነት ለመምራት መቀላቀሉን የአፍሪካን ላይፍስ መረጃ ያሳያል፡፡

ላሜ በአሁኑ ጊዜ በአለማችን ካሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን የተለያዩ ውስብስብ ዘልማዳዊ ድርጊቶችን እና አፈ-ታሪኮችን እንዴት ቀለል ባለ መንገድ ሊቀርቡ እንደሚገባ የሚያሳዩ አጫጭር ቪዲዮዎችን በማቅረብ ይታወቃል። 

ላሜ በ2020 የፋብሪካ ስራውን ካጣ በኋላ ወደ ቲክቶኩ ዓለም በመግባት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ150 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን ማፍራት የቻለ እና ዓመታዊ ገቢው 13 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ቲክቶከር ነው።